caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Rahmaan الرحمن

78 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 97

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱلرَّحْمَٰنُ

Amharic Translation - Africa Academy1. አር-ረህማን

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَّمَ ٱلْقُرْءَانَ

Amharic Translation - Africa Academy2. ቁርኣንን አስተማረ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ

Amharic Translation - Africa Academy3. ሰውን ፈጠረ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَّمَهُ ٱلْبَيَانَ

Amharic Translation - Africa Academy4. መግለፅንም አስተማረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ بِحُسْبَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy5. ጸሐይና ጨረቃ በተወሰነ (በየሂሳባቸው) ልክ ይሄዳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلنَّجْمُ وَٱلشَّجَرُ يَسْجُدَانِ

Amharic Translation - Africa Academy6. የሰማይ ከዋክብትና የምድር ዛፎችም ለእርሱ ይሰግዳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلْمِيزَانَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ሰማይንም ከፍ አደረጋት:: የትክክለኛነትን ሚዛንንም አስቀመጠ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَّا تَطْغَوْا۟ فِى ٱلْمِيزَانِ

Amharic Translation - Africa Academy8. በሚዛን ስትመዝኑም እንዳትበድሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَقِيمُوا۟ ٱلْوَزْنَ بِٱلْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا۟ ٱلْمِيزَانَ

Amharic Translation - Africa Academy9. መመዘንንም በትክክል መዝኑ:: ስትመዝኑም አታጉድሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ

Amharic Translation - Africa Academy10. ምድርንም ለፍጡር አደላደላት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهَا فَٰكِهَةٌ وَٱلنَّخْلُ ذَاتُ ٱلْأَكْمَامِ

Amharic Translation - Africa Academy11. በውስጧ እሸትም ባለ ሽፍን የሆኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْحَبُّ ذُو ٱلْعَصْفِ وَٱلرَّيْحَانُ

Amharic Translation - Africa Academy12. ባለቅርፊት ቅንጣትና ባለ መልካም መዓዛ ቅጠሎችም ያሉባት ስትሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy13. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች መካከል በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ مِن صَلْصَٰلٍ كَٱلْفَخَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy14. ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَخَلَقَ ٱلْجَآنَّ مِن مَّارِجٍ مِّن نَّارٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. ጂንንም ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ፈጠረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy16. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبُّ ٱلْمَشْرِقَيْنِ وَرَبُّ ٱلْمَغْرِبَيْنِ

Amharic Translation - Africa Academy17. የሁለቱ ምስራቆችና የሁለቱ ምዕራቦች ጌታ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy18. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ

Amharic Translation - Africa Academy19. ሁለቱም ባህሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ

Amharic Translation - Africa Academy20. እንዳይዋሀዱ በመካከላቸው የማይታይ መጋረጃ አለ:: አንዱ በሌላው ላይ ወሰን አያልፉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy21. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَخْرُجُ مِنْهُمَا ٱللُّؤْلُؤُ وَٱلْمَرْجَانُ

Amharic Translation - Africa Academy22. ሉልና መርጃን የተባሉት ማዕድናት ከሁለቱ (ባህሮች) ይወጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy23. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُ ٱلْجَوَارِ ٱلْمُنشَـَٔاتُ فِى ٱلْبَحْرِ كَٱلْأَعْلَٰمِ

Amharic Translation - Africa Academy24. እንደ ጋራዎች ሆነው በባህር ውስጥ የተሰሩት ተንሻላዮችም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy25. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy26. በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو ٱلْجَلَٰلِ وَٱلْإِكْرَامِ

Amharic Translation - Africa Academy27. የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ብቻ ይቀራል (አይጠፋም)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy28. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْـَٔلُهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ كُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِى شَأْنٍ

Amharic Translation - Africa Academy29.በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል። በየቀኑ ሁሉ እርሱ በስራ ላይ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy30. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَنَفْرُغُ لَكُمْ أَيُّهَ ٱلثَّقَلَانِ

Amharic Translation - Africa Academy31. እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ መቆጣጠር በእርግጥ እንገኛለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy32. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰمَعْشَرَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ إِنِ ٱسْتَطَعْتُمْ أَن تَنفُذُوا۟ مِنْ أَقْطَارِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ فَٱنفُذُوا۟ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلْطَٰنٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. የአጋንንትና የሰው ስብስቦች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ከቻላችሁ ውጡ:: በአላህ ስልጣን እንጂ አትወጡም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy34. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرْسَلُ عَلَيْكُمَا شُوَاظٌ مِّن نَّارٍ وَنُحَاسٌ فَلَا تَنتَصِرَانِ

Amharic Translation - Africa Academy35. በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበላባልና ጭስን ይላክባችኋል:: ሁለታችሁም ድል አታደርጉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy36. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ !) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا ٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتْ وَرْدَةً كَٱلدِّهَانِ

Amharic Translation - Africa Academy37. ሰማይ በተሰነጠቀችና እንደጽጌረዳ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ (ጭንቁን ምን አበረታው)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy38. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْـَٔلُ عَن ذَنۢبِهِۦٓ إِنسٌ وَلَا جَآنٌّ

Amharic Translation - Africa Academy39. በዚያ ቀን ሰዉም ጂንም ከሐጢአት አይጠየቅም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy40. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُعْرَفُ ٱلْمُجْرِمُونَ بِسِيمَٰهُمْ فَيُؤْخَذُ بِٱلنَّوَٰصِى وَٱلْأَقْدَامِ

Amharic Translation - Africa Academy41. ከሓዲያን በምልክታቸው ይታወቃሉ:: ከዚያ አናቶቻቸውንና እግሮቻቸውን ይያዛሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy42. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِى يُكَذِّبُ بِهَا ٱلْمُجْرِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. "ይህች ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት" (ይባላሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَطُوفُونَ بَيْنَهَا وَبَيْنَ حَمِيمٍ ءَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy44. በእርሷና በጣም ሞቃት በሆነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy45. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ

Amharic Translation - Africa Academy46. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታዉም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁሉ ሁለት ገነቶች አሉት፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy47. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَوَاتَآ أَفْنَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy48. የቀንዘሎች ባለቤቶች የሆኑ ገነቶች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy49. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِمَا عَيْنَانِ تَجْرِيَانِ

Amharic Translation - Africa Academy50. በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy51. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِمَا مِن كُلِّ فَٰكِهَةٍ زَوْجَانِ

Amharic Translation - Africa Academy52. በሁለቱ ውስጥ ከየፍራፍሬው ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አሉ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy53. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ فُرُشٍۭ بَطَآئِنُهَا مِنْ إِسْتَبْرَقٍ وَجَنَى ٱلْجَنَّتَيْنِ دَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy54. የውስጥ ጉዝጉዛቸው ከወፍራም ሀር በሆኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቸ ሲሆን ይንፈላሰሳሉ፤ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ ለለቃሚ ቅርብ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy55. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِنَّ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرْفِ لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَآنٌّ

Amharic Translation - Africa Academy56. በውስጣቸው ከባሎቻቸው በፊት ሰዉም ጂንም ያልዳሰሳቸው (ያልገሰሳቸው) ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ ብቻ) አሳጣሪዎች ሴቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy57. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَأَنَّهُنَّ ٱلْيَاقُوتُ وَٱلْمَرْجَانُ

Amharic Translation - Africa Academy58. ልክ የያቁትንና የመርጃንን ማዕድናት ይመስላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy59. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ جَزَآءُ ٱلْإِحْسَٰنِ إِلَّا ٱلْإِحْسَٰنُ

Amharic Translation - Africa Academy60. የበጎ ስራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy61. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ

Amharic Translation - Africa Academy62. ከሁለት ገነቶች ሌላም ሁለት ገነቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy63. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُدْهَآمَّتَانِ

Amharic Translation - Africa Academy64. ከልምላሜዎቻቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy65. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِمَا عَيْنَانِ نَضَّاخَتَانِ

Amharic Translation - Africa Academy66. በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy67. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِمَا فَٰكِهَةٌ وَنَخْلٌ وَرُمَّانٌ

Amharic Translation - Africa Academy68. በውስጣቸው ፍራፍሬ ዘንባባና ሩማን አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy69. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهِنَّ خَيْرَٰتٌ حِسَانٌ

Amharic Translation - Africa Academy70. በውስጣቸው ጸባየ መልካሞችና መልከ ውብ ሴቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy71. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حُورٌ مَّقْصُورَٰتٌ فِى ٱلْخِيَامِ

Amharic Translation - Africa Academy72. በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቸቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy73. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَمْ يَطْمِثْهُنَّ إِنسٌ قَبْلَهُمْ وَلَا جَآنٌّ

Amharic Translation - Africa Academy74. ከእነርሱ በፊት ሰዉም ሆነ ጃን አልዳሰሳቸዉም (አልገሰሳቸዉም) ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy75. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ رَفْرَفٍ خُضْرٍ وَعَبْقَرِىٍّ حِسَانٍ

Amharic Translation - Africa Academy76. በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲሆኑ ይቀመጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

Amharic Translation - Africa Academy77. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَبَٰرَكَ ٱسْمُ رَبِّكَ ذِى ٱلْجَلَٰلِ وَٱلْإِكْرَامِ

Amharic Translation - Africa Academy78. የግርማ የመከበር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ላቀ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70