caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Naazi'aat النازعات

46 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 81

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلنَّٰزِعَٰتِ غَرْقًا

Amharic Translation - Africa Academy1. (ነፍስን (ሩህን)) በኃይል መንጫቂዎች በሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلنَّٰشِطَٰتِ نَشْطًا

Amharic Translation - Africa Academy2. በቀስታ መምዘዝን መዛዦች በሆኑትም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّٰبِحَٰتِ سَبْحًا

Amharic Translation - Africa Academy3. መዋኘትንም ዋኚዎች በሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلسَّٰبِقَٰتِ سَبْقًا

Amharic Translation - Africa Academy4. መቅደምንም ቀዳሚዎች በሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْمُدَبِّرَٰتِ أَمْرًا

Amharic Translation - Africa Academy5. ጉዳይንም አስተናባሪዎች በሆኑት መላዕክት እምላለሁ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تَرْجُفُ ٱلرَّاجِفَةُ

Amharic Translation - Africa Academy6. (ይህም የሚሆነው) ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَتْبَعُهَا ٱلرَّادِفَةُ

Amharic Translation - Africa Academy7. ተከታይቱም በምትከተላት ቀን (ትቀሰቀሳላችሁ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلُوبٌ يَوْمَئِذٍ وَاجِفَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَبْصَٰرُهَا خَٰشِعَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَقُولُونَ أَءِنَّا لَمَرْدُودُونَ فِى ٱلْحَافِرَةِ

Amharic Translation - Africa Academy10. «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ሁኔታ ተመላሾች ነን እንዴ?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمًا نَّخِرَةً

Amharic Translation - Africa Academy11. የበሰበሱ አጥንቶች በሆንን ጊዜ እንደገና እንቀሰቀሳለን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ تِلْكَ إِذًا كَرَّةٌ خَاسِرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. «እንዲያማ ከሆነ ያች የኪሳራ መመለስ ናታ!» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّمَا هِىَ زَجْرَةٌ وَٰحِدَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy13. እርሷን (እውን የምታደርጋት) አንዲት ጩኸት ብቻ ናት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا هُم بِٱلسَّاهِرَةِ

Amharic Translation - Africa Academy14. ወዲያውኑ በንቃት ላይ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ መጣልህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ نَادَىٰهُ رَبُّهُۥ بِٱلْوَادِ ٱلْمُقَدَّسِ طُوًى

Amharic Translation - Africa Academy16. ጌታው በተቀደሰው ጡዋ ሸለቆ በጠራው ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy17. ወደ ፈርዖን ሂድ፤ ወሰን አልፏልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقُلْ هَل لَّكَ إِلَىٰٓ أَن تَزَكَّىٰ

Amharic Translation - Africa Academy18. (እንዲህም) በለው: «እራስህን ለማጥራት ታስባለህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَهْدِيَكَ إِلَىٰ رَبِّكَ فَتَخْشَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy19. ጌታህንም ትፈራ ዘንድ መንገዱን ልመራህ፤ (ታስባለህን?)»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَرَىٰهُ ٱلْـَٔايَةَ ٱلْكُبْرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy20. (ሙሳ ለፈርዖን) ታላቁንም ተዐምር አሳየው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَذَّبَ وَعَصَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy21. አስተባበለም፤ አመጸም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَدْبَرَ يَسْعَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy22. ከዚያ ለመጥፋት የሚተጋ ሆኖ ዞረ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَحَشَرَ فَنَادَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy23. (ህዝቡን) ሰበሰበም ተጣራም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَالَ أَنَا۠ رَبُّكُمُ ٱلْأَعْلَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy24. እኔ «ታላቁ ጌታችሁ ነኝ» አለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخَذَهُ ٱللَّهُ نَكَالَ ٱلْـَٔاخِرَةِ وَٱلْأُولَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy25. አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ ቃል ቅጣት ያዘው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّمَن يَخْشَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy26. በዚህ ውስጥ አላህን ለሚፈሩ በእርግጥ ማስጠንቀቂያ አለበት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ ٱلسَّمَآءُ بَنَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy27. በአፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَفَعَ سَمْكَهَا فَسَوَّىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy28. ከፍታዋን አጓነ አስተካከላትም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَغْطَشَ لَيْلَهَا وَأَخْرَجَ ضُحَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy29. ሌሊቷንም ሸፈነ፤ ቀኗንም ግልጽ አደረገ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَىٰهَآ

Amharic Translation - Africa Academy30. ምድርንም ከዚያ በኋላ ዘረጋት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَخْرَجَ مِنْهَا مَآءَهَا وَمَرْعَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy31. ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْجِبَالَ أَرْسَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy32. ጋራዎችንም አደላደላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَتَٰعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَٰمِكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy33. ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጣቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይሄን አደረገ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا جَآءَتِ ٱلطَّآمَّةُ ٱلْكُبْرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy34. ታላቂቱም መዓት በመጣች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يَتَذَكَّرُ ٱلْإِنسَٰنُ مَا سَعَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy35. ሰው ሁሉ የሰራውን የሚያስታውስበት ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبُرِّزَتِ ٱلْجَحِيمُ لِمَن يَرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy36. ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا مَن طَغَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy37. የካደ ሰውማ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاثَرَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا

Amharic Translation - Africa Academy38. ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّ ٱلْجَحِيمَ هِىَ ٱلْمَأْوَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy39. በእርግጥ መኖሪያው ጀሀነም ናት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ وَنَهَى ٱلنَّفْسَ عَنِ ٱلْهَوَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy40. በጌታው ፊት መቆምን የፈራና ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለማ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّ ٱلْجَنَّةَ هِىَ ٱلْمَأْوَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy41. በእርግጥ መኖሪያው ገነት ናት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy42. ስለሰዓቲቱም መነሻዋ መቼ እንደሆነ ይጠይቁሃል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيمَ أَنتَ مِن ذِكْرَىٰهَآ

Amharic Translation - Africa Academy43. (ለመሆኑ አንተ ስለዚያች እለት) በመወሳቷ ምን ላይ አለህበትና?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَىٰ رَبِّكَ مُنتَهَىٰهَآ

Amharic Translation - Africa Academy44. የእርሷ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخْشَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy45. አንተ ያለብህ ለሚፈራት ሰው ሁሉ ስለ እርሷ (ከወዲሁ) ማስጠንቀቅ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَهَا لَمْ يَلْبَثُوٓا۟ إِلَّا عَشِيَّةً أَوْ ضُحَىٰهَا

Amharic Translation - Africa Academy46. እነርሱ የሚያይዋት ቀን የአንዲትን ቀን ምሽት ወይም ረፋዷን እንጂ ያልቆዩ ይመስላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70