caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Abasa عبس

42 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 24

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَن جَآءَهُ ٱلْأَعْمَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy2. ዓይነስውሩ ወደ እርሱ ስለመጣ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምን ያሳውቅሃል? ምን አልባትም (ይህ አይነስውር ሰው ካንተ በሚሰማው ምክር ከኃጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكْرَىٰٓ

Amharic Translation - Africa Academy4. ወይም ሊገሰጽና ግሳጼይቱም ልትጠቅመው ይከጀላል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّا مَنِ ٱسْتَغْنَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy5. ያ! ከአላህ የተብቃቃውን ሰውማ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ

Amharic Translation - Africa Academy6. አንተ ለእርሱ ትዘጋጃለህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا عَلَيْكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ

Amharic Translation - Africa Academy7. ባይጥራራ (ባያምን)፤ ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا مَن جَآءَكَ يَسْعَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy8. ያ! እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ يَخْشَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy9. እርሱ አላህን የሚፈራ ሲሆን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنتَ عَنْهُ تَلَهَّىٰ

Amharic Translation - Africa Academy10. አንተ ከእርሱ ትዘናጋለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّآ إِنَّهَا تَذْكِرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy11. ተከልከል፤ (ቁርኣን) ማስገንዘቢያ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy12. የፈለገ ሰው ሁሉ (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى صُحُفٍ مُّكَرَّمَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy13. በተከበሩት ጹሑፎች ውስጥ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّرْفُوعَةٍ مُّطَهَّرَةٍۭ

Amharic Translation - Africa Academy14. ከፍ በተደረገች፤ ንጹህም በተደረገች (ጹሑፍ ውስጥ ነው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِأَيْدِى سَفَرَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. በጸሐፊዎች መላዕክት እጆች (ንጹህ የተደረገ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كِرَامٍۭ بَرَرَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy16. የተከበሩና ታዛዦች በሆኑት ጸሐፊዎች (እጆች)፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُتِلَ ٱلْإِنسَٰنُ مَآ أَكْفَرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy17. ሰው ተረገመ። ምን ከሓዲ አደረገው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِنْ أَىِّ شَىْءٍ خَلَقَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy18. (ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُۥ فَقَدَّرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy19. (አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ ٱلسَّبِيلَ يَسَّرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy20. ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَمَاتَهُۥ فَأَقْبَرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy21. ከዚያም ገደለው:: እንዲቀበርም አደረገው፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِذَا شَآءَ أَنشَرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy22. ከዚያ ማንሳቱን በፈለገ ጊዜ ያስነሳዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا لَمَّا يَقْضِ مَآ أَمَرَهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy23. በእውነት ያንን ጌታው ያዘዘውን ገና አልፈጸመም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلْيَنظُرِ ٱلْإِنسَٰنُ إِلَىٰ طَعَامِهِۦٓ

Amharic Translation - Africa Academy24. ሰው ወደ ምግቡ ይመልከት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَنَّا صَبَبْنَا ٱلْمَآءَ صَبًّا

Amharic Translation - Africa Academy25. እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ شَقَقْنَا ٱلْأَرْضَ شَقًّا

Amharic Translation - Africa Academy26. ከዚያ ምድርን በደካማ ቡቃያ መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنۢبَتْنَا فِيهَا حَبًّا

Amharic Translation - Africa Academy27. በውስጧም እህልን ያበቀልን

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعِنَبًا وَقَضْبًا

Amharic Translation - Africa Academy28. ወይንም እርጥብ ሳርንም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَزَيْتُونًا وَنَخْلًا

Amharic Translation - Africa Academy29. የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحَدَآئِقَ غُلْبًا

Amharic Translation - Africa Academy30. ጭፍቆች አትክልቶችንም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفَٰكِهَةً وَأَبًّا

Amharic Translation - Africa Academy31. ፍራፍሬንና፤ ገለባንም (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّتَٰعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَٰمِكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy32. ለእናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا جَآءَتِ ٱلصَّآخَّةُ

Amharic Translation - Africa Academy33. አደንቋሪይቱ (መከራ) በመጣች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يَفِرُّ ٱلْمَرْءُ مِنْ أَخِيهِ

Amharic Translation - Africa Academy34. ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُمِّهِۦ وَأَبِيهِ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከእናቱም፤ ከአባቱም፤ (በሚሸሽበት ቀን)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَصَٰحِبَتِهِۦ وَبَنِيهِ

Amharic Translation - Africa Academy36. ከሚስቱና ከልጁም፤ (በሚሸሽበት ቀን)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِكُلِّ ٱمْرِئٍ مِّنْهُمْ يَوْمَئِذٍ شَأْنٌ يُغْنِيهِ

Amharic Translation - Africa Academy37. ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን ከሌላው የሚያብቃቃው ሁኔታ አለው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُّسْفِرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy38. ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ضَاحِكَةٌ مُّسْتَبْشِرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy39. ሳቂዎችና ተደሳቾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትብያ አለባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy41. ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْكَفَرَةُ ٱلْفَجَرَةُ

Amharic Translation - Africa Academy42. እነዚያ እነርሱ በአላህ ከሓዲያን እና በትዕዛዙ ላይ አመጸኞቹ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70