caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Adh-Dhaariyat الذاريات

60 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 67

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلذَّٰرِيَٰتِ ذَرْوًا

Amharic Translation - Africa Academy1. መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْحَٰمِلَٰتِ وِقْرًا

Amharic Translation - Africa Academy2. ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْجَٰرِيَٰتِ يُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy3. ገር መንሻለልን ተንሻላዩች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْمُقَسِّمَٰتِ أَمْرًا

Amharic Translation - Africa Academy4. ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٌ

Amharic Translation - Africa Academy5. የምተቀጠሩት ትንሳኤ እውነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ ٱلدِّينَ لَوَٰقِعٌ

Amharic Translation - Africa Academy6. (እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلْحُبُكِ

Amharic Translation - Africa Academy7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّكُمْ لَفِى قَوْلٍ مُّخْتَلِفٍ

Amharic Translation - Africa Academy8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُؤْفَكُ عَنْهُ مَنْ أُفِكَ

Amharic Translation - Africa Academy9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُتِلَ ٱلْخَرَّٰصُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ هُمْ فِى غَمْرَةٍ سَاهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْـَٔلُونَ أَيَّانَ يَوْمُ ٱلدِّينِ

Amharic Translation - Africa Academy12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ هُمْ عَلَى ٱلنَّارِ يُفْتَنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذُوقُوا۟ فِتْنَتَكُمْ هَٰذَا ٱلَّذِى كُنتُم بِهِۦ تَسْتَعْجِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُتَّقِينَ فِى جَنَّٰتٍ وَعُيُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَاخِذِينَ مَآ ءَاتَىٰهُمْ رَبُّهُمْ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَبْلَ ذَٰلِكَ مُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَانُوا۟ قَلِيلًا مِّنَ ٱلَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبِٱلْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِىٓ أَمْوَٰلِهِمْ حَقٌّ لِّلسَّآئِلِ وَٱلْمَحْرُومِ

Amharic Translation - Africa Academy19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى ٱلْأَرْضِ ءَايَٰتٌ لِّلْمُوقِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِىٓ أَنفُسِكُمْ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى ٱلسَّمَآءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَرَبِّ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ إِنَّهُۥ لَحَقٌّ مِّثْلَ مَآ أَنَّكُمْ تَنطِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَٰهِيمَ ٱلْمُكْرَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ دَخَلُوا۟ عَلَيْهِ فَقَالُوا۟ سَلَٰمًا قَالَ سَلَٰمٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَرَاغَ إِلَىٰٓ أَهْلِهِۦ فَجَآءَ بِعِجْلٍ سَمِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَرَّبَهُۥٓ إِلَيْهِمْ قَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً قَالُوا۟ لَا تَخَفْ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَقْبَلَتِ ٱمْرَأَتُهُۥ فِى صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْحَكِيمُ ٱلْعَلِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ فَمَا خَطْبُكُمْ أَيُّهَا ٱلْمُرْسَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy31. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ إِنَّآ أُرْسِلْنَآ إِلَىٰ قَوْمٍ مُّجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy32. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኖች ህዝቦች ተልከናል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِنُرْسِلَ عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن طِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. «በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ لِلْمُسْرِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy34. «በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ በየስማቸው ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخْرَجْنَا مَن كَانَ فِيهَا مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy35. ከምዕመናም በእርሷ በከተማቸው ውስጥ የነበሩትን አወጣን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا وَجَدْنَا فِيهَا غَيْرَ بَيْتٍ مِّنَ ٱلْمُسْلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَكْنَا فِيهَآ ءَايَةً لِّلَّذِينَ يَخَافُونَ ٱلْعَذَابَ ٱلْأَلِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy37. በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى مُوسَىٰٓ إِذْ أَرْسَلْنَٰهُ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ بِسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy38. በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَوَلَّىٰ بِرُكْنِهِۦ وَقَالَ سَٰحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ

Amharic Translation - Africa Academy39. ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም ከእምነት ዞረ:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخَذْنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذْنَٰهُمْ فِى ٱلْيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy40. እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى عَادٍ إِذْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلرِّيحَ ٱلْعَقِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy41. በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا تَذَرُ مِن شَىْءٍ أَتَتْ عَلَيْهِ إِلَّا جَعَلَتْهُ كَٱلرَّمِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy42. በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥነት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى ثَمُودَ إِذْ قِيلَ لَهُمْ تَمَتَّعُوا۟ حَتَّىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy43. በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَعَتَوْا۟ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِمْ فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَهُمْ يَنظُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. ከጌታቸው ትዕዘዝም ኮሩ:: እነርሱም እያዩ ጩኸቷ ያዘቻቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا ٱسْتَطَٰعُوا۟ مِن قِيَامٍ وَمَا كَانُوا۟ مُنتَصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy45. መቆምንም አልቻሉም:: እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَوْمَ نُوحٍ مِّن قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا فَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. የኑህንም ህዝቦች (ከዚህ በፊት አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّمَآءَ بَنَيْنَٰهَا بِأَيْي۟دٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. ሰማይንም በሀይል ገነባናት:: እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْأَرْضَ فَرَشْنَٰهَا فَنِعْمَ ٱلْمَٰهِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَفِرُّوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ إِنِّى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy50. ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَجْعَلُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ إِنِّى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy51. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላኩ:: ግልጽ አስፈራሪ ነኝና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ مَآ أَتَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُوا۟ سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ

Amharic Translation - Africa Academy52. ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَتَوَاصَوْا۟ بِهِۦ بَلْ هُمْ قَوْمٌ طَاغُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَوَلَّ عَنْهُمْ فَمَآ أَنتَ بِمَلُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَذَكِّرْ فَإِنَّ ٱلذِّكْرَىٰ تَنفَعُ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا خَلَقْتُ ٱلْجِنَّ وَٱلْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

Amharic Translation - Africa Academy56. ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَآ أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ

Amharic Translation - Africa Academy57. ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلرَّزَّاقُ ذُو ٱلْقُوَّةِ ٱلْمَتِينُ

Amharic Translation - Africa Academy58. አላህ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ ذَنُوبًا مِّثْلَ ذَنُوبِ أَصْحَٰبِهِمْ فَلَا يَسْتَعْجِلُونِ

Amharic Translation - Africa Academy59. ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው:: ስለዚህ አያስቸኩሉኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن يَوْمِهِمُ ٱلَّذِى يُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዩላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70