caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Burooj البروج

22 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 27

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلْبُرُوجِ

Amharic Translation - Africa Academy1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْيَوْمِ ٱلْمَوْعُودِ

Amharic Translation - Africa Academy2. በተቀጠረዉም ቀን፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ

Amharic Translation - Africa Academy3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُتِلَ أَصْحَٰبُ ٱلْأُخْدُودِ

Amharic Translation - Africa Academy4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلْوَقُودِ

Amharic Translation - Africa Academy5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ

Amharic Translation - Africa Academy6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِٱلْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ

Amharic Translation - Africa Academy7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا نَقَمُوا۟ مِنْهُمْ إِلَّآ أَن يُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَمِيدِ

Amharic Translation - Africa Academy8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ ጌታ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِى لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُوا۟ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا۟ فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ ٱلْحَرِيقِ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው:: ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمْ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْكَبِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው:: ይህ ታላቅ ስኬት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ

Amharic Translation - Africa Academy13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلْوَدُودُ

Amharic Translation - Africa Academy14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذُو ٱلْعَرْشِ ٱلْمَجِيدُ

Amharic Translation - Africa Academy15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ

Amharic Translation - Africa Academy16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلْجُنُودِ

Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ

Amharic Translation - Africa Academy18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى تَكْذِيبٍ

Amharic Translation - Africa Academy19. በእውነት እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطٌۢ

Amharic Translation - Africa Academy20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ هُوَ قُرْءَانٌ مَّجِيدٌ

Amharic Translation - Africa Academy21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى لَوْحٍ مَّحْفُوظٍۭ

Amharic Translation - Africa Academy22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70