caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Insaan الانسان

31 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 98

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ هَلْ أَتَىٰ عَلَى ٱلْإِنسَٰنِ حِينٌ مِّنَ ٱلدَّهْرِ لَمْ يَكُن شَيْـًٔا مَّذْكُورًا

Amharic Translation - Africa Academy1. በሰው ላይ የሚታወስ ነገር (እንኳ) ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ አላለፈም ነበርን? (በእርግጥ አልፏል)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَٰهُ سَمِيعًۢا بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy2. እኛ ሰውን (በሕግጋት ግዳጅ) የምንሞክረው ስንሆን ከወንድና ከሴት ፈሳሽ ቅልቅሎች ከሆነች የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው:: ሰሚና ተመልካችም አደረግነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا هَدَيْنَٰهُ ٱلسَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy3. እኛ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲሆን መንገዱን መራነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَعْتَدْنَا لِلْكَٰفِرِينَ سَلَٰسِلَا۟ وَأَغْلَٰلًا وَسَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy4. እኛ ለከሓዲያን ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም (አዘጋጅተናል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا

Amharic Translation - Africa Academy5. እነዚያ (ትክክለኛ) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا عِبَادُ ٱللَّهِ يُفَجِّرُونَهَا تَفْجِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy6. ከእርሷ እነዚያ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት ና ወደ ፈለጉበት ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከሆነች የጠጅ ምንጭ (ይጠጣሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُوفُونَ بِٱلنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْمًا كَانَ شَرُّهُۥ مُسْتَطِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy7. (ዛሬ በዚህ ዓለም እያሉ) በስለታቸው ይሞላሉ:: መከራው ተሰራጪ የሆነንም ቀን ይፈራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُطْعِمُونَ ٱلطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ مِسْكِينًا وَيَتِيمًا وَأَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy8. ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፤ ለየቲምና ለምርኮኛ ያበላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ ٱللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَآءً وَلَا شُكُورًا

Amharic Translation - Africa Academy9. «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው:: ከናንተ ክፍያንም ሆነ ማመስገንን አንፈልግም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy10. እኛ ያንን (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» (ይላሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَقَىٰهُمُ ٱللَّهُ شَرَّ ذَٰلِكَ ٱلْيَوْمِ وَلَقَّىٰهُمْ نَضْرَةً وَسُرُورًا

Amharic Translation - Africa Academy11. አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው። (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَزَىٰهُم بِمَا صَبَرُوا۟ جَنَّةً وَحَرِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy12. በመታገሳቸዉም (ምክንያት) ገነትንና የሀር ልብስን መነዳቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ لَا يَرَوْنَ فِيهَا شَمْسًا وَلَا زَمْهَرِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy13. በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች፤ በውስጧ የጸሀይን ሐሩርንም ሆነ ብርድንም የማያዩ ሲሆኑ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَانِيَةً عَلَيْهِمْ ظِلَٰلُهَا وَذُلِّلَتْ قُطُوفُهَا تَذْلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy14. ዛፎቿም ለእነርሱ የቀረበች፤ ፍራፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መገራትን የተገራች ስትሆን ገነትን መነዳቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُطَافُ عَلَيْهِم بِـَٔانِيَةٍ مِّن فِضَّةٍ وَأَكْوَابٍ كَانَتْ قَوَارِيرَا۠

Amharic Translation - Africa Academy15. በእነርሱም ላይ ከብር በተሰሩ ዕቃዎች (ሳህኖች)፤ ብርጭቆዎች እና በኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَوَارِيرَا۟ مِن فِضَّةٍ قَدَّرُوهَا تَقْدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy16. መለካትን የለኳቸው በሆኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُسْقَوْنَ فِيهَا كَأْسًا كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy17. በእርሷም መበረዣዋ ዝንጂብል የሆነች ወይን ጠጅ ይጥጠጣሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَيْنًا فِيهَا تُسَمَّىٰ سَلْسَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy18. በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَٰنٌ مُّخَلَّدُونَ إِذَا رَأَيْتَهُمْ حَسِبْتَهُمْ لُؤْلُؤًا مَّنثُورًا

Amharic Translation - Africa Academy19. በእነርሱም ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ:: ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَأَيْتَ ثَمَّ رَأَيْتَ نَعِيمًا وَمُلْكًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy20. እዚያንም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግስናን ታያለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَٰلِيَهُمْ ثِيَابُ سُندُسٍ خُضْرٌ وَإِسْتَبْرَقٌ وَحُلُّوٓا۟ أَسَاوِرَ مِن فِضَّةٍ وَسَقَىٰهُمْ رَبُّهُمْ شَرَابًا طَهُورًا

Amharic Translation - Africa Academy21. አረንጓዴዎች የሆኑ ቀጭን ሀር ልብሶችና ወፍራም ሀርም በላያቸው ላይ አለ። ከብር የሆኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ:: ጌታቸዉም (ከራሱ አልፎ) ሌላን አጥሪ የሆነን መጠጥ ያጠጣቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذَا كَانَ لَكُمْ جَزَآءً وَكَانَ سَعْيُكُم مَّشْكُورًا

Amharic Translation - Africa Academy22. «ይህ ለእናንተ ዋጋ ሆነ:: ስራችሁም ምስጉን ሆነ» ይባላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ ٱلْقُرْءَانَ تَنزِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ (ይህንን) ቁርኣን ባንተ ላይ ማውረድን አወረድነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تُطِعْ مِنْهُمْ ءَاثِمًا أَوْ كَفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy24. ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: ከእነርሱም መካከል ኃጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرِ ٱسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy25. የጌታህን ስም በጠዋትና ከቀትር በኋላ አውሳ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَٱسْجُدْ لَهُۥ وَسَبِّحْهُ لَيْلًا طَوِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy26 ከሌሊቱም ለእርሱ ብቻ ስገድ፤ በረዢም ሌሊትም አወድሰው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ يُحِبُّونَ ٱلْعَاجِلَةَ وَيَذَرُونَ وَرَآءَهُمْ يَوْمًا ثَقِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያ ይህችን ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ። ከባድና (አስቸጋሪ) ቀንም በስተፊታቸው ሆኖ ችላ ይላሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَّحْنُ خَلَقْنَٰهُمْ وَشَدَدْنَآ أَسْرَهُمْ وَإِذَا شِئْنَا بَدَّلْنَآ أَمْثَٰلَهُمْ تَبْدِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy28. እኛ ፈጠርናቸው:: የአካሎቻቸዉንም መለያያቸውን አጠነከርን:: በፈለግን ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذِهِۦ تَذْكِرَةٌ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy29. ይህ መገሰጫ ነው:: የፈለገ ሰውም ወደ ጌታው መንገድ ይይዛል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy30. አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፤ አላህ አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُدْخِلُ مَن يَشَآءُ فِى رَحْمَتِهِۦ وَٱلظَّٰلِمِينَ أَعَدَّ لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًۢا

Amharic Translation - Africa Academy31. (አላህ) የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዩችንም (ዝቶባቸዋል) ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70