إِنَّ رَبَّكَ يَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدْنَىٰ مِن ثُلُثَىِ ٱلَّيْلِ وَنِصْفَهُۥ وَثُلُثَهُۥ وَطَآئِفَةٌ مِّنَ ٱلَّذِينَ مَعَكَ وَٱللَّهُ يُقَدِّرُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ عَلِمَ أَن لَّن تُحْصُوهُ فَتَابَ عَلَيْكُمْ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرْضَىٰ وَءَاخَرُونَ يَضْرِبُونَ فِى ٱلْأَرْضِ يَبْتَغُونَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ وَءَاخَرُونَ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَقْرِضُوا۟ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا وَمَا تُقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيْرًا وَأَعْظَمَ أَجْرًا وَٱسْتَغْفِرُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል:: (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል:: አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል:: ሌሊቱን በሙሉ የማትቆሙት መሆናችሁን አወቀ:: እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ:: ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ:: ከናንተ ውስጥ ሌሎችም በሽተኞች ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ ሌሎችም፤ በአላህ መንገድ ሃይማኖት ላይ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ:: አቃለለላቸዉም ከቁርኣን የቻላችሁትን አንብቡ:: ሶላትንም ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ:: ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህን ምህረት ለምኑት:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንተ ከሌሊቱ ከሶስት ሁለት እጅ ያነሰን ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መኾንህን ጌታህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ከእነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች (የሚቆሙ መኾናቸውን ያውቃል)፡፡ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይለክካል፡፡ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተ ላይም (ወደ ማቃለል) ተመለሰላችሁ፡፡ ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፡፡ ከእናንተ ውስጥ በሽተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፡፡ (አቃለለላቸውም)፡፡ ከእርሱም የተቻለችሁን አንብቡ፡፡ ሶላትንም ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፡፡ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡