ሱረቱ Al-Jinn الجن
28 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 40
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ قُلْ أُوحِىَ إِلَىَّ أَنَّهُ ٱسْتَمَعَ نَفَرٌ مِّنَ ٱلْجِنِّ فَقَالُوٓا۟ إِنَّا سَمِعْنَا قُرْءَانًا عَجَبًا
Amharic Translation - Africa Academy1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን አዳመጠው እንዲህ ማለታቸው ተወረደልኝ በል: «እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَهْدِىٓ إِلَى ٱلرُّشْدِ فَـَٔامَنَّا بِهِۦ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَآ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy2. «ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርኣን ሰማን) በእርሱም አመንን:: በጌታችን አንድንም አናጋራም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ تَعَٰلَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا ٱتَّخَذَ صَٰحِبَةً وَلَا وَلَدًا
Amharic Translation - Africa Academy3. «እነሆ የጌታችን ክብር ላቀ:: ሚስትንም ልጅንም አልያዘም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ كَانَ يَقُولُ سَفِيهُنَا عَلَى ٱللَّهِ شَطَطًا
Amharic Translation - Africa Academy4. «እነሆ ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን ውሸት ይናገር ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا ظَنَنَّآ أَن لَّن تَقُولَ ٱلْإِنسُ وَٱلْجِنُّ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا
Amharic Translation - Africa Academy5. «እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን ቃል አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን» አሉ በማለት ወደእኔ ተወረደ በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ ٱلْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ ٱلْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا
Amharic Translation - Africa Academy6. እነሆ ከሰዎች የሆኑ ወንዶች ከአጋንንት በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር። ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُمْ ظَنُّوا۟ كَمَا ظَنَنتُمْ أَن لَّن يَبْعَثَ ٱللَّهُ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ እነርሱም ጠረጠሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا لَمَسْنَا ٱلسَّمَآءَ فَوَجَدْنَٰهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا
Amharic Translation - Africa Academy8. እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا كُنَّا نَقْعُدُ مِنْهَا مَقَٰعِدَ لِلسَّمْعِ فَمَن يَسْتَمِعِ ٱلْـَٔانَ يَجِدْ لَهُۥ شِهَابًا رَّصَدًا
Amharic Translation - Africa Academy9. እኛም ከእርሷ ወሬን ለማዳመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበር:: አሁን (ግን) የሚያዳምጥ (ሁሉ) ተጠባባቂ የእሳት ችቦ ያገኘዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا لَا نَدْرِىٓ أَشَرٌّ أُرِيدَ بِمَن فِى ٱلْأَرْضِ أَمْ أَرَادَ بِهِمْ رَبُّهُمْ رَشَدًا
Amharic Translation - Africa Academy10. እኛም በምድር ውስጥ ባሉት ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ (በኩል) ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا مِنَّا ٱلصَّٰلِحُونَ وَمِنَّا دُونَ ذَٰلِكَ كُنَّا طَرَآئِقَ قِدَدًا
Amharic Translation - Africa Academy11. ከእኛም ውስጥ ደጋጎች አሉ:: ከእኛም ውስጥ ከዚህ ሌላ የሆኑ አሉ:: የተለያዩ መንገዶች ባለቤቶች ነበርን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا ظَنَنَّآ أَن لَّن نُّعْجِزَ ٱللَّهَ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَن نُّعْجِزَهُۥ هَرَبًا
Amharic Translation - Africa Academy12. እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መሆናችንን አረጋገጥን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا لَمَّا سَمِعْنَا ٱلْهُدَىٰٓ ءَامَنَّا بِهِۦ فَمَن يُؤْمِنۢ بِرَبِّهِۦ فَلَا يَخَافُ بَخْسًا وَلَا رَهَقًا
Amharic Translation - Africa Academy13. እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በእርሱ አመንን:: ያ! በጌታው የሚያምን ሰው ሁሉ መጎደልንም ሆነ መጨመርን አይፈራም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّا مِنَّا ٱلْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا ٱلْقَٰسِطُونَ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ تَحَرَّوْا۟ رَشَدًا
Amharic Translation - Africa Academy14. ከእኛም ውስጥ ሙስሊሞች አሉ:: ከእኛም ውስጥ በዳዩች አሉ:: እነዚያ የሰለሙ ሰዎች ቅንን መንገድ መረጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَمَّا ٱلْقَٰسِطُونَ فَكَانُوا۟ لِجَهَنَّمَ حَطَبًا
Amharic Translation - Africa Academy15. እነዚያ በዳዩችማ ለገሀነም ማገዶ ሆኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَلَّوِ ٱسْتَقَٰمُوا۟ عَلَى ٱلطَّرِيقَةِ لَأَسْقَيْنَٰهُم مَّآءً غَدَقًا
Amharic Translation - Africa Academy16. (ሰዎች ሁሉ በአላህ) በመንገድ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናብን ባጠጣናቸው ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّنَفْتِنَهُمْ فِيهِ وَمَن يُعْرِضْ عَن ذِكْرِ رَبِّهِۦ يَسْلُكْهُ عَذَابًا صَعَدًا
Amharic Translation - Africa Academy17. በእርሱ ልንፈትናቸው (ባጠጣናቸው ነበር)። ያ ጌታውን ከማስታወስ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪ ቅጣት ውስጥ ያስገባዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy18. መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው:: እናም በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትን ተወረደልኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّهُۥ لَمَّا قَامَ عَبْدُ ٱللَّهِ يَدْعُوهُ كَادُوا۟ يَكُونُونَ عَلَيْهِ لِبَدًا
Amharic Translation - Africa Academy19. እነሆ የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ) አላህን የሚጠራው ሆኖ በተነሳ ጊዜ ጋኒኖቹ በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊሆኑ ቀረቡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُوا۟ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِهِۦٓ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ የማመልከው ጌታየን ብቻ ነው:: በእርሱ አንድንም አላጋራም» በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنِّى لَآ أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرًّا وَلَا رَشَدًا
Amharic Translation - Africa Academy21. «እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ሆነ ማቅናትን አልችልም» በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنِّى لَن يُجِيرَنِى مِنَ ٱللَّهِ أَحَدٌ وَلَنْ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلْتَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy22. «እኔን ከአላህ ቅጣት አንድም (አካል) አያድነኝም:: ከእርሱ ሌላ መጠጊያም አላገኝም» በል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا بَلَٰغًا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِسَٰلَٰتِهِۦ وَمَن يَعْصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا
Amharic Translation - Africa Academy23. ከአላህ የሆኑ መልዕክቶችን ከማድረስ በስተቀር አልችልም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚያምጽ ሁሉ ለእርሱ የገሀነም እሳት አለው:: በውስጧም ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حَتَّىٰٓ إِذَا رَأَوْا۟ مَا يُوعَدُونَ فَسَيَعْلَمُونَ مَنْ أَضْعَفُ نَاصِرًا وَأَقَلُّ عَدَدًا
Amharic Translation - Africa Academy24. የሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳተ ደካማ ቁጥሩም አነስተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ إِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ مَّا تُوعَدُونَ أَمْ يَجْعَلُ لَهُۥ رَبِّىٓ أَمَدًا
Amharic Translation - Africa Academy25. «ያ! የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት እሩቅ መሆኑን አላውቅም።» በላቸው
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy26. እርሱም እሩቁን ሚስጢር አዋቂ ነው::በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُۥ يَسْلُكُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِۦ رَصَدًا
Amharic Translation - Africa Academy27. (በሚስጢሩም ላይ) ከመልዕክተኛው ለወደደው ቢሆን እንጂ (ለሌላ አንድንም አያሳውቅም):: አይገልጽም:: ለእርሱም ከበስተፊቱም ከበስተኋላዉም ጠባቂዎቸን ያደርግለታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا۟ رِسَٰلَٰتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَىْءٍ عَدَدًۢا
Amharic Translation - Africa Academy28. ከእነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀት የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን የጌታቸውን መልዕክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ (ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→