caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Waaqia الواقعة

96 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 46

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا وَقَعَتِ ٱلْوَاقِعَةُ

Amharic Translation - Africa Academy1. ተጨባጪቱ (ቂያማ) እውን በሆነች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَيْسَ لِوَقْعَتِهَا كَاذِبَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy2. (ቂያማ) እውን ለመሆኗ አንዲትም አስተባባይ ነፍስ የለችም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَافِضَةٌ رَّافِعَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy3. እርሷ (ገሚሱን) ዝቅ አድራጊና (ገሚሱን) ደግሞ ከፍ አድራጊ ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذَا رُجَّتِ ٱلْأَرْضُ رَجًّا

Amharic Translation - Africa Academy4. ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبُسَّتِ ٱلْجِبَالُ بَسًّا

Amharic Translation - Africa Academy5. ተራራዎች (እንደተፈጨ ዱቄት) መፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَانَتْ هَبَآءً مُّنۢبَثًّا

Amharic Translation - Africa Academy6. የተበተነ ብናኝ በሆኑም ጊዜ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُنتُمْ أَزْوَٰجًا ثَلَٰثَةً

Amharic Translation - Africa Academy7. እናንተ (ሰዎች) ሶስት ዓይነቶችም በሆናችሁ ጊዜ (ገሚሱን ዝቅ እና ገሚሱን ከፍ ታደርጋለች)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَصْحَٰبُ ٱلْمَيْمَنَةِ مَآ أَصْحَٰبُ ٱلْمَيْمَنَةِ

Amharic Translation - Africa Academy8. እናም በዚያ ቀን የቀኝ ጓዶች ለመሆን የበቁ ሁሉ ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَصْحَٰبُ ٱلْمَشْـَٔمَةِ مَآ أَصْحَٰبُ ٱلْمَشْـَٔمَةِ

Amharic Translation - Africa Academy9. የግራ ጓዶች ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلسَّٰبِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ (ለበጎ ስራ) ቀዳሚዎች የሆኑ ሁሉ (ለገነትም) ቀዳሚዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلْمُقَرَّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያ (በአላህ ዘንድም) ባለሟሎች ናቸው

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy12. በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُلَّةٌ مِّنَ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. (የዚህ እድል ባለ ቤቶች) ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَلِيلٌ مِّنَ ٱلْـَٔاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ከኋለኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَىٰ سُرُرٍ مَّوْضُونَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy15. በተሸሞኑ አልጋዎች ላይ ይሆናሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّتَّكِـِٔينَ عَلَيْهَا مُتَقَٰبِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲሆኑ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَٰنٌ مُّخَلَّدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. እነርሱን (ለማገለገል) በእነርሱ ዙሪያ ሁልጊዜ የማያረጁ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِأَكْوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy18. ከ(ጠጅ) ምንጭ በብርጨቆዎች፣ በኩስኩስቶችና (እብሪቆች) በጽዋም በእነርሱ ዙሪያ እንዲዞሩ ይደረጋሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. ከእርሷ የራስ ምታት እንኳን አያገኛቸዉም:: አይሰክሩምም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفَٰكِهَةٍ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. ከእሸቶች ከሚመርጡት ዓይነት

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَحْمِ طَيْرٍ مِّمَّا يَشْتَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. ከሚፈልጉት የበራሪ ስጋ ይዘው ይዞሩላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحُورٌ عِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy22. ዓይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆ ሴቶችም አሏቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَأَمْثَٰلِ ٱللُّؤْلُؤِ ٱلْمَكْنُونِ

Amharic Translation - Africa Academy23. ልክ እንደተሸፈነ ሉል የሚመስሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ለዚያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ ይህንን አደረግንላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا تَأْثِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy25. በውስጧ ውድቅ ንግግርንና መወንጀልንም አይሰሙም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا قِيلًا سَلَٰمًا سَلَٰمًا

Amharic Translation - Africa Academy26. ሰላም ሰላም መባባልን ግን ይሰማሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَصْحَٰبُ ٱلْيَمِينِ مَآ أَصْحَٰبُ ٱلْيَمِينِ

Amharic Translation - Africa Academy27. የቀኝ ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى سِدْرٍ مَّخْضُودٍ

Amharic Translation - Africa Academy28. በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَطَلْحٍ مَّنضُودٍ

Amharic Translation - Africa Academy29. ፍሬው በተነባበረ ሙዝ ዛፍም ውስጥ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَظِلٍّ مَّمْدُودٍ

Amharic Translation - Africa Academy30. በተዘረጋ ጥላ ስርም ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآءٍ مَّسْكُوبٍ

Amharic Translation - Africa Academy31. በሚንቧቡ ውሃ አጠገብም ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفَٰكِهَةٍ كَثِيرَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy32. በብዙ ዓይነት ፍራፍሬዎችም ውስጥ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا مَقْطُوعَةٍ وَلَا مَمْنُوعَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. ምንጊዜም የማትቋረጥ የማትከለከልም የሆነች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفُرُشٍ مَّرْفُوعَةٍ

Amharic Translation - Africa Academy34. ከፍ በተደረጉ ምንጣፎች ላይም ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَنشَأْنَٰهُنَّ إِنشَآءً

Amharic Translation - Africa Academy35. እኛ (የገነት ሴቶችን) አዲስ ፍጥረት አድርገን ፈጠርናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَجَعَلْنَٰهُنَّ أَبْكَارًا

Amharic Translation - Africa Academy36. እናም ደናግሎችም አደረግናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عُرُبًا أَتْرَابًا

Amharic Translation - Africa Academy37. ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎችና እኩያዎች አደረግናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّأَصْحَٰبِ ٱلْيَمِينِ

Amharic Translation - Africa Academy38. ለቀኝ ጓዶች አዘጋጀናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُلَّةٌ مِّنَ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy39. ከፊተኞቹ ብዙ ቡድኖች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَثُلَّةٌ مِّنَ ٱلْـَٔاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy40. ከኋለኞቹም ብዙ ቡድኖች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَصْحَٰبُ ٱلشِّمَالِ مَآ أَصْحَٰبُ ٱلشِّمَالِ

Amharic Translation - Africa Academy41. የግራ ጓዶችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى سَمُومٍ وَحَمِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy42. በመርዛም ንፋስና በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَظِلٍّ مِّن يَحْمُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy43. ከጥቁር ጭስም በሆነ ጥላ ውስጥ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا بَارِدٍ وَلَا كَرِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy44. ቀዝቃዛም መልካምም ያልሆነ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَبْلَ ذَٰلِكَ مُتْرَفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy45. እነርሱ ከዚህ በፊት የነብያትን አስተምህሮት ወደ ጎን የተው የዱንያ ቅምጥሎች ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَانُوا۟ يُصِرُّونَ عَلَى ٱلْحِنثِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy46. በከባድ ኃጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَانُوا۟ يَقُولُونَ أَئِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبْعُوثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. (እንዲህ) ይሉ ነበርም፡ "ሞተን አፈር፣ አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَءَابَآؤُنَا ٱلْأَوَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy48. "የፊተኞቹ አባቶቻችንንም (ይቀሰቀሳሉን)?" (ይሉ ነበር)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِنَّ ٱلْأَوَّلِينَ وَٱلْـَٔاخِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) "ፊተኞቹም ሆኑ ኋለኞቹ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَمَجْمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَٰتِ يَوْمٍ مَّعْلُومٍ

Amharic Translation - Africa Academy50. "በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው" በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّكُمْ أَيُّهَا ٱلضَّآلُّونَ ٱلْمُكَذِّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy51. ከዚያም እናንተ ጠማሞችና አስተባባዩች ሆይ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَـَٔاكِلُونَ مِن شَجَرٍ مِّن زَقُّومٍ

Amharic Translation - Africa Academy52. ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَالِـُٔونَ مِنْهَا ٱلْبُطُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَشَٰرِبُونَ عَلَيْهِ مِنَ ٱلْحَمِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy54. በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَشَٰرِبُونَ شُرْبَ ٱلْهِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy55. የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذَا نُزُلُهُمْ يَوْمَ ٱلدِّينِ

Amharic Translation - Africa Academy56. ይህ የፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَحْنُ خَلَقْنَٰكُمْ فَلَوْلَا تُصَدِّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. (ሰዎች ሆይ!) እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتُم مَّا تُمْنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. በሴቶች ማህጸኖች የምታፈሱትን (የምትረጩትን ፍትወት) አያችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُۥٓ أَمْ نَحْنُ ٱلْخَٰلِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. እናንተ ትፈጥሩታላችሁን! ወይስ እኛ ነን ፈጣሪዎቹ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَحْنُ قَدَّرْنَا بَيْنَكُمُ ٱلْمَوْتَ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy60. እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ أَمْثَٰلَكُمْ وَنُنشِئَكُمْ فِى مَا لَا تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም ቅርጽ እናንተኑ በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ ٱلنَّشْأَةَ ٱلْأُولَىٰ فَلَوْلَا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. የፊተኛይቱን አፈጣጠር በእርግጥ አውቃችኋል አትገነዘቡምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتُم مَّا تَحْرُثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. የምትዘሩትን (አዝርአት) አያችሁን

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَنتُمْ تَزْرَعُونَهُۥٓ أَمْ نَحْنُ ٱلزَّٰرِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ نَشَآءُ لَجَعَلْنَٰهُ حُطَٰمًا فَظَلْتُمْ تَفَكَّهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. ብንሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባረደግነው እና የምትደነቁም በሆናችሁ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا لَمُغْرَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66. "እኛ በእዳ ተያዥዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ نَحْنُ مَحْرُومُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. "በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለክልን ነን" ትሉ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتُمُ ٱلْمَآءَ ٱلَّذِى تَشْرَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy68. ያንን ምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَنتُمْ أَنزَلْتُمُوهُ مِنَ ٱلْمُزْنِ أَمْ نَحْنُ ٱلْمُنزِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ نَشَآءُ جَعَلْنَٰهُ أُجَاجًا فَلَوْلَا تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. ብንፈልግ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር:: አታመሰግኑምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتُمُ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى تُورُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. ያችንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَأَنتُمْ أَنشَأْتُمْ شَجَرَتَهَآ أَمْ نَحْنُ ٱلْمُنشِـُٔونَ

Amharic Translation - Africa Academy72. እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَحْنُ جَعَلْنَٰهَا تَذْكِرَةً وَمَتَٰعًا لِّلْمُقْوِينَ

Amharic Translation - Africa Academy73. እኛ ለገሀነም ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسَبِّحْ بِٱسْمِ رَبِّكَ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy74. የታላቁን ጌታህንም ስም አጥራው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَآ أُقْسِمُ بِمَوَٰقِعِ ٱلنُّجُومِ

Amharic Translation - Africa Academy75. በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّهُۥ لَقَسَمٌ لَّوْ تَعْلَمُونَ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy76. እርሱም ብታውቁ ታላቅ መሀላ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy77. እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِى كِتَٰبٍ مَّكْنُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy78. በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥም ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَمَسُّهُۥٓ إِلَّا ٱلْمُطَهَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. የተጥራሩት እንጂ ሌላ አይነካዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنزِيلٌ مِّن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy80. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَبِهَٰذَا ٱلْحَدِيثِ أَنتُم مُّدْهِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81. በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَجْعَلُونَ رِزْقَكُمْ أَنَّكُمْ تُكَذِّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. ሲሳያችሁንም (ዝናብን) እናንተ የምታስተባበሉት ታደርጋላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَوْلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلْحُلْقُومَ

Amharic Translation - Africa Academy83. ነፍስ ጉሮሮንም በደረሰች ጊዜ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنتُمْ حِينَئِذٍ تَنظُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትሆኑ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنكُمْ وَلَٰكِن لَّا تُبْصِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. እኛም ግን እናንተ አታዩም እንጂ ከናንተ ይልቅ ወደ እርሱ የቀረብን ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَوْلَآ إِن كُنتُمْ غَيْرَ مَدِينِينَ

Amharic Translation - Africa Academy86. የማትዳኙም ከሆናችሁ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَرْجِعُونَهَآ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy87. እውነተኞች እንደሆናችሁ ነፍሲቱን ወደ አካል ለምን አትመልሷትም?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ

Amharic Translation - Africa Academy88. እናም ሟቹ ከባለሟሎቹ ከሆነም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَرَوْحٌ وَرَيْحَانٌ وَجَنَّتُ نَعِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy89. ለእርሱ እረፍት መልካም ሲሳይና የመጠቀሚያ ገነት አለው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنْ أَصْحَٰبِ ٱلْيَمِينِ

Amharic Translation - Africa Academy90. ሟቹ ከቀኝ ጓዶችም ከሆነ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسَلَٰمٌ لَّكَ مِنْ أَصْحَٰبِ ٱلْيَمِينِ

Amharic Translation - Africa Academy91."ከቀኝ ጓዶች ስለሆንክ ላንተ ሰላም ነው የሚገባህ" ይባላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلْمُكَذِّبِينَ ٱلضَّآلِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy92. ሟች ከእነዚያ ከሚያስተባብሉት ጠማማዎች ከሆነ ደግሞ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَنُزُلٌ مِّنْ حَمِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy93. ከፈላ ውሃ የሆነ መስተንግዶ አለለት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَصْلِيَةُ جَحِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy94. በገሀነም መቃጠልም አለለት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ ٱلْيَقِينِ

Amharic Translation - Africa Academy95. ይህ እርሱ እርግጠኛው እውነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَسَبِّحْ بِٱسْمِ رَبِّكَ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የታላቁ ጌታህን ስም አጥራው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70