caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hadid الحديد

29 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 94

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ። እርሱም ኃያሉና ጥበበኛው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy2. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱው ብቻ ነው:: ሕይወትን የሚሰጥና ሕይወትን የሚነሳ እሱው ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلْأَوَّلُ وَٱلْـَٔاخِرُ وَٱلظَّٰهِرُ وَٱلْبَاطِنُ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy3. እርሱ ( ከበፊቱ ምንም ያልቀደመው) የመጀመሪያ! (ፊት ያለ) (ከኋላው ምንም የሌለ የመጨረሻ) ብቻዉን ቀሪ፤ ከበላዩ ማንም የሌለ (ግልጽና የበላይ) ስውርም (ድብቅ) ነው:: እርሱ (በምድርም ሆነ በሰማይ ያለን) ሁሉ ነገር አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ

Amharic Translation - Africa Academy5. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَهُوَ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy6. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَأَنفِقُوا۟ مِمَّا جَعَلَكُم مُّسْتَخْلَفِينَ فِيهِ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَأَنفَقُوا۟ لَهُمْ أَجْرٌ كَبِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy7. (ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ:: አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ:: እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا لَكُمْ لَا تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلرَّسُولُ يَدْعُوكُمْ لِتُؤْمِنُوا۟ بِرَبِّكُمْ وَقَدْ أَخَذَ مِيثَٰقَكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy8. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبْدِهِۦٓ ءَايَٰتٍۭ بَيِّنَٰتٍ لِّيُخْرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَإِنَّ ٱللَّهَ بِكُمْ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው:: አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا لَكُمْ أَلَّا تُنفِقُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَا يَسْتَوِى مِنكُم مَّنْ أَنفَقَ مِن قَبْلِ ٱلْفَتْحِ وَقَٰتَلَ أُو۟لَٰٓئِكَ أَعْظَمُ دَرَجَةً مِّنَ ٱلَّذِينَ أَنفَقُوا۟ مِنۢ بَعْدُ وَقَٰتَلُوا۟ وَكُلًّا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْحُسْنَىٰ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy10. የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተከከልም:: ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና:: ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّن ذَا ٱلَّذِى يُقْرِضُ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥ وَلَهُۥٓ أَجْرٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy11. ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ تَرَى ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ يَسْعَىٰ نُورُهُم بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَٰنِهِم بُشْرَىٰكُمُ ٱلْيَوْمَ جَنَّٰتٌ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy12. ወንድ ትክክለኛ አማኞችንና ሴት ትክክለኛ አማኞችን በስተፊቶቻቸው በቀኞቻቸዉም ብርሀናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ታላቅ ምንዳ አለላቸው።) "ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ يَقُولُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱنظُرُونَا نَقْتَبِسْ مِن نُّورِكُمْ قِيلَ ٱرْجِعُوا۟ وَرَآءَكُمْ فَٱلْتَمِسُوا۟ نُورًا فَضُرِبَ بَيْنَهُم بِسُورٍ لَّهُۥ بَابٌۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحْمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلْعَذَابُ

Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት "ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና" የሚሉበትን ቀን አስታውስ:: "ወደ ኋላችሁ ተመለሱ:: ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ" ይባላሉ:: በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል:: ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُنَادُونَهُمْ أَلَمْ نَكُن مَّعَكُمْ قَالُوا۟ بَلَىٰ وَلَٰكِنَّكُمْ فَتَنتُمْ أَنفُسَكُمْ وَتَرَبَّصْتُمْ وَٱرْتَبْتُمْ وَغَرَّتْكُمُ ٱلْأَمَانِىُّ حَتَّىٰ جَآءَ أَمْرُ ٱللَّهِ وَغَرَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ

Amharic Translation - Africa Academy14. "ከናንተ ጋር አልነበርንምን?" በማለት ይጠሯቸዋል:: "እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ:: ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ:: በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ትጠራጠራላችሁም:: የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱلْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مَأْوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ هِىَ مَوْلَىٰكُمْ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy15. በመሆኑም ዛሬ ከናንተም ሆነ በአላህ ከካዱት ሰዎች የገንዘብ ክፍያ (ቤዛ) አይወሰድም:: መኖሪያችሁ የገሀነም እሳት ብቻ ናት:: እርሷ ተገቢያችሁ ናትና:: የገሀነም እሳት መመለሻነቷ ምን ትከፋም" (ይሏቸዋል)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ ٱلْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ለእነዚያ (በአላህ) ላመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው እውነታ ልቦቻቸው ሊፈሩ፤ እንደነዚያ በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ ስለ ረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁባቸው ህዝቦች የማይሆኑበት ጊዜ አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يُحْىِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው የሚደርጋት መሆኑን እወቁ። ታውቁም ዘንድ አናቅጽን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُصَّدِّقِينَ وَٱلْمُصَّدِّقَٰتِ وَأَقْرَضُوا۟ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَٰعَفُ لَهُمْ وَلَهُمْ أَجْرٌ كَرِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy18. የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህ መልካምን ብድር ያበደሩ ሁሉ ለእነርሱም ምንዳ ይደራረብላቸዋል:: ለእነርሱም መልካም የተከበረ ምንዳ አለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصِّدِّيقُونَ وَٱلشُّهَدَآءُ عِندَ رَبِّهِمْ لَهُمْ أَجْرُهُمْ وَنُورُهُمْ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَآ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy19. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ ሰዎች እነዚያ እነርሱ በጣም እውነቶኞች በጌታቸዉም ዘንድ መስካሪዎች ናቸው:: ለእነርሱ ምንዳቸውም ብርሀናቸዉም አለላቸው:: እነዚያ (በአላህ) የካዱትና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሰዎች ደግሞ የእሳት ጓዶች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌۢ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِى ٱلْأَمْوَٰلِ وَٱلْأَوْلَٰدِ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ ٱلْكُفَّارَ نَبَاتُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَٰمًا وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنٌ وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلْغُرُورِ

Amharic Translation - Africa Academy20. (ሰዎች ሆይ!) ቅርቢቱን ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፤ ማጌጫም፤ በመካከችሁም መፎካከሪያ፤ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆኗን እወቁ:: እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን ቡቃያው እንደሚያስደስት ዝናብና ከዚያ በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደሚታየው ከዚም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ለአጥፊዎች ብርቱ ቅጣት፤ ለትክክለኛ አማኞች ከአላህ ምህረትና ውዴታ አለ:: የቅርቢቱ ሕይወት እኮ የመታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَابِقُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا كَعَرْضِ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ أُعِدَّتْ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ذَٰلِكَ فَضْلُ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy21. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኞች ላመኑት ወደ ተዘጋጀችውና የወርዷ ስፋት እንደ ሰማይና ምድር ወደ ሆነችም ገነት ተሸቀዳደሙ:: ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚፈልገው ሰው ብቻ ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَآ أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مِّن قَبْلِ أَن نَّبْرَأَهَآ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy22. በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ መከራ ማንንም አታጋጥምም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጂ:: ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّكَيْلَا تَأْسَوْا۟ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا تَفْرَحُوا۟ بِمَآ ءَاتَىٰكُمْ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ

Amharic Translation - Africa Academy23. (ይህን ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑና አላህ በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው:: አላህ ኩራተኛንና ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَبْخَلُونَ وَيَأْمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلْبُخْلِ وَمَن يَتَوَلَّ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْغَنِىُّ ٱلْحَمِيدُ

Amharic Translation - Africa Academy24. እነርሱም እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት ላይ የሚያዙ ናቸው:: ከእውነት የሚሸሽ (ሰው) ሁሉ ጉዳቱ ለራሱ ብቻ ነው:: አላህ ተብቃቂ ና ምስጉን ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ وَأَنزَلْنَا ٱلْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَلِيَعْلَمَ ٱللَّهُ مَن يَنصُرُهُۥ وَرُسُلَهُۥ بِٱلْغَيْبِ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِىٌّ عَزِيزٌ

Amharic Translation - Africa Academy25. መልዕክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች አጠናክረን በእርግጥ ላክን:: ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን:: ብረትንም ከውስጡ ብርቱ ኃይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን:: አላህ ሃይማኖትንና መልዕክተኞችን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን (ሰው) ሊያውቅ (ሊገልጽ) አወረደው:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا وَإِبْرَٰهِيمَ وَجَعَلْنَا فِى ذُرِّيَّتِهِمَا ٱلنُّبُوَّةَ وَٱلْكِتَٰبَ فَمِنْهُم مُّهْتَدٍ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ኑህንና ኢብራሂምን በእርግጥ ላክን:: በዘሮቻቸዉም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍትን አደረግን:: ከእነርሱም መካከል ቅን ሰው አለ:: ከእነርሱም መካከል ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ٱبْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَٰهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ٱبْتِغَآءَ رِضْوَٰنِ ٱللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا فَـَٔاتَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ከዚያም በእነርሱ ፈለጋቸው ላይ መልዕክተኞችን አከታተልን:: የመርየም ልጅን ዒሳንም አስከተልን:: ኢንጂልንም ሰጠነው:: በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፤ አዲስ የፈጠሯትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልደነገግንም:: ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ከራሳቸው ፈጠሯት:: ተገቢ አጠባበቅንም አልጠበቋትም:: ከእነርሱም መካከል በአላህ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው:: ከእነርሱ ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَءَامِنُوا۟ بِرَسُولِهِۦ يُؤْتِكُمْ كِفْلَيْنِ مِن رَّحْمَتِهِۦ وَيَجْعَل لَّكُمْ نُورًا تَمْشُونَ بِهِۦ وَيَغْفِرْ لَكُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: በመልክተኛዉም እመኑ:: ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና:: ለእናተም የምትሄዱበትን ብርሃን ያደርግላችኋል:: ለእናንተም ወንጀላችሁን ይምራል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّئَلَّا يَعْلَمَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ أَلَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَىْءٍ مِّن فَضْلِ ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلْفَضْلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy29. (ይህም) የመጽሐፍ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውንና ችሮታዉም አላህ ለሚሻው ሰው ብቻ የሚሰጠው በእርሱ እጅ ብቻ መሆኑን እንዲያውቁ ነው:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70