caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Kahf الكهف

110 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 69

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ ٱلْكِتَٰبَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُۥ عِوَجَا

Amharic Translation - Africa Academy1-ምስጋና ሁሉ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ ቅንጣት መጣመምን ሳያደርግ በባሪያው (በሙሐመድ) ላይ ላወረደው ለአላህ ብቻ ይገባው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَيِّمًا لِّيُنذِرَ بَأْسًا شَدِيدًا مِّن لَّدُنْهُ وَيُبَشِّرَ ٱلْمُؤْمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعْمَلُونَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا حَسَنًا

Amharic Translation - Africa Academy2. ቀጥተኛ ሲሆን ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፤ እነዚያንም በጎ ሰሪዎችን ለእነርሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን ሊያበስርበት (አወረደው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّٰكِثِينَ فِيهِ أَبَدًا

Amharic Translation - Africa Academy3. በውስጡም ዘለዓለም የሚቆዩ መሆናቸውን ሊያበስርበት አወረደው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُنذِرَ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል።» ያሉትን ሊያስፈራራበት (ቁርኣንን አወረደው።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ وَلَا لِـَٔابَآئِهِمْ كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَٰهِهِمْ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا

Amharic Translation - Africa Academy5.ለእነርሱም ሆነ ለአባቶቻቸው ስለ አላህ ልጅ መኖር ምንም እውቀት የላቸዉም:: ከአፎቻቸው የሚወጣው ቃል ምን አከበደው! ውሸትን እንጂ ሌላን አይናገሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَعَلَّكَ بَٰخِعٌ نَّفْسَكَ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمْ إِن لَّمْ يُؤْمِنُوا۟ بِهَٰذَا ٱلْحَدِيثِ أَسَفًا

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚህም ንግግር በቁርኣን ካላመኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሀል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا جَعَلْنَا مَا عَلَى ٱلْأَرْضِ زِينَةً لَّهَا لِنَبْلُوَهُمْ أَيُّهُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا

Amharic Translation - Africa Academy7.እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መሆኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ የእርሷ ጌጥ አደረግን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّا لَجَٰعِلُونَ مَا عَلَيْهَا صَعِيدًا جُرُزًا

Amharic Translation - Africa Academy8. እኛ በእርሷ ላይ ያለውን ሁሉ በመጨረሻ ቡቃያ የሌለበት ምልጥ አፈር አድራጊዎች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ حَسِبْتَ أَنَّ أَصْحَٰبَ ٱلْكَهْفِ وَٱلرَّقِيمِ كَانُوا۟ مِنْ ءَايَٰتِنَا عَجَبًا

Amharic Translation - Africa Academy9-(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራታችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ أَوَى ٱلْفِتْيَةُ إِلَى ٱلْكَهْفِ فَقَالُوا۟ رَبَّنَآ ءَاتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا

Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወጣቶቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና: «ጌታችን ሆይ! ካንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን:: ለእኛም ከነገራችን ቅንን ነገር አዘጋጅልን።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውስ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَضَرَبْنَا عَلَىٰٓ ءَاذَانِهِمْ فِى ٱلْكَهْفِ سِنِينَ عَدَدًا

Amharic Translation - Africa Academy11. በዋሻዉም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው (አስተኛናቸው)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ بَعَثْنَٰهُمْ لِنَعْلَمَ أَىُّ ٱلْحِزْبَيْنِ أَحْصَىٰ لِمَا لَبِثُوٓا۟ أَمَدًا

Amharic Translation - Africa Academy12.ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ ከተኙበት አስነሳናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نَّحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ نَبَأَهُم بِٱلْحَقِّ إِنَّهُمْ فِتْيَةٌ ءَامَنُوا۟ بِرَبِّهِمْ وَزِدْنَٰهُمْ هُدًى

Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወሬያቸውን ባንተ ላይ በእውነት እንተርክልሃለን:: እነርሱ በጌታቸው በትክክል ያመኑ ወጣቶች ናቸው:: ወደ ቀናው መንገድ መመራትንም ጨመርንላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَبَطْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ إِذْ قَامُوا۟ فَقَالُوا۟ رَبُّنَا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَن نَّدْعُوَا۟ مِن دُونِهِۦٓ إِلَٰهًا لَّقَدْ قُلْنَآ إِذًا شَطَطًا

Amharic Translation - Africa Academy14. በንጉሳቸው ፊት በቆሙና እንዲህም ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን በእምነት አጠነከርን: «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክን አንገዛም:: ከእሱ ሌላን ብናመልክማ ወሰን ያለፈን ንግግር በእርግጥ ተናገርን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰٓؤُلَآءِ قَوْمُنَا ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً لَّوْلَا يَأْتُونَ عَلَيْهِم بِسُلْطَٰنٍۭ بَيِّنٍ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا

Amharic Translation - Africa Academy15. «እነዚህ ህዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ:: እውነተኞች ከሆኑ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም? በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذِ ٱعْتَزَلْتُمُوهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ فَأْوُۥٓا۟ إِلَى ٱلْكَهْفِ يَنشُرْ لَكُمْ رَبُّكُم مِّن رَّحْمَتِهِۦ وَيُهَيِّئْ لَكُم مِّنْ أَمْرِكُم مِّرْفَقًا

Amharic Translation - Africa Academy16. «እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በተለያችሁ ጊዜ ወደ ዋሻው ተጠጉ። ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያ ያዘጋጅላችኋልና።» (ተባባሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَى ٱلشَّمْسَ إِذَا طَلَعَت تَّزَٰوَرُ عَن كَهْفِهِمْ ذَاتَ ٱلْيَمِينِ وَإِذَا غَرَبَت تَّقْرِضُهُمْ ذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَهُمْ فِى فَجْوَةٍ مِّنْهُ ذَٰلِكَ مِنْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ مَن يَهْدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلْمُهْتَدِ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ وَلِيًّا مُّرْشِدًا

Amharic Translation - Africa Academy17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَحْسَبُهُمْ أَيْقَاظًا وَهُمْ رُقُودٌ وَنُقَلِّبُهُمْ ذَاتَ ٱلْيَمِينِ وَذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَكَلْبُهُم بَٰسِطٌ ذِرَاعَيْهِ بِٱلْوَصِيدِ لَوِ ٱطَّلَعْتَ عَلَيْهِمْ لَوَلَّيْتَ مِنْهُمْ فِرَارًا وَلَمُلِئْتَ مِنْهُمْ رُعْبًا

Amharic Translation - Africa Academy18. እነርሱ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ የነቁ ይመስሉሃል:: ወደቀኝና ወደ ግራ ጎናቸው እናገላብጣቸዋለን:: ውሻቸዉም በዋሻቸው በር ላይ የፊት እግሩን ዘርግቷል:: ብታያቸው ኖሮ ከእነርሱ በእርግጥ የምትሸሽ ኾነህ በዞርክ ነበር:: በፍርሀትም በተሞላህ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ بَعَثْنَٰهُمْ لِيَتَسَآءَلُوا۟ بَيْنَهُمْ قَالَ قَآئِلٌ مِّنْهُمْ كَمْ لَبِثْتُمْ قَالُوا۟ لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ قَالُوا۟ رَبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا لَبِثْتُمْ فَٱبْعَثُوٓا۟ أَحَدَكُم بِوَرِقِكُمْ هَٰذِهِۦٓ إِلَى ٱلْمَدِينَةِ فَلْيَنظُرْ أَيُّهَآ أَزْكَىٰ طَعَامًا فَلْيَأْتِكُم بِرِزْقٍ مِّنْهُ وَلْيَتَلَطَّفْ وَلَا يُشْعِرَنَّ بِكُمْ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُمْ إِن يَظْهَرُوا۟ عَلَيْكُمْ يَرْجُمُوكُمْ أَوْ يُعِيدُوكُمْ فِى مِلَّتِهِمْ وَلَن تُفْلِحُوٓا۟ إِذًا أَبَدًا

Amharic Translation - Africa Academy20. «እነርሱ በእናንተ ላይ ቢዘልቁ ይቀጠቅጧችኋል:: ወይም ወደ ሃይማኖታቸው ይመልሷችኋል፤ ያን ጊዜም በፍጹም ፍላጎታችሁን አታገኙም።» ተባባሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ أَعْثَرْنَا عَلَيْهِمْ لِيَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَأَنَّ ٱلسَّاعَةَ لَا رَيْبَ فِيهَآ إِذْ يَتَنَٰزَعُونَ بَيْنَهُمْ أَمْرَهُمْ فَقَالُوا۟ ٱبْنُوا۟ عَلَيْهِم بُنْيَٰنًا رَّبُّهُمْ أَعْلَمُ بِهِمْ قَالَ ٱلَّذِينَ غَلَبُوا۟ عَلَىٰٓ أَمْرِهِمْ لَنَتَّخِذَنَّ عَلَيْهِم مَّسْجِدًا

Amharic Translation - Africa Academy21. ልክ እንደዚሁም የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን ሰዓቲቱም በእርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሰዎችን አሳወቅን:: አማኞቹና ከሓዲያን ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ የሆነውን አስታውስ:: ከሓዲያን «በእነርሱ ላይ ግንብን ገንቡ።» አሉ:: ጌታቸው ለእነርሱ ይበልጥ አዋቂ ነው:: እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት ግን «በእነርሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ قُل رَّبِّىٓ أَعْلَمُ بِعِدَّتِهِم مَّا يَعْلَمُهُمْ إِلَّا قَلِيلٌ فَلَا تُمَارِ فِيهِمْ إِلَّا مِرَآءً ظَٰهِرًا وَلَا تَسْتَفْتِ فِيهِم مِّنْهُمْ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَقُولَنَّ لِشَا۟ىْءٍ إِنِّى فَاعِلٌ ذَٰلِكَ غَدًا

Amharic Translation - Africa Academy23 ለማንኛዉም ነገር «እኔ ይህንን ነገ ሠሪ ነኝ።» አትበል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ وَٱذْكُر رَّبَّكَ إِذَا نَسِيتَ وَقُلْ عَسَىٰٓ أَن يَهْدِيَنِ رَبِّى لِأَقْرَبَ مِنْ هَٰذَا رَشَدًا

Amharic Translation - Africa Academy24. «አላህ ቢሻ እሠራዋለሁ።» ብትል እንጂ። በረሳህ ጊዜም ጌታህን አውሳ። «ጌታዬም ከዚህ ይበልጥ ለቀጥታ የቀረበን ሊመራኝ ይከጀላል» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَبِثُوا۟ فِى كَهْفِهِمْ ثَلَٰثَ مِا۟ئَةٍ سِنِينَ وَٱزْدَادُوا۟ تِسْعًا

Amharic Translation - Africa Academy25. በዋሻቸዉም ውስጥ ሶስት መቶ ዓመታትን ቆዩ:: ዘጠኝ አመታትንም ጨመሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلِ ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا لَبِثُوا۟ لَهُۥ غَيْبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَبْصِرْ بِهِۦ وَأَسْمِعْ مَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِىٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِى حُكْمِهِۦٓ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ብቻ የቆዩትን ልክ በትክክል አዋቂ ነው። የሰማያትና የምድር ሚስጢር የእሱ ብቻ ነዉ። እርሱ (አላህ) ሁሉን ተመልካች ሁሉን ሰሚ መሆኑ ይግረምህ። ለእነርሱ ከእርሱ በስተቀር ምንም ወዳጅ የላቸዉም:: በፍርዱም አንድንም አያጋራም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتْلُ مَآ أُوحِىَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَ لَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَن تَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلْتَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ መጽሀፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ለቃሎቹ ለዋጭ የላቸዉም:: ከርሱም በስተቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱصْبِرْ نَفْسَكَ مَعَ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ رَبَّهُم بِٱلْغَدَوٰةِ وَٱلْعَشِىِّ يُرِيدُونَ وَجْهَهُۥ وَلَا تَعْدُ عَيْنَاكَ عَنْهُمْ تُرِيدُ زِينَةَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُۥ عَن ذِكْرِنَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ وَكَانَ أَمْرُهُۥ فُرُطًا

Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُلِ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَن شَآءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَآءَ فَلْيَكْفُرْ إِنَّآ أَعْتَدْنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا وَإِن يَسْتَغِيثُوا۟ يُغَاثُوا۟ بِمَآءٍ كَٱلْمُهْلِ يَشْوِى ٱلْوُجُوهَ بِئْسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتْ مُرْتَفَقًا

Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ مَنْ أَحْسَنَ عَمَلًا

Amharic Translation - Africa Academy30. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ እኛ ሥራ ያሳመረን ምንዳ አናጠፋም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ جَنَّٰتُ عَدْنٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهِمُ ٱلْأَنْهَٰرُ يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٍ وَيَلْبَسُونَ ثِيَابًا خُضْرًا مِّن سُندُسٍ وَإِسْتَبْرَقٍ مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ نِعْمَ ٱلثَّوَابُ وَحَسُنَتْ مُرْتَفَقًا

Amharic Translation - Africa Academy31.እነዚያ ለእነርሱ የመኖሪያ ገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አሏቸው:: በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አምባሮች ይሸለማሉ:: ከቀጭን ሀርና ከወፍራም ሀርም አረንጓዴ ልብሶችን ይለብሳሉ:: በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ የተደገፉ ሆነው ይቀመጣሉ:: እነዚህ ሰዎች ምንዳቸው ምን ያምር! መኖሪያቸው ገነትም ምንኛ አማረች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا رَّجُلَيْنِ جَعَلْنَا لِأَحَدِهِمَا جَنَّتَيْنِ مِنْ أَعْنَٰبٍ وَحَفَفْنَٰهُمَا بِنَخْلٍ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمَا زَرْعًا

Amharic Translation - Africa Academy32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለከሓዲያን የሁለትን ሰዎችን ምሳሌ ግለጽላቸው:: ለአንደኛው ከሓዲ ሁለት የወይን አትክልቶች አደረግንለት። በዘንባባም ከበብናቸው። በመካከላቸውም አዝመራን አደረግን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كِلْتَا ٱلْجَنَّتَيْنِ ءَاتَتْ أُكُلَهَا وَلَمْ تَظْلِم مِّنْهُ شَيْـًٔا وَفَجَّرْنَا خِلَٰلَهُمَا نَهَرًا

Amharic Translation - Africa Academy33. ሁለቱም አትክልቶች ሰብላቸውን ሰጡ፤ ከርሱም ምንም አላጎደሉም። በመካከላቸዉም ወንዝን አፈሰስን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَانَ لَهُۥ ثَمَرٌ فَقَالَ لِصَٰحِبِهِۦ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَنَا۠ أَكْثَرُ مِنكَ مَالًا وَأَعَزُّ نَفَرًا

Amharic Translation - Africa Academy34.ለእርሱ ከአትክልቶቹ ሌላ ፍሬያማ ሀብት ነበረው:: ለአማኙ ጓደኛዉም የሚወዳደረው ሲሆን «እኔ ካንተ በገንዘብ ይበልጥ የበዛሁ በወገንም ይበልጥ የበረታሁ ነኝ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدَخَلَ جَنَّتَهُۥ وَهُوَ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِۦ قَالَ مَآ أَظُنُّ أَن تَبِيدَ هَٰذِهِۦٓ أَبَدًا

Amharic Translation - Africa Academy35. እርሱም ነፍሱንም በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ። (እንዲህም) አለ: «ይህች አትክልት መቸም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةً وَلَئِن رُّدِدتُّ إِلَىٰ رَبِّى لَأَجِدَنَّ خَيْرًا مِّنْهَا مُنقَلَبًا

Amharic Translation - Africa Academy36. «ሰዓቲቱንም ትከሰታለች ብዬ አልጠረጥርም፤ እንደምትለው ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرْتَ بِٱلَّذِى خَلَقَكَ مِن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلًا

Amharic Translation - Africa Academy37. አማኙ ጓደኛውም ለእርሱ የሚመላለሰው ሲሆን (እንዲህ) አለው: «በዚያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ በፈጠረህ ከዚያም ሰው ባደረገህ ሃያል አምላክ ካድክን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّٰكِنَّا۠ هُوَ ٱللَّهُ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِرَبِّىٓ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy38. «እኔ ግን አላህ ጌታዬ ነው እላለሁ። በጌታዬም አንድንም አላጋራም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْلَآ إِذْ دَخَلْتَ جَنَّتَكَ قُلْتَ مَا شَآءَ ٱللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِٱللَّهِ إِن تَرَنِ أَنَا۠ أَقَلَّ مِنكَ مَالًا وَوَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy39. «እኔን በገንዘብም ሆነ በልጅ ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝም ወደ አትክልትህ በገባህ ጊዜ ‹አላህ የሻው ሆኗል። በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም የለም› አትልም ኖሯልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَعَسَىٰ رَبِّىٓ أَن يُؤْتِيَنِ خَيْرًا مِّن جَنَّتِكَ وَيُرْسِلَ عَلَيْهَا حُسْبَانًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَتُصْبِحَ صَعِيدًا زَلَقًا

Amharic Translation - Africa Academy40. «ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በአትክልትህ ላይ ደግሞ በሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትሆንም ይቻላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوْ يُصْبِحَ مَآؤُهَا غَوْرًا فَلَن تَسْتَطِيعَ لَهُۥ طَلَبًا

Amharic Translation - Africa Academy41. «ወይም ውሀው ሰራጊ ሊሆንብህ ይችላል። ያን ጊዜ እርሱን መፈለጉን ፈጽሞ አትችልም።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِۦ فَأَصْبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيْهِ عَلَىٰ مَآ أَنفَقَ فِيهَا وَهِىَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُشْرِكْ بِرَبِّىٓ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy42. ሀብቱም ተጠፋ:: እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ የተጸጸተ መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ።» የሚል ሆነ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ فِئَةٌ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مُنتَصِرًا

Amharic Translation - Africa Academy43.እርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች አልነበሩትም:: ተረጂም አልነበረም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُنَالِكَ ٱلْوَلَٰيَةُ لِلَّهِ ٱلْحَقِّ هُوَ خَيْرٌ ثَوَابًا وَخَيْرٌ عُقْبًا

Amharic Translation - Africa Academy44.እዚያ ዘንድ በትንሳኤ ቀን ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا كَمَآءٍ أَنزَلْنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخْتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلْأَرْضِ فَأَصْبَحَ هَشِيمًا تَذْرُوهُ ٱلرِّيَٰحُ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ مُّقْتَدِرًا

Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْمَالُ وَٱلْبَنُونَ زِينَةُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَٱلْبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيْرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابًا وَخَيْرٌ أَمَلًا

Amharic Translation - Africa Academy46. ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ህይወት ጌጦች ብቻ ናቸው:: መልካም ቀሪ ሥራዎች ግን በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በተስፋም በላጭ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ نُسَيِّرُ ٱلْجِبَالَ وَتَرَى ٱلْأَرْضَ بَارِزَةً وَحَشَرْنَٰهُمْ فَلَمْ نُغَادِرْ مِنْهُمْ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተራራዎችን የምናስኬድበትን ቀን አስታውስ:: ምድርንም ግልጽ ሆና ታያታለህ:: እንሰበስባቸዋለንም:: ከእነርሱ አንድንም አንተዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعُرِضُوا۟ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفًّا لَّقَدْ جِئْتُمُونَا كَمَا خَلَقْنَٰكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍۭ بَلْ زَعَمْتُمْ أَلَّن نَّجْعَلَ لَكُم مَّوْعِدًا

Amharic Translation - Africa Academy48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوُضِعَ ٱلْكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلْمُجْرِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيْلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلْكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةً وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحْصَىٰهَا وَوَجَدُوا۟ مَا عَمِلُوا۟ حَاضِرًا وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy49 ለሰው ሁሉ መጽሐፉ ይቀርባል:: ወዲያዉም ከሓዲያንን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። «ዋ ጥፋታችን! ይህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው?» ይላሉ:: የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቅርብ ሆኖ ያገኙታል:: ጌታህም አንድንም አይበድልም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَٰٓئِكَةِ ٱسْجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ ٱلْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِۦٓ أَفَتَتَّخِذُونَهُۥ وَذُرِّيَّتَهُۥٓ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِى وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّۢ بِئْسَ لِلظَّٰلِمِينَ بَدَلًا

Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክት «ለአደም ስገዱ።» ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ወዲያዉም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሁሉም ሰገዱ:: ከአጋንንት ጎሳ ነበርና:: ከጌታዉም ትዕዛዝ ወጣ:: እርሱንና ዘሮቹን እነርሱም ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከኔ ሌላ ረዳቶች ታደርጋላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّآ أَشْهَدتُّهُمْ خَلْقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَلَا خَلْقَ أَنفُسِهِمْ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ ٱلْمُضِلِّينَ عَضُدًا

Amharic Translation - Africa Academy51.የሰማያትና የምድርም አፈጣጠር አላሰየኋቸዉም:: የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር እንደዚሁ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَوْمَ يَقُولُ نَادُوا۟ شُرَكَآءِىَ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُمْ فَدَعَوْهُمْ فَلَمْ يَسْتَجِيبُوا۟ لَهُمْ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُم مَّوْبِقًا

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያንም አምላክ የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ።» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: ይጠሯቸዋልም። ግን አይመልሱላቸዉም:: በመካከላቸዉም መጥፊያን ስፍራ ገሀነምንም አደረግን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَءَا ٱلْمُجْرِمُونَ ٱلنَّارَ فَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُم مُّوَاقِعُوهَا وَلَمْ يَجِدُوا۟ عَنْهَا مَصْرِفًا

Amharic Translation - Africa Academy53. ከሓዲያንም እሳትን ያያሉ፤ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ صَرَّفْنَا فِى هَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ لِلنَّاسِ مِن كُلِّ مَثَلٍ وَكَانَ ٱلْإِنسَٰنُ أَكْثَرَ شَىْءٍ جَدَلًا

Amharic Translation - Africa Academy54. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከየምሳሌው ሁሉ ለሰዎች መላልሰን ገለጽን፤ ሰዉም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤْمِنُوٓا۟ إِذْ جَآءَهُمُ ٱلْهُدَىٰ وَيَسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّهُمْ إِلَّآ أَن تَأْتِيَهُمْ سُنَّةُ ٱلْأَوَّلِينَ أَوْ يَأْتِيَهُمُ ٱلْعَذَابُ قُبُلًا

Amharic Translation - Africa Academy55.ሰዎችንም መመሪያ በመጣላችሁ ጊዜ ከማመንና ጌታቸውንም ምህረትን ከመለመን የከለከላቸው የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ልማድ መጥፋት ልትመጣባቸው ወይም ቅጣቱ በየዓይነቱ ሊመጣባቸው መጠባበቅ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا نُرْسِلُ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَيُجَٰدِلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِٱلْبَٰطِلِ لِيُدْحِضُوا۟ بِهِ ٱلْحَقَّ وَٱتَّخَذُوٓا۟ ءَايَٰتِى وَمَآ أُنذِرُوا۟ هُزُوًا

Amharic Translation - Africa Academy56. መልዕክተኞችንም አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች ሆነው እንጂ አንልክም:: እነዚያ የካዱትም በውሸት እውነቱን በእሱ ሊያበላሹ ይከራከራሉ:: አንቀፆቼንና በእርሱ የተስፈራሩበትንም ነገር ማላገጫ አድርገው ያዙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ فَأَعْرَضَ عَنْهَا وَنَسِىَ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ إِنَّا جَعَلْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَن يَفْقَهُوهُ وَفِىٓ ءَاذَانِهِمْ وَقْرًا وَإِن تَدْعُهُمْ إِلَى ٱلْهُدَىٰ فَلَن يَهْتَدُوٓا۟ إِذًا أَبَدًا

Amharic Translation - Africa Academy57.በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከእርሷም ከዞረ፤ ሁለት እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳቸዉም ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَبُّكَ ٱلْغَفُورُ ذُو ٱلرَّحْمَةِ لَوْ يُؤَاخِذُهُم بِمَا كَسَبُوا۟ لَعَجَّلَ لَهُمُ ٱلْعَذَابَ بَل لَّهُم مَّوْعِدٌ لَّن يَجِدُوا۟ مِن دُونِهِۦ مَوْئِلًا

Amharic Translation - Africa Academy58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በጣም መሀሪው የእዝነት ባለቤት ነው:: በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነርሱ ባስቸኮለባቸው ነበር:: ግን ለእነርሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتِلْكَ ٱلْقُرَىٰٓ أَهْلَكْنَٰهُمْ لَمَّا ظَلَمُوا۟ وَجَعَلْنَا لِمَهْلِكِهِم مَّوْعِدًا

Amharic Translation - Africa Academy59.እነዚህ ከተሞችም በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፤ ለመጥፊያቸዉም የተወሰነ ጊዜ አደረግን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَىٰهُ لَآ أَبْرَحُ حَتَّىٰٓ أَبْلُغَ مَجْمَعَ ٱلْبَحْرَيْنِ أَوْ أَمْضِىَ حُقُبًا

Amharic Translation - Africa Academy60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለወጣቱ «የሁለቱን ባህሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምሄድ ድረስ ከመጓዝ አልወገድም።» ያለውን (አስታውስ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا بَلَغَا مَجْمَعَ بَيْنِهِمَا نَسِيَا حُوتَهُمَا فَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِى ٱلْبَحْرِ سَرَبًا

Amharic Translation - Africa Academy61. የሁለቱን ባህር መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዓሳቸውን ረሱ፤ ዓሳውም መንገዱን በባህር ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا جَاوَزَا قَالَ لِفَتَىٰهُ ءَاتِنَا غَدَآءَنَا لَقَدْ لَقِينَا مِن سَفَرِنَا هَٰذَا نَصَبًا

Amharic Translation - Africa Academy62. ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَرَءَيْتَ إِذْ أَوَيْنَآ إِلَى ٱلصَّخْرَةِ فَإِنِّى نَسِيتُ ٱلْحُوتَ وَمَآ أَنسَىٰنِيهُ إِلَّا ٱلشَّيْطَٰنُ أَنْ أَذْكُرَهُۥ وَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِى ٱلْبَحْرِ عَجَبًا

Amharic Translation - Africa Academy63. «አየህን? ወደ ቋጥኟ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሳውን ረሳሁ፤ ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፤ በባህሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ መንገድ አድርጎ ያዘ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ذَٰلِكَ مَا كُنَّا نَبْغِ فَٱرْتَدَّا عَلَىٰٓ ءَاثَارِهِمَا قَصَصًا

Amharic Translation - Africa Academy64. ሙሳም «ይህ እኮ እንፈልገው የነበረው ነው።» አለው። ከዚያ በኮቴዎቻቸው (ዱካቸው) ላይ እየተከተሉ ተመለሱ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَجَدَا عَبْدًا مِّنْ عِبَادِنَآ ءَاتَيْنَٰهُ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَعَلَّمْنَٰهُ مِن لَّدُنَّا عِلْمًا

Amharic Translation - Africa Academy65.ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከኛም ዘንድ እውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያችንን አገኙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰ هَلْ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰٓ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمْتَ رُشْدًا

Amharic Translation - Africa Academy66. ሙሳ «ለእርሱ ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን እውቀት ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህ?» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنَّكَ لَن تَسْتَطِيعَ مَعِىَ صَبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy67. ባሪያዉም አለ: «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَيْفَ تَصْبِرُ عَلَىٰ مَا لَمْ تُحِطْ بِهِۦ خُبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy68. «በእውቀት ባልደረስክበት ነገር ላይስ እንዴት ትታገሳለህ?»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ صَابِرًا وَلَآ أَعْصِى لَكَ أَمْرًا

Amharic Translation - Africa Academy69. ሙሳም «አላህ የፈለገ እንደሆነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ فَإِنِ ٱتَّبَعْتَنِى فَلَا تَسْـَٔلْنِى عَن شَىْءٍ حَتَّىٰٓ أُحْدِثَ لَكَ مِنْهُ ذِكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy70. «ብትከተለኝም ላንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا رَكِبَا فِى ٱلسَّفِينَةِ خَرَقَهَا قَالَ أَخَرَقْتَهَا لِتُغْرِقَ أَهْلَهَا لَقَدْ جِئْتَ شَيْـًٔا إِمْرًا

Amharic Translation - Africa Academy71. ሄዱም:: በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ መርከቢቱን ቀደዳት። «ባለቤቶችዋን ልታሰምጥ ቀደድካትን? ትልቅን ጥፋት በእርግጥ ሠራህ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَلَمْ أَقُلْ إِنَّكَ لَن تَسْتَطِيعَ مَعِىَ صَبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy72. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ لَا تُؤَاخِذْنِى بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرْهِقْنِى مِنْ أَمْرِى عُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy73. «በረሳሁት ነገር አትያዝብኝ:: ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا لَقِيَا غُلَٰمًا فَقَتَلَهُۥ قَالَ أَقَتَلْتَ نَفْسًا زَكِيَّةًۢ بِغَيْرِ نَفْسٍ لَّقَدْ جِئْتَ شَيْـًٔا نُّكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy74. ወርደው ተጓዙም ወጣቱንም ልጅ ባገኘውና በገደለው ጊዜ «ነፍስን ያልገደለችን ንጹህን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሰራህ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَلَمْ أَقُل لَّكَ إِنَّكَ لَن تَسْتَطِيعَ مَعِىَ صَبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy75. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩህምን?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِن سَأَلْتُكَ عَن شَىْءٍۭ بَعْدَهَا فَلَا تُصَٰحِبْنِى قَدْ بَلَغْتَ مِن لَّدُنِّى عُذْرًا

Amharic Translation - Africa Academy76. «ከአሁኒቱ በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ አትጎዳኘኝ:: ከእኔ የይቅርታን መጨረሻ በእርግጥ ደርሰሃል።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَيَآ أَهْلَ قَرْيَةٍ ٱسْتَطْعَمَآ أَهْلَهَا فَأَبَوْا۟ أَن يُضَيِّفُوهُمَا فَوَجَدَا فِيهَا جِدَارًا يُرِيدُ أَن يَنقَضَّ فَأَقَامَهُۥ قَالَ لَوْ شِئْتَ لَتَّخَذْتَ عَلَيْهِ أَجْرًا

Amharic Translation - Africa Academy77. ሄዱም። ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች ዘንድ ደረሱ ከነዋሪዎች ምግብን ጠየቁ:: (እንደ እንግዳ) ማስተናገዳቸዉንም እምቢ አሉ:: በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን የቤት ግድግዳ አገኙ:: አቆመው:: ሙሳም «ብትፈልግ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَٰذَا فِرَاقُ بَيْنِى وَبَيْنِكَ سَأُنَبِّئُكَ بِتَأْوِيلِ مَا لَمْ تَسْتَطِع عَّلَيْهِ صَبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy78. አለም: «ይህ በእኔና ባንተ መካከል መለያያችን ነው። በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻለክበትን ፍቺ እነግርሃለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمَّا ٱلسَّفِينَةُ فَكَانَتْ لِمَسَٰكِينَ يَعْمَلُونَ فِى ٱلْبَحْرِ فَأَرَدتُّ أَنْ أَعِيبَهَا وَكَانَ وَرَآءَهُم مَّلِكٌ يَأْخُذُ كُلَّ سَفِينَةٍ غَصْبًا

Amharic Translation - Africa Academy79. «መርከቢቱማ በባህር ውስጥ ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች:: ከኋላቸው መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚወስድ ክፉ ንጉስ ነበረና እንዳይቀማቸው ላስነውራት ፈልጌ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلْغُلَٰمُ فَكَانَ أَبَوَاهُ مُؤْمِنَيْنِ فَخَشِينَآ أَن يُرْهِقَهُمَا طُغْيَٰنًا وَكُفْرًا

Amharic Translation - Africa Academy80. «ያ ወጣቱም ልጅ ወላጆቹ አማኞች ነበሩ:: ቢያድግ በትዕቢትና በክህደት ወላጆቹን የሚያስገድዳቸው መሆኑን ፈራን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَرَدْنَآ أَن يُبْدِلَهُمَا رَبُّهُمَا خَيْرًا مِّنْهُ زَكَوٰةً وَأَقْرَبَ رُحْمًا

Amharic Translation - Africa Academy81. «ጌታቸው በንጹሕነት ከእርሱ በላጭን፤ በእዝነትም ከእርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلْجِدَارُ فَكَانَ لِغُلَٰمَيْنِ يَتِيمَيْنِ فِى ٱلْمَدِينَةِ وَكَانَ تَحْتَهُۥ كَنزٌ لَّهُمَا وَكَانَ أَبُوهُمَا صَٰلِحًا فَأَرَادَ رَبُّكَ أَن يَبْلُغَآ أَشُدَّهُمَا وَيَسْتَخْرِجَا كَنزَهُمَا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ وَمَا فَعَلْتُهُۥ عَنْ أَمْرِى ذَٰلِكَ تَأْوِيلُ مَا لَمْ تَسْطِع عَّلَيْهِ صَبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy82. «ግድግዳዉም በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር:: በስሩም ለእነርሱ የሆነ የተቀበረ ድልብ ነበረና አባታቸዉም መልካም ሰው ነበር:: ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ:: በፈቃዴም አልሠራሁትም:: ይህ ያ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍቹ ነው።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَسْـَٔلُونَكَ عَن ذِى ٱلْقَرْنَيْنِ قُلْ سَأَتْلُوا۟ عَلَيْكُم مِّنْهُ ذِكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ዙልቀርነይንም ይጠይቁሀል:: «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን (ማስታወሻን) አነባለሁ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا مَكَّنَّا لَهُۥ فِى ٱلْأَرْضِ وَءَاتَيْنَٰهُ مِن كُلِّ شَىْءٍ سَبَبًا

Amharic Translation - Africa Academy84.እኛ እርሱን በምድር ላይ አስመቸነው:: በነገሩም ሁሉ መዳረሻ መንገድን ሰጠነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَتْبَعَ سَبَبًا

Amharic Translation - Africa Academy85. መንገድንም (ወደ ምዕራብ) ተከተለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ ٱلشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِى عَيْنٍ حَمِئَةٍ وَوَجَدَ عِندَهَا قَوْمًا قُلْنَا يَٰذَا ٱلْقَرْنَيْنِ إِمَّآ أَن تُعَذِّبَ وَإِمَّآ أَن تَتَّخِذَ فِيهِمْ حُسْنًا

Amharic Translation - Africa Academy86. ወደ ጸሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃማ ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት:: በአጠገቧም ህዝቦችን አገኘ:: «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም በመግደል ትቀጣለህ፤ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን ትሠራለህ።» አልነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَمَّا مَن ظَلَمَ فَسَوْفَ نُعَذِّبُهُۥ ثُمَّ يُرَدُّ إِلَىٰ رَبِّهِۦ فَيُعَذِّبُهُۥ عَذَابًا نُّكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy87. (እርሱም) አለ: «የበደለውንማ ወደፊት እንቀጣዋለን ከዚያ ወደ ጌታው ይመለሳል:: ብርቱንም ቅጣት ይቀጣዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا مَنْ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَلَهُۥ جَزَآءً ٱلْحُسْنَىٰ وَسَنَقُولُ لَهُۥ مِنْ أَمْرِنَا يُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy88. «ያመነና መልካምን ሥራ የሰራ ለእርሱ ከምንዳ በኩል መልካሚቱ ገነት አለችው:: ለእርሱም ከትዕዛዛችን ገርን ነገር እናዘዋለን።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَتْبَعَ سَبَبًا

Amharic Translation - Africa Academy89-. ከዚያ መንገድን (ወደ ምስራቅ) ቀጠለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ مَطْلِعَ ٱلشَّمْسِ وَجَدَهَا تَطْلُعُ عَلَىٰ قَوْمٍ لَّمْ نَجْعَل لَّهُم مِّن دُونِهَا سِتْرًا

Amharic Translation - Africa Academy90.ወደ ጸሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነርሱ ከበታቹ መከለያን ባላደረግንላቸው ህዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ وَقَدْ أَحَطْنَا بِمَا لَدَيْهِ خُبْرًا

Amharic Translation - Africa Academy91.ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: እርሱም ዘንድ ባለው ነገር ሁሉ በእርግጥ በእውቀት ከበብን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَتْبَعَ سَبَبًا

Amharic Translation - Africa Academy92. ከዚያ (ወደ ሰሜን አቅጣጫ) መንገድን ቀጠለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ بَيْنَ ٱلسَّدَّيْنِ وَجَدَ مِن دُونِهِمَا قَوْمًا لَّا يَكَادُونَ يَفْقَهُونَ قَوْلًا

Amharic Translation - Africa Academy93.በሁለቱ ጋራዎችም መካከል በደረሰ ጊዜ በአቅራቢያቸው ንግግርን ለማወቅ የማይቃረቡ ህዝቦችን አገኘ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ يَٰذَا ٱلْقَرْنَيْنِ إِنَّ يَأْجُوجَ وَمَأْجُوجَ مُفْسِدُونَ فِى ٱلْأَرْضِ فَهَلْ نَجْعَلُ لَكَ خَرْجًا عَلَىٰٓ أَن تَجْعَلَ بَيْنَنَا وَبَيْنَهُمْ سَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy94. «ዙልቀርነይን ሆይ! የዕጁጅና መዕጁጅ በምድር ላይ አበላሾች ናቸው። ግብር እናድርግልህና በእኛና በእነርሱ መካከል ግድብን ታደርግልን?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ مَا مَكَّنِّى فِيهِ رَبِّى خَيْرٌ فَأَعِينُونِى بِقُوَّةٍ أَجْعَلْ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُمْ رَدْمًا

Amharic Translation - Africa Academy95. (እርሱም) አለ: «ጌታዬ ያስመቸብኝ ሀብት ከናንተ ግብር በላጭ ነው:: እናም በጉልበት ብቻ እገዙኝ:: በእናንተና በእነርሱ መካከል ብርቱን ግድብ አደርጋለሁና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ءَاتُونِى زُبَرَ ٱلْحَدِيدِ حَتَّىٰٓ إِذَا سَاوَىٰ بَيْنَ ٱلصَّدَفَيْنِ قَالَ ٱنفُخُوا۟ حَتَّىٰٓ إِذَا جَعَلَهُۥ نَارًا قَالَ ءَاتُونِىٓ أُفْرِغْ عَلَيْهِ قِطْرًا

Amharic Translation - Africa Academy96. «የብረትን ታላላቅ ቁራጮች ስጡኝ።» አላቸው:: በሁለቱ ኮረብታዎች ጫፍ መካከልም ባስተካከለ ጊዜ «አናፉ» አላቸው። ብረቱን እሳትም ባደረገው ጊዜም: «የቀለጠውን ነሀስ ስጡኝ በእርሱ ላይ አፈስበታለሁና።» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا ٱسْطَٰعُوٓا۟ أَن يَظْهَرُوهُ وَمَا ٱسْتَطَٰعُوا۟ لَهُۥ نَقْبًا

Amharic Translation - Africa Academy97. የእጁጅና መእጁጅ ይህን መከላከያ ሊወጡት አልቻሉም:: ለእርሱ መሸንቆሩንም እንኳን አልቻሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ هَٰذَا رَحْمَةٌ مِّن رَّبِّى فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ رَبِّى جَعَلَهُۥ دَكَّآءَ وَكَانَ وَعْدُ رَبِّى حَقًّا

Amharic Translation - Africa Academy98. «ይህ ግድብ ከጌታዬ ችሮታዎች ነው:: የጌታዬ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እንኩትኩት ያደርገዋል:: የጌታዬም ቀጠሮ የተረጋገጠ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَكْنَا بَعْضَهُمْ يَوْمَئِذٍ يَمُوجُ فِى بَعْضٍ وَنُفِخَ فِى ٱلصُّورِ فَجَمَعْنَٰهُمْ جَمْعًا

Amharic Translation - Africa Academy99. በዚያን ቀን ከፊላቸውን በከፊሉ የሚቀላቀሉ አድርገን እንተዋቸዋለን:: በቀንዱም ይነፋል:: መሰብሰብንም እንሰበስባቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَرَضْنَا جَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ لِّلْكَٰفِرِينَ عَرْضًا

Amharic Translation - Africa Academy100. ገሀነምንም በዚያ ቀን ለከሓዲያን በጣም ማቅረብን እናቀርባታለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ كَانَتْ أَعْيُنُهُمْ فِى غِطَآءٍ عَن ذِكْرِى وَكَانُوا۟ لَا يَسْتَطِيعُونَ سَمْعًا

Amharic Translation - Africa Academy101.ለእነዚያ አይኖቻቸው ከግሳጼዬ በሽፋን ውስጥ ለነበሩትና መስማትንም የማይችሉ ለነበሩት እናቀርባታለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًا

Amharic Translation - Africa Academy102. እነዚያ በእኔ የካዱት ባሮቼን ከኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲያን መስተንግዶ አዘጋጅተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُم بِٱلْأَخْسَرِينَ أَعْمَٰلًا

Amharic Translation - Africa Academy103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا

Amharic Translation - Africa Academy104. «እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمْ وَلِقَآئِهِۦ فَحَبِطَتْ أَعْمَٰلُهُمْ فَلَا نُقِيمُ لَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَزْنًا

Amharic Translation - Africa Academy105. እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ተዓምራትና መገናኘት የካዱ ናቸው። ሥራዎቻቸዉም ተበላሸ:: ለእነርሱም በትንሳኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُمْ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُوا۟ وَٱتَّخَذُوٓا۟ ءَايَٰتِى وَرُسُلِى هُزُوًا

Amharic Translation - Africa Academy106. ነገሩ ይህ ነው:: በክህደታቸው፣ አንቀፆቼንና መልዕክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّٰتُ ٱلْفِرْدَوْسِ نُزُلًا

Amharic Translation - Africa Academy107. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ፊርደውስ የተባለው የገነት ክፍል ለእነርሱ መስፈሪያ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يَبْغُونَ عَنْهَا حِوَلًا

Amharic Translation - Africa Academy108. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች፤ ከእርሷም መዛወርን የማይፈልጉ ሲሆኑ መስፈሪያቸው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لَّوْ كَانَ ٱلْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَٰتِ رَبِّى لَنَفِدَ ٱلْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَٰتُ رَبِّى وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِۦ مَدَدًا

Amharic Translation - Africa Academy109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ባህሩ ለጌታዬ ቃላት መጻፊያ ቀለሞችን ቢሆን ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳ የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባህሩ ባለቀ ነበር።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَٰلِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

Amharic Translation - Africa Academy110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ መሰላችሁ ሰው ነኝ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል መልዕክት ወደ እኔ የሚወረድልኝ:: እናም ከጌታው ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ መልካም ሥራን ይሥራ:: በጌታዉም መገዛት ላይ አንድንም አያጋራ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70