caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Kahf፣ አንቀጽ 22

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 69 · 18:22

سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ قُل رَّبِّىٓ أَعْلَمُ بِعِدَّتِهِم مَّا يَعْلَمُهُمْ إِلَّا قَلِيلٌ فَلَا تُمَارِ فِيهِمْ إِلَّا مِرَآءً ظَٰهِرًا وَلَا تَسْتَفْتِ فِيهِم مِّنْهُمْ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (በጥርጣሬ) «ሦስት ናቸው፤ አራተኛቸው ውሻቸው ነው» ይላሉ፡፡ «አምስት ናቸው፤ ስድስተኛቸው ውሻቸው ነውም» ይላሉ፡፡ «ሰባት ናቸው፤ ስምንተኛቸውም ውሻቸው ነው» ይላሉም፡፡ «ጌታዬ ቁጥራቸውን ዐዋቂ ነው፡፡ ጥቂት (ሰው) እንጂ አያውቃቸውም» በላቸው፡፡ በእነሱም ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ (ጠልቀህ) አትከራከር፡፡ በእነሱም ጉዳይ ከነሱ (ከመጽሐፉ ሰዎች) አንድንም አትጠይቅ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70