وَٱصْبِرْ نَفْسَكَ مَعَ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ رَبَّهُم بِٱلْغَدَوٰةِ وَٱلْعَشِىِّ يُرِيدُونَ وَجْهَهُۥ وَلَا تَعْدُ عَيْنَاكَ عَنْهُمْ تُرِيدُ زِينَةَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُۥ عَن ذِكْرِنَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ وَكَانَ أَمْرُهُۥ فُرُطًا
Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነፍስህንም፤ ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን (ውዴታውን) የሚሹ ኾነው በጧትና በማታ ከሚግገዙት ጋር አስታግስ፡፡ የቅርቢቱንም ሕይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ ዓይኖችህ ከእነሱ (ወደ ሌላ) አይለፉ፡፡ ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ፡፡