وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا كَمَآءٍ أَنزَلْنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخْتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلْأَرْضِ فَأَصْبَحَ هَشِيمًا تَذْرُوهُ ٱلرِّيَٰحُ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ مُّقْتَدِرًا
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእነሱም የቅርቢቱን ሕይወት ምሳሌ አውሳላቸው፡፡ (እርሷ) ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር በቃይ እንደ ተቀላቀለበት (ከተዋበ በኋላ ደርቆ) ነፋሶችም የሚያበኑት ደቃቅ እንደ ኾነ ብጤ ናት፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡