وَعُرِضُوا۟ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفًّا لَّقَدْ جِئْتُمُونَا كَمَا خَلَقْنَٰكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍۭ بَلْ زَعَمْتُمْ أَلَّن نَّجْعَلَ لَكُم مَّوْعِدًا
Amharic Translation - Africa Academy48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።»
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየተሰለፉም ኾነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ፡፡ (ይባላሉም) «በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ (ራቁታችሁን) በእርግጥ መጣችሁን በእውነቱ ለእናንተ (ለመቀስቀሻ) ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር፡፡»