caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Kahf፣ አንቀጽ 29

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 69 · 18:29

وَقُلِ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ فَمَن شَآءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَآءَ فَلْيَكْفُرْ إِنَّآ أَعْتَدْنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا وَإِن يَسْتَغِيثُوا۟ يُغَاثُوا۟ بِمَآءٍ كَٱلْمُهْلِ يَشْوِى ٱلْوُجُوهَ بِئْسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتْ مُرْتَفَقًا

Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፡፡ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70