قُلِ ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا لَبِثُوا۟ لَهُۥ غَيْبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَبْصِرْ بِهِۦ وَأَسْمِعْ مَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِىٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِى حُكْمِهِۦٓ أَحَدًا
Amharic Translation - Africa Academy26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ብቻ የቆዩትን ልክ በትክክል አዋቂ ነው። የሰማያትና የምድር ሚስጢር የእሱ ብቻ ነዉ። እርሱ (አላህ) ሁሉን ተመልካች ሁሉን ሰሚ መሆኑ ይግረምህ። ለእነርሱ ከእርሱ በስተቀር ምንም ወዳጅ የላቸዉም:: በፍርዱም አንድንም አያጋራም።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«አላህ የቆዩትን ልክ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ምስጢር የእሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱ ምን ያይ! ምን ይሰማም! ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ በፍርዱም አንድንም አያጋራም፡፡