وَتَرَى ٱلشَّمْسَ إِذَا طَلَعَت تَّزَٰوَرُ عَن كَهْفِهِمْ ذَاتَ ٱلْيَمِينِ وَإِذَا غَرَبَت تَّقْرِضُهُمْ ذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَهُمْ فِى فَجْوَةٍ مِّنْهُ ذَٰلِكَ مِنْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ مَن يَهْدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلْمُهْتَدِ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ وَلِيًّا مُّرْشِدًا
Amharic Translation - Africa Academy17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqፀሐይንም በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ፡፡ በገባችም ጊዜ እነርሱ ከእርሱ በሰፊው ስፍራ ውስጥ ኾነው ሳሉ ወደ ግራ በኩል ትተዋቸዋለች፡፡ ይህ ከአላህ ተዓምራቶች ነው፡፡ አላህ የሚያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው፡፡ የሚያጠመውም ሰው ለርሱ አቅኝን ረዳት አታገኝለትም፡፡