فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَيَآ أَهْلَ قَرْيَةٍ ٱسْتَطْعَمَآ أَهْلَهَا فَأَبَوْا۟ أَن يُضَيِّفُوهُمَا فَوَجَدَا فِيهَا جِدَارًا يُرِيدُ أَن يَنقَضَّ فَأَقَامَهُۥ قَالَ لَوْ شِئْتَ لَتَّخَذْتَ عَلَيْهِ أَجْرًا
Amharic Translation - Africa Academy77. ሄዱም። ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች ዘንድ ደረሱ ከነዋሪዎች ምግብን ጠየቁ:: (እንደ እንግዳ) ማስተናገዳቸዉንም እምቢ አሉ:: በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን የቤት ግድግዳ አገኙ:: አቆመው:: ሙሳም «ብትፈልግ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር።» አለው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqኼዱም፡፡ ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች በመጡም ጊዜ ነዋሪዎቿን ምግብን ጠየቁ፡፡ ከማስተናገዳቸውም እምቢ አሉ፡፡ በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን ግድግዳ አገኙ፡፡ (ኸደር) አቆመውም፡፡ (ሙሳም) «በሻህ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር» አለው፡፡