حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ مَغْرِبَ ٱلشَّمْسِ وَجَدَهَا تَغْرُبُ فِى عَيْنٍ حَمِئَةٍ وَوَجَدَ عِندَهَا قَوْمًا قُلْنَا يَٰذَا ٱلْقَرْنَيْنِ إِمَّآ أَن تُعَذِّبَ وَإِمَّآ أَن تَتَّخِذَ فِيهِمْ حُسْنًا
Amharic Translation - Africa Academy86. ወደ ጸሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃማ ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት:: በአጠገቧም ህዝቦችን አገኘ:: «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም በመግደል ትቀጣለህ፤ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን ትሠራለህ።» አልነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት፡፡ ባጠገቧም ሕዝቦችን አገኘ፡፡ «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም (በመግደል) ትቀጣለህ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን (መማረክን) ትሠራለህ» አልነው፡፤