caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Kahf፣ አንቀጽ 19

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 69 · 18:19

وَكَذَٰلِكَ بَعَثْنَٰهُمْ لِيَتَسَآءَلُوا۟ بَيْنَهُمْ قَالَ قَآئِلٌ مِّنْهُمْ كَمْ لَبِثْتُمْ قَالُوا۟ لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ قَالُوا۟ رَبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا لَبِثْتُمْ فَٱبْعَثُوٓا۟ أَحَدَكُم بِوَرِقِكُمْ هَٰذِهِۦٓ إِلَى ٱلْمَدِينَةِ فَلْيَنظُرْ أَيُّهَآ أَزْكَىٰ طَعَامًا فَلْيَأْتِكُم بِرِزْقٍ مِّنْهُ وَلْيَتَلَطَّفْ وَلَا يُشْعِرَنَّ بِكُمْ أَحَدًا

Amharic Translation - Africa Academy19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእንዲሁም በመካከላቸው እንዲጠያየቁ ቀሰቀስናቸው፡፡ ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያክል ቆያችሁ?» አለ፡፡ «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን» አሉ፡፡ «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ ዐዋቂ ነው፡፡ ከዚህችም ብራችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ፡፡ ከምግቦቿ የትኛዋ ንጹሕ መሆኗንም ይመልከት፡፡ ከእርሱም (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ፡፡ ቀስም ይበል፡፡ በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ» አሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70