caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Maryam مريم

98 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 44

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ كٓهيعٓصٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ካፍ፤ ሃ፤ ያ፤ ዐይን፤ ሷድ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذِكْرُ رَحْمَتِ رَبِّكَ عَبْدَهُۥ زَكَرِيَّآ

Amharic Translation - Africa Academy2. ይህ ጌታህ ባርያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَآءً خَفِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy3. ጌታውን የሚስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ إِنِّى وَهَنَ ٱلْعَظْمُ مِنِّى وَٱشْتَعَلَ ٱلرَّأْسُ شَيْبًا وَلَمْ أَكُنۢ بِدُعَآئِكَ رَبِّ شَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy4. (እንዲህም) አለ: «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴም ደከመ:: ራሴም በሽበት ተንቀለቀለ። ጌታዬ ሆይ! አንተንም በመለመኔ፤ ምንጊዜም ዕድለ ቢስ እልሆንኩም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنِّى خِفْتُ ٱلْمَوَٰلِىَ مِن وَرَآءِى وَكَانَتِ ٱمْرَأَتِى عَاقِرًا فَهَبْ لِى مِن لَّدُنكَ وَلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy5. «እኔም ከበኋላዬ (ከሞትኩ በኋላ) ዘመዶቼን (ከእምነት እንዳይወጡ) ፈራሁ:: ሚስቴም መካን ነበረች:: ስለዚህ ካንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَرِثُنِى وَيَرِثُ مِنْ ءَالِ يَعْقُوبَ وَٱجْعَلْهُ رَبِّ رَضِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy6. «የሚወርሰኝ ከየዕቁብ ቤተሰቦችም የእምነትን ሃላፊነት የሚወርስን ልጅ ስጠኝ:: ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰزَكَرِيَّآ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ ٱسْمُهُۥ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَل لَّهُۥ مِن قَبْلُ سَمِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy7. «ዘከሪያ ሆይ! እኛ ስሙ የሕያ በሆነና ከዚያ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌ وَكَانَتِ ٱمْرَأَتِى عَاقِرًا وَقَدْ بَلَغْتُ مِنَ ٱلْكِبَرِ عِتِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy8. «ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን እኔም ከእርጅና የተነሳ ድርቀትን የደረስኩ ስሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ كَذَٰلِكَ قَالَ رَبُّكَ هُوَ عَلَىَّ هَيِّنٌ وَقَدْ خَلَقْتُكَ مِن قَبْلُ وَلَمْ تَكُ شَيْـًٔا

Amharic Translation - Africa Academy9. (ጅብሪልም) አለ: «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው። ጌታህ ‹ከዚህ በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስሆን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው።› ብሏል።»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ ٱجْعَل لِّىٓ ءَايَةً قَالَ ءَايَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ ٱلنَّاسَ ثَلَٰثَ لَيَالٍ سَوِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy10. እርሱም «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ ምልክት አድርግልኝ።» አለ። «ምልክትህ (ጤናማ ሆነህ ሳለህ) ሶስት ሌሊት ከነቀናቸው ሰዎችን ማነጋገር አለመቻልህ ነው።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوْمِهِۦ مِنَ ٱلْمِحْرَابِ فَأَوْحَىٰٓ إِلَيْهِمْ أَن سَبِّحُوا۟ بُكْرَةً وَعَشِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy11. እርሱም ከምኩራቡ ወደ ህዝቦቹ ወጣ:: ጧትና ማታ ጌታችሁን አውሱ አጥሩትም በማለትም ወደ እነርሱ ጠቀሰ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰيَحْيَىٰ خُذِ ٱلْكِتَٰبَ بِقُوَّةٍ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْحُكْمَ صَبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy12. «የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ።» አልነው:: ጥበብንም በሕጻንነቱ ሰጠነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَحَنَانًا مِّن لَّدُنَّا وَزَكَوٰةً وَكَانَ تَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy13. ከእኛም የሆነን ርህራሄና ንጽህናንም (ሰጠነው):: ጥንቁቅም ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبَرًّۢا بِوَٰلِدَيْهِ وَلَمْ يَكُن جَبَّارًا عَصِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy14. ለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር:: ትዕቢተኛና አመጸኛም አልነበረም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَلَٰمٌ عَلَيْهِ يَوْمَ وُلِدَ وَيَوْمَ يَمُوتُ وَيَوْمَ يُبْعَثُ حَيًّا

Amharic Translation - Africa Academy15. በተወለደበት ቀንና በሚሞትበት ቀን ህያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مَرْيَمَ إِذِ ٱنتَبَذَتْ مِنْ أَهْلِهَا مَكَانًا شَرْقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መርየም ከቤተሰቧ ወደ ምስራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ የሆነውን ታሪኳን በመጽሐፉ ውስጥ አውሳ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَآ إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy17. ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች:: መንፈሳችንንም (መልዐኩ ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን:: ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ إِنِّىٓ أَعُوذُ بِٱلرَّحْمَٰنِ مِنكَ إِن كُنتَ تَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy18. «ካንተ በአር-ረህማን እጠበቃለሁ። ጌታህን ፈሪ ከሆንክ (አትቅረበኝ)።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنَّمَآ أَنَا۠ رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَٰمًا زَكِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy19. «እኔ ንጹሕ የሆነን ልጅ ላንቺ ልሰጥ የመጣሁ የጌታሽ መልዕክተኛ ነኝ።» አላት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy20. «በጋብቻ አንድም ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራ ዝሙትኛ ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَىَّ هَيِّنٌ وَلِنَجْعَلَهُۥٓ ءَايَةً لِّلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِّنَّا وَكَانَ أَمْرًا مَّقْضِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy21. (መልአኩም) «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው የሚፈጸመው። ጌታሽ ‹እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው:: ለሰዎችም ተዓምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሰራን፤ ነገሩ የተወሰነም ነው።› ብሏል።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَحَمَلَتْهُ فَٱنتَبَذَتْ بِهِۦ مَكَانًا قَصِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy22. ወዲያውኑም አረገዘችው:: እርሱንም በሆድዋ ይዛው ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَجَآءَهَا ٱلْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ ٱلنَّخْلَةِ قَالَتْ يَٰلَيْتَنِى مِتُّ قَبْلَ هَٰذَا وَكُنتُ نَسْيًا مَّنسِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy23. ምጡ ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት:: እርሷም «ወይኔ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩና የተረሳሁ በሆንኩ።» አለች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَنَادَىٰهَا مِن تَحْتِهَآ أَلَّا تَحْزَنِى قَدْ جَعَلَ رَبُّكِ تَحْتَكِ سَرِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy24. ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት: «አትዘኝ። ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓልና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُزِّىٓ إِلَيْكِ بِجِذْعِ ٱلنَّخْلَةِ تُسَٰقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy25. «የዘምባባይቱን ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዢው:: በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ያረግፍልሻልና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكُلِى وَٱشْرَبِى وَقَرِّى عَيْنًا فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ ٱلْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِىٓ إِنِّى نَذَرْتُ لِلرَّحْمَٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ ٱلْيَوْمَ إِنسِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy26. «ብይ፤ ጠጭም። ተደሰችም ከሰዎች አንድንም ብታይ እኔ ለአዛኙ አምላክ ዝምታን ተስያለሁ:: እናም ዛሬ ማንንም ሰው በፍጹም አላነጋግርም በይ።» አላት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًٔا فَرِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy27. እርሱን ተሸክማው ወደ ዘመዶቿ መጣች (እንዲህም) አሏት: «መርየም ሆይ! ከባድ ነገርን በእርግጥ ፈጸምሽ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy28. «አንቺ የሃሩን እህት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም:: እናትሽም አመንዝራ ዝሙተኛ አልነበረችም።» አሏት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَشَارَتْ إِلَيْهِ قَالُوا۟ كَيْفَ نُكَلِّمُ مَن كَانَ فِى ٱلْمَهْدِ صَبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy29. እርሷም ወደ ህፃኑ አመለከተች:: እነርሱም «በአንቀልባ ያለን ህፃን እንዴት እናናግራለን?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ إِنِّى عَبْدُ ٱللَّهِ ءَاتَىٰنِىَ ٱلْكِتَٰبَ وَجَعَلَنِى نَبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy30. ህፃኑም አለ: «እኔ የአላህ አገልጋይ ነኝ፤ መጽሐፍን ሰጥቶኛል። ነብይም አድርጎኛል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلَنِى مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَٰنِى بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

Amharic Translation - Africa Academy31. «በየትም ስፍራ ብሆን የተባረኩኝ አድርጎኛል። በህይወትም እስካለሁ ሶላትንና ዘካን አዞኛል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبَرًّۢا بِوَٰلِدَتِى وَلَمْ يَجْعَلْنِى جَبَّارًا شَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy32. «ለእናቴም ታዛዥ አድርጎኛል:: ትዕቢተኛ እድለቢስ አላደረገኝም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلسَّلَٰمُ عَلَىَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا

Amharic Translation - Africa Academy33. «በተወለድሁበት ቀን በምሞትበት ቀንና ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን ሰላም በእኔ ላይ ይስፈን።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. የመርየም ልጅ ዒሳ ይሀው ነው፤ ያ በእርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ይህ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ سُبْحَٰنَهُۥٓ إِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Amharic Translation - Africa Academy35. ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም:: ከጉድለት ሁሉ ጠራ:: አንድን ነገር በወሰነ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ሁን» ብቻ ነው:: ወዲያዉም ይሆናል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy36. ዒሳ ለህዝቦቹ «አላህ የእኔም ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነውና ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱخْتَلَفَ ٱلْأَحْزَابُ مِنۢ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن مَّشْهَدِ يَوْمٍ عَظِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy37. ከመካከላቸዉም አንጃዎች በእርሱ ነገር ላይ ተለያዩ:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ክስተት ወዮላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَسْمِعْ بِهِمْ وَأَبْصِرْ يَوْمَ يَأْتُونَنَا لَٰكِنِ ٱلظَّٰلِمُونَ ٱلْيَوْمَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy38. ወደ እኛ በሚመጡ ቀን ምን ያህል ሰሚ ምን ያህል ተመልካች አደረጋቸው:: ግን አመጸኞች በዳዮች ዛሬ በዚህች ዓለም በግልጽ ስህተትና ጥመት ውስጥ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنذِرْهُمْ يَوْمَ ٱلْحَسْرَةِ إِذْ قُضِىَ ٱلْأَمْرُ وَهُمْ فِى غَفْلَةٍ وَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭትን ቀን አስፈራራቸው እነርሱ አሁን በመዘንጋት ላይ ናቸው:: እነርሱ አያምኑምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّا نَحْنُ نَرِثُ ٱلْأَرْضَ وَمَنْ عَلَيْهَا وَإِلَيْنَا يُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy40. ምድርንና በእርሷም ላይ ያለውን ፍጡር ሁሉ እኛ እንወርሳለን:: ወደ እኛም ይመለሳሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِبْرَٰهِيمَ إِنَّهُۥ كَانَ صِدِّيقًا نَّبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምን አውሳ:: እርሱም በጣም እውነተኛ ነብይ ነበርና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَٰٓأَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِى عَنكَ شَيْـًٔا

Amharic Translation - Africa Academy42. ለአባቱ (እንዲህ) ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ላንተም ምንንም የማይጠቅምህን (የማይፈይድህን) ጣዖት ለምን ታመልካለህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَبَتِ إِنِّى قَدْ جَآءَنِى مِنَ ٱلْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَٱتَّبِعْنِىٓ أَهْدِكَ صِرَٰطًا سَوِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy43. «አባቴ ሆይ! እኔ አንተ ያልደረሰህን እውቀት መጥቶልኛልና ተከተለኝ:: ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَبَتِ لَا تَعْبُدِ ٱلشَّيْطَٰنَ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy44. «አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትገዛ \አታምልክ\:: ሰይጣን ለአር-ረህማን አመጸኛ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَبَتِ إِنِّىٓ أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ ٱلرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَٰنِ وَلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy45. «አባቴ ሆይ! እኔ የአር-ረህማን ቅጣት ሊያገኝህ እና ከዚያ የሰይጣን ጓደኛ ልትሆን እፈራለሁ::»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ ءَالِهَتِى يَٰٓإِبْرَٰهِيمُ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ وَٱهْجُرْنِى مَلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy46. አባቱም «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን? ከዚህ ተግባርህ ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ:: ረዥም ጊዜንም ተወኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ سَلَٰمٌ عَلَيْكَ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّىٓ إِنَّهُۥ كَانَ بِى حَفِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy47. ኢብራሂምም አለ: «ደህና ሁን (ሰላም ላንተ ይሁን):: ከጌታዬ ምህረትን እለምንልሃለሁ:: እርሱ ለእኔ በጣም ሩህሩህ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَعْتَزِلُكُمْ وَمَا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَأَدْعُوا۟ رَبِّى عَسَىٰٓ أَلَّآ أَكُونَ بِدُعَآءِ رَبِّى شَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy48. «እናንተንና ከአላህ ሌላ የምትገዙትን ሁሉ እርቃለሁ:: ጌታዬንም ብቻ እገዛለሁ፤ ጌታዬን በመገዛት የማፍር አለመሆኔን እከጅላለሁ (ተስፋ አደርጋለሁ)።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَمَّا ٱعْتَزَلَهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَهَبْنَا لَهُۥٓ إِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَكُلًّا جَعَلْنَا نَبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy49. እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በራቀ ጊዜ ኢስሐቅንና የዕቁብን ሰጠነው:: ሁለቱንም ነብይ አደረግናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوَهَبْنَا لَهُم مِّن رَّحْمَتِنَا وَجَعَلْنَا لَهُمْ لِسَانَ صِدْقٍ عَلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy50. ለእነርሱም ከችሮታችን ሰጠናቸው:: ለእነርሱም ከፍ ያለ ምስጉን ዝናን አደረግንላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًا وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ሙሳን አውሳ:: እርሱ ምርጥ ነበርና:: መልዕክተኛ ነብይም ነበርና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy52. ከጡር ጋራ በስተቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው። በሚስጥር ያነጋገርነውም ስንሆን አቀረብነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَوَهَبْنَا لَهُۥ مِن رَّحْمَتِنَآ أَخَاهُ هَٰرُونَ نَبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy53. ከእዝነታችንም (ከችሮታችንም) ወንድሙን ሃሩንን ነብይ አደረግንለት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِسْمَٰعِيلَ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢስማዒልንም አውሳ:: እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرْضِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy55. ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር:: በጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِدْرِيسَ إِنَّهُۥ كَانَ صِدِّيقًا نَّبِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢድሪስንም አውሳ:: እርሱ እውነተኛ ነብይ ነበርና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَفَعْنَٰهُ مَكَانًا عَلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy57. (ኢድሪስን) ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِن ذُرِّيَّةِ ءَادَمَ وَمِمَّنْ حَمَلْنَا مَعَ نُوحٍ وَمِن ذُرِّيَّةِ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْرَٰٓءِيلَ وَمِمَّنْ هَدَيْنَا وَٱجْتَبَيْنَآ إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُ ٱلرَّحْمَٰنِ خَرُّوا۟ سُجَّدًا وَبُكِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy58. እነዚህ (አሥሩ) እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሰላቸው ከነብያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር በመርከቢቱ ላይ ከጫንናቸዉም ዘሮች ከኢብራሂምና ከኢስራኢልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸዉም የሆኑት የአር-ረህማን አናቅጽ በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ሆነው ወደ መሬት የሚወድቁ (የሚደፉ) ናቸው። {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَخَلَفَ مِنۢ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلشَّهَوَٰتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

Amharic Translation - Africa Academy59. ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ትውልዶች ተተኩ:: «ገይ» የሚባልን የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا فَأُو۟لَٰٓئِكَ يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ شَيْـًٔا

Amharic Translation - Africa Academy60. ግና ከእነርሱ የተጸጸቱ በአላህ ያመኑ በጎንም ስራ የሰሩ ሰዎች ወደ ገነት ይገባሉ:: አንዳችንም አይበደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

جَنَّٰتِ عَدْنٍ ٱلَّتِى وَعَدَ ٱلرَّحْمَٰنُ عِبَادَهُۥ بِٱلْغَيْبِ إِنَّهُۥ كَانَ وَعْدُهُۥ مَأْتِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy61. የመኖሪያን ገነቶች ያችን አር-ረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ:: እርሱ ተስፋው ሁልጊዜም ተፈጻሚ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا إِلَّا سَلَٰمًا وَلَهُمْ رِزْقُهُمْ فِيهَا بُكْرَةً وَعَشِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy62. በእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም:: ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تِلْكَ ٱلْجَنَّةُ ٱلَّتِى نُورِثُ مِنْ عِبَادِنَا مَن كَانَ تَقِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy63. ይህ ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለሆኑት ሁሉ የምናወርሳት ገነት ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy64. (ጂብሪልም ለነቢዩ) «በጌታህ ትእዛዝ እንጂ አንወርድም:: በፊታችን፤ በኋላችንና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ጌታህም ረሺ አይደለም።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَٱعْبُدْهُ وَٱصْطَبِرْ لِعِبَٰدَتِهِۦ هَلْ تَعْلَمُ لَهُۥ سَمِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy65. እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው:: እርሱን በመገዛትም ላይ ታገሥ:: ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُ ٱلْإِنسَٰنُ أَءِذَا مَا مِتُّ لَسَوْفَ أُخْرَجُ حَيًّا

Amharic Translation - Africa Academy66. ሰው «በሞትኩ ጊዜ ወደ ፊት ህያው ሆኜ ከመቃብር እወጣለሁን?» ይላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَا يَذْكُرُ ٱلْإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقْنَٰهُ مِن قَبْلُ وَلَمْ يَكُ شَيْـًٔا

Amharic Translation - Africa Academy67. ሰው ከዚህ በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲሆን የፈጠርነው መሆኑን አያስታውስምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَوَرَبِّكَ لَنَحْشُرَنَّهُمْ وَٱلشَّيَٰطِينَ ثُمَّ لَنُحْضِرَنَّهُمْ حَوْلَ جَهَنَّمَ جِثِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን:: ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ሆነው እናቀርባቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ لَنَنزِعَنَّ مِن كُلِّ شِيعَةٍ أَيُّهُمْ أَشَدُّ عَلَى ٱلرَّحْمَٰنِ عِتِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy69. ከዚያም ከየቡድኖቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን በአር-ረህማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የሆነውን መዘን እናወጣለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ لَنَحْنُ أَعْلَمُ بِٱلَّذِينَ هُمْ أَوْلَىٰ بِهَا صِلِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy70. ከዚያም እነዚያን በእርሷ ለመቃጠል ይበልጥ ተገቢ የሆኑትን ሰዎች እናውቃለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy71. (ሰዎች ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ ገሀነም የማይወርድ አንድም የለም:: መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታና አይቀሬ ዉሳኔ ነው:: {1}

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ نُنَجِّى ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ وَّنَذَرُ ٱلظَّٰلِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy72. ከዚያም እነዚያን አላህን የፈሩትን ብቻ እናድናለን:: አመጸኞችን ደግሞ የተንበረከኩ ሆነው በውስጧ እንተዋቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَىُّ ٱلْفَرِيقَيْنِ خَيْرٌ مَّقَامًا وَأَحْسَنُ نَدِيًّا

Amharic Translation - Africa Academy73. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ማስረጃዎች ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያው የበለጠውና ሸንጎዉም ይበልጥ የሚያምረው ማንኛው ነው?» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّن قَرْنٍ هُمْ أَحْسَنُ أَثَٰثًا وَرِءْيًا

Amharic Translation - Africa Academy74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች እነርሱ በእይታ በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَن كَانَ فِى ٱلضَّلَٰلَةِ فَلْيَمْدُدْ لَهُ ٱلرَّحْمَٰنُ مَدًّا حَتَّىٰٓ إِذَا رَأَوْا۟ مَا يُوعَدُونَ إِمَّا ٱلْعَذَابَ وَإِمَّا ٱلسَّاعَةَ فَسَيَعْلَمُونَ مَنْ هُوَ شَرٌّ مَّكَانًا وَأَضْعَفُ جُندًا

Amharic Translation - Africa Academy75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በስህተት ውስጥ የሆነውን አዛኙ አምላክ ለእርሱ ጥመትን ይጨምርለት (ማዘግየትን ያዘግየው::) የሚዛትባቸውንም ቅጣትን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ እርሱ ስፍራው መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَزِيدُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ٱهْتَدَوْا۟ هُدًى وَٱلْبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيْرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابًا وَخَيْرٌ مَّرَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy76. እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል:: መልካም ቀሪ ስራዎች በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በመመለሻነትም የተሻሉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتَ ٱلَّذِى كَفَرَ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالًا وَوَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በአናቅጻችን የካደውንና «በትንሣኤ ቀን ገንዘብም ሆነ ልጅ በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَطَّلَعَ ٱلْغَيْبَ أَمِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحْمَٰنِ عَهْدًا

Amharic Translation - Africa Academy78. ሩቁን ምስጢር አወቀን ? ወይስ አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا سَنَكْتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُۥ مِنَ ٱلْعَذَابِ مَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy79. ከዚህ አቋሙ ይታቀብ:: አይሰጠዉም:: የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን:: ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَرِثُهُۥ مَا يَقُولُ وَيَأْتِينَا فَرْدًا

Amharic Translation - Africa Academy80. አለኝ የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን ወደ እኛም ብቻውን ሆኖ ይመጣል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةً لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّا

Amharic Translation - Africa Academy81. ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲሆኗቸው ያዙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَلَّا سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا

Amharic Translation - Africa Academy82. ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ (ይታቀቡ):: መገዛታቸውን በእርግጥ ወደፊት ይከዷቸዋል:: በእነርሱም ላይ ተቃራኒ (ባላጋራ) ይሆኑባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ أَنَّآ أَرْسَلْنَا ٱلشَّيَٰطِينَ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ تَؤُزُّهُمْ أَزًّا

Amharic Translation - Africa Academy83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰይጣናትን በከሓዲያን ላይ በመጥፎ ሥራ የሚገፋፏቸው ሲሆኑ የላክንባቸው መሆናችንን አላየህምን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تَعْجَلْ عَلَيْهِمْ إِنَّمَا نَعُدُّ لَهُمْ عَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም መቀጣት ላይ አትቸኩል:: ለእነርሱ ቀንን እንቆጥርላቸዋለንና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَ نَحْشُرُ ٱلْمُتَّقِينَ إِلَى ٱلرَّحْمَٰنِ وَفْدًا

Amharic Translation - Africa Academy85. ትክክለኛ አማኞችን የተከበሩ ቡድኖች ሆነው ወደ አዛኙ አምላክ የምንሰበሰብበትንና:

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَنَسُوقُ ٱلْمُجْرِمِينَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ وِرْدًا

Amharic Translation - Africa Academy86. ከሓዲያንን የተጠሙ ሆነው ወደገሀነም የምንነዳበትን ቀን አስታውስ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَمْلِكُونَ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَنِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحْمَٰنِ عَهْدًا

Amharic Translation - Africa Academy87. አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ቢሆን እንጂ ሌሎች ማማለድን አይችሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحْمَٰنُ وَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy88. አጋሪዎች «አዛኙ አምላክ አላህ ልጅ ወለደ።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ جِئْتُمْ شَيْـًٔا إِدًّا

Amharic Translation - Africa Academy89.(አጋሪዎች ሆይ!) እጅግ ከባድና መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْهُ وَتَنشَقُّ ٱلْأَرْضُ وَتَخِرُّ ٱلْجِبَالُ هَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy90. ከዚህ ንግግራቸው ሰማያት ሊቀደዱ፤ ምድርም ልትሰነጠቅ፤ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَن دَعَوْا۟ لِلرَّحْمَٰنِ وَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy91. ይህም ለአዛኙ አምላክ ልጅ አለው ስላሉ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا يَنۢبَغِى لِلرَّحْمَٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا

Amharic Translation - Africa Academy92. አዛኙ ጌታ ልጅን መያዝ አይገባዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن كُلُّ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ إِلَّآ ءَاتِى ٱلرَّحْمَٰنِ عَبْدًا

Amharic Translation - Africa Academy93. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን (ለአር-ረህማን) ለአዛኙ ጌታ ባሪያ ሆነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ أَحْصَىٰهُمْ وَعَدَّهُمْ عَدًّا

Amharic Translation - Africa Academy94. አላህ በእርግጥ በዕውቀቱ ከቧቸዋል:: መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكُلُّهُمْ ءَاتِيهِ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فَرْدًا

Amharic Translation - Africa Academy95. ሁሉም በትንሳኤ ቀን ለየብቻ ሆነው ወደ እርሱ መጪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَيَجْعَلُ لَهُمُ ٱلرَّحْمَٰنُ وُدًّا

Amharic Translation - Africa Academy96. እነዚያ በአላህ ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ አር-ረህማን ለእነርሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِنَّمَا يَسَّرْنَٰهُ بِلِسَانِكَ لِتُبَشِّرَ بِهِ ٱلْمُتَّقِينَ وَتُنذِرَ بِهِۦ قَوْمًا لُّدًّا

Amharic Translation - Africa Academy97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምላስህም ቁርኣንን ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆችን ልታበስርበትና በእርሱ ተከራካሪ ሕዝቦችን ልታስፈራራበት ዘንድ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّن قَرْنٍ هَلْ تُحِسُّ مِنْهُم مِّنْ أَحَدٍ أَوْ تَسْمَعُ لَهُمْ رِكْزًۢا

Amharic Translation - Africa Academy98. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙ ትውልዶችን አጥፍተናል:: ከእነርሱ አንድን እንኳ ታያለህን? ወይንስ ለእነርሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን? (አታይም፣ አጸማምም)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70