caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Takwir التكوير

29 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 7

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا ٱلشَّمْسُ كُوِّرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy1. ጸሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلنُّجُومُ ٱنكَدَرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy2. ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْجِبَالُ سُيِّرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy3. ተራራዎች በተናዱ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْعِشَارُ عُطِّلَتْ

Amharic Translation - Africa Academy4. የአስር ወር እርጉዝ ግመሎች ያለጠባቂ በተተው ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْوُحُوشُ حُشِرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy5. አራዊቶችም በተሰበሰቡ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْبِحَارُ سُجِّرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy6. ባህሮችም በተቀጣጠሉ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلنُّفُوسُ زُوِّجَتْ

Amharic Translation - Africa Academy7. ነፍሶች በተቆራኙ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْمَوْءُۥدَةُ سُئِلَتْ

Amharic Translation - Africa Academy8. ከነሕይወቷ የተቀበረችው ሴት ልጅም በተጠየቀች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بِأَىِّ ذَنۢبٍ قُتِلَتْ

Amharic Translation - Africa Academy9. በምን ወንጀል እንደተገደለች፤ በተጠየቀች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلصُّحُفُ نُشِرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy10. ጹሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلسَّمَآءُ كُشِطَتْ

Amharic Translation - Africa Academy11. ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْجَحِيمُ سُعِّرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy12. ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ٱلْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ

Amharic Translation - Africa Academy13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّآ أَحْضَرَتْ

Amharic Translation - Africa Academy14. ነፍስ (ሁሉ ከስራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَآ أُقْسِمُ بِٱلْخُنَّسِ

Amharic Translation - Africa Academy15. (ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: ተመላሾች በሆኑት (ከዋክብት) እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلْجَوَارِ ٱلْكُنَّسِ

Amharic Translation - Africa Academy16. አንዳንድ ጊዜ ሂያጆች በሌላ ጊዜ ገቢዎች በሆኑት

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ

Amharic Translation - Africa Academy17. በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ

Amharic Translation - Africa Academy18. በንጋትም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ እምላለሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy19. እርሱ (ቁርኣን) የተከበረው መልዕክተኛ ጅብሪል ቃል ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذِى قُوَّةٍ عِندَ ذِى ٱلْعَرْشِ مَكِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy20. የኃይል ባለቤት የሆነ፤ ከዙፋኑ ባለቤት ዘንድም ባለሟል የሆነ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy21. በዚያ ስፍራ ትዕዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝም የሆነው (መልዕክተኛ ቃል ነው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

Amharic Translation - Africa Academy22. ነብያችሁም በፍጹም እብድ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ رَءَاهُ بِٱلْأُفُقِ ٱلْمُبِينِ

Amharic Translation - Africa Academy23. በግልጹ አድማስ ላይ ሆኖ (ጅብሪልን) በእርግጥ አይቶታል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا هُوَ عَلَى ٱلْغَيْبِ بِضَنِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy24. እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَٰنٍ رَّجِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy25. (ቁርኣን) የርጉም ሰይጣን ቃልም አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ታዲያ (ይህንን በተመለከተ) ወዴት ትሄዳላቸሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy27. እርሱ የዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِمَن شَآءَ مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ

Amharic Translation - Africa Academy28. ከናንተ መካከል ቀጥተኛ መሆንን ለፈለገ (ሁሉ መገሰጫ) ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. (ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70