ሱረቱ Al-Ma'aarij المعارج
44 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 79
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ سَأَلَ سَآئِلٌۢ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ
Amharic Translation - Africa Academy1. ወዳቂ (ተከሳች) ከሆነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّلْكَٰفِرِينَ لَيْسَ لَهُۥ دَافِعٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. ከሓዲያን ላይ (ወዳቂ ከሆነው) ለእርሱ መላሽ የለዉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِّنَ ٱللَّهِ ذِى ٱلْمَعَارِجِ
Amharic Translation - Africa Academy3. የ (ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከሆነው አላህ (መላሽ የለዉም)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَعْرُجُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيْهِ فِى يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُۥ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ
Amharic Translation - Africa Academy4. መላዕክትና መንፈሱም ልኩ ሀምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ (ይወጣሉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy5. መልካምን ትዕግስት ታገስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُۥ بَعِيدًا
Amharic Translation - Africa Academy6. እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገው ያዩታል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَرَىٰهُ قَرِيبًا
Amharic Translation - Africa Academy7. እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلْمُهْلِ
Amharic Translation - Africa Academy8. ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትሆንበት ቀን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَتَكُونُ ٱلْجِبَالُ كَٱلْعِهْنِ
Amharic Translation - Africa Academy9. ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ንፋስ) እንደበተነውና እንደሚያበረው በሚሆኑበት ቀን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَسْـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy10. ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን መላሽ የለዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُبَصَّرُونَهُمْ يَوَدُّ ٱلْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِى مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍۭ بِبَنِيهِ
Amharic Translation - Africa Academy11. (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፤ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ቤዛ ሊያደርግ ይመኛል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ
Amharic Translation - Africa Academy12. በሚስቱም በወንድሙም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِى تُـْٔوِيهِ
Amharic Translation - Africa Academy13. በዚያች በምታስጠጋው ጎሳውም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ
Amharic Translation - Africa Academy14. በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያ ሊያድነው (ይመኛል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّآ إِنَّهَا لَظَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy15. ይተው፤እርሷ (እሳቲቱ) ነዲድ እሳት ናት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy16. የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትሆን፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَدْعُوا۟ مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy17. (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደ እርሷ) ትጠራለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy18. ገንዘብን የሰበሰበንና ዘካውን ሳይሰጥ የቆጠረንም (ትጠራለች)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا
Amharic Translation - Africa Academy19. ሰው ቅጠ ቢስ ሆኖ ተፈጠረ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعًا
Amharic Translation - Africa Academy20. ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጭተኛ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلْخَيْرُ مَنُوعًا
Amharic Translation - Africa Academy21. መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘው ጊዜ ከልካይ ሆኖ ተፈጠረ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا ٱلْمُصَلِّينَ
Amharic Translation - Africa Academy22. ሰጋጆች ብቻ ሲቀሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَآئِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘወታሪዎች የሆኑት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ فِىٓ أَمْوَٰلِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የሆኑት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّلسَّآئِلِ وَٱلْمَحْرُومِ
Amharic Translation - Africa Academy25. ለለማኝ እና ከልመና ለሚቆጠብም መብት (ያለባቸው የሆኑ)፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ ٱلدِّينِ
Amharic Translation - Africa Academy26. እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት የሚያረጋግጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የሆኑት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ
Amharic Translation - Africa Academy28. የጌታቸው ቅጣት የማያስተማምን ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَٰفِظُونَ
Amharic Translation - Africa Academy29. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزْوَٰجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች ላይ ሲቀር:: እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَنِ ٱبْتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْعَادُونَ
Amharic Translation - Africa Academy31. ከዚያ ወዲያ የፈለገ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هُمْ لِأَمَٰنَٰتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَٰعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy32. እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የሆኑት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمْ قَآئِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy33. እነዚያም እነርሱ በምስክሮቻቸው ላይ ቀጥ ያሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ فِى جَنَّٰتٍ مُّكْرَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ
Amharic Translation - Africa Academy36. እነዚያ (በአላህ) የካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ቡድኖች ሲሆኑ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَيَطْمَعُ كُلُّ ٱمْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy38. ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَلَّآ إِنَّا خَلَقْنَٰهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy39. ይከልከል፤ በፍጹም እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍተወት ጠብታ) ፈጠርናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَآ أُقْسِمُ بِرَبِّ ٱلْمَشَٰرِقِ وَٱلْمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy40. (እናም ጉዳዩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም):: በምስራቆችና በምዕራቦች ጌታ እምላለሁ፤ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy41. ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا۟ وَيَلْعَبُوا۟ حَتَّىٰ يُلَٰقُوا۟ يَوْمَهُمُ ٱلَّذِى يُوعَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy42. ያንንም የሚሰፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተዋቸው፤ በአሉባልታዎችም ዉስጥ ይዋኙ፤ ይጫወቱም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ ٱلْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَ
Amharic Translation - Africa Academy43. ያ ቀን ወደ ጣዖት እንደሚሽቀዳደሙ ሆነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَٰشِعَةً أَبْصَٰرُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ذَٰلِكَ ٱلْيَوْمُ ٱلَّذِى كَانُوا۟ يُوعَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy44. ዓይኖቻቸው ያፈሩ ሆነው፤ ውርደት ትሸፍናቸዋለች:: ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቀን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→