ሱረቱ Nooh نوح
28 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 71
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِنَّآ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِۦٓ أَنْ أَنذِرْ قَوْمَكَ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰقَوْمِ إِنِّى لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ
Amharic Translation - Africa Academy3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرْكُمْ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى إِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ إِذَا جَآءَ لَا يُؤَخَّرُ لَوْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ إِنِّى دَعَوْتُ قَوْمِى لَيْلًا وَنَهَارًا
Amharic Translation - Africa Academy5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمْ يَزِدْهُمْ دُعَآءِىٓ إِلَّا فِرَارًا
Amharic Translation - Africa Academy6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنِّى كُلَّمَا دَعَوْتُهُمْ لِتَغْفِرَ لَهُمْ جَعَلُوٓا۟ أَصَٰبِعَهُمْ فِىٓ ءَاذَانِهِمْ وَٱسْتَغْشَوْا۟ ثِيَابَهُمْ وَأَصَرُّوا۟ وَٱسْتَكْبَرُوا۟ ٱسْتِكْبَارًا
Amharic Translation - Africa Academy7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنِّى دَعَوْتُهُمْ جِهَارًا
Amharic Translation - Africa Academy8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ إِنِّىٓ أَعْلَنتُ لَهُمْ وَأَسْرَرْتُ لَهُمْ إِسْرَارًا
Amharic Translation - Africa Academy9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقُلْتُ ٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارًا
Amharic Translation - Africa Academy10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُرْسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا
Amharic Translation - Africa Academy11. «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيُمْدِدْكُم بِأَمْوَٰلٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّٰتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَٰرًا
Amharic Translation - Africa Academy12. «ገንዘቦችና ልጆችንም ይለግሳችኋል:: ለእናንተ አትክልቶችን ያደርግላችኋል:: ለእናተም ወንዞችን ያደርግላችኋል አልኳቸው።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا لَكُمْ لَا تَرْجُونَ لِلَّهِ وَقَارًا
Amharic Translation - Africa Academy13. ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَدْ خَلَقَكُمْ أَطْوَارًا
Amharic Translation - Africa Academy14. በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَوْا۟ كَيْفَ خَلَقَ ٱللَّهُ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍ طِبَاقًا
Amharic Translation - Africa Academy15. አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَعَلَ ٱلْقَمَرَ فِيهِنَّ نُورًا وَجَعَلَ ٱلشَّمْسَ سِرَاجًا
Amharic Translation - Africa Academy16. በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ:: ጸሐይንም ብርሃን አደረገ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ نَبَاتًا
Amharic Translation - Africa Academy17. አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا
Amharic Translation - Africa Academy18. ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል:: ማውጣትንም ያወጣችኋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ بِسَاطًا
Amharic Translation - Africa Academy19. አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّتَسْلُكُوا۟ مِنْهَا سُبُلًا فِجَاجًا
Amharic Translation - Africa Academy20. ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ نُوحٌ رَّبِّ إِنَّهُمْ عَصَوْنِى وَٱتَّبَعُوا۟ مَن لَّمْ يَزِدْهُ مَالُهُۥ وَوَلَدُهُۥٓ إِلَّا خَسَارًا
Amharic Translation - Africa Academy21. ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَكَرُوا۟ مَكْرًا كُبَّارًا
Amharic Translation - Africa Academy22. «ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَا تَذَرُنَّ ءَالِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا
Amharic Translation - Africa Academy23. መሪዎችም አሉ፡- <አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።>
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَدْ أَضَلُّوا۟ كَثِيرًا وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا ضَلَٰلًا
Amharic Translation - Africa Academy24. «በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ:: ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِّمَّا خَطِيٓـَٰٔتِهِمْ أُغْرِقُوا۟ فَأُدْخِلُوا۟ نَارًا فَلَمْ يَجِدُوا۟ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَنصَارًا
Amharic Translation - Africa Academy25. በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ:: እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ:: ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ نُوحٌ رَّبِّ لَا تَذَرْ عَلَى ٱلْأَرْضِ مِنَ ٱلْكَٰفِرِينَ دَيَّارًا
Amharic Translation - Africa Academy26. ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكَ إِن تَذَرْهُمْ يُضِلُّوا۟ عِبَادَكَ وَلَا يَلِدُوٓا۟ إِلَّا فَاجِرًا كَفَّارًا
Amharic Translation - Africa Academy27. «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና:: ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رَّبِّ ٱغْفِرْ لِى وَلِوَٰلِدَىَّ وَلِمَن دَخَلَ بَيْتِىَ مُؤْمِنًا وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا تَبَارًۢا
Amharic Translation - Africa Academy28. «ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ:: ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→