ሱረቱ Qaaf ق
45 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 34
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ قٓ وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْمَجِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy1. ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ عَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَىْءٌ عَجِيبٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَءِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا ذَٰلِكَ رَجْعٌۢ بَعِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy3. «በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنقُصُ ٱلْأَرْضُ مِنْهُمْ وَعِندَنَا كِتَٰبٌ حَفِيظٌۢ
Amharic Translation - Africa Academy4. ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
بَلْ كَذَّبُوا۟ بِٱلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمْ فَهُمْ فِىٓ أَمْرٍ مَّرِيجٍ
Amharic Translation - Africa Academy5. ይልቁንም ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَمْ يَنظُرُوٓا۟ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَوْقَهُمْ كَيْفَ بَنَيْنَٰهَا وَزَيَّنَّٰهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٍ
Amharic Translation - Africa Academy6. ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏቸው ሆነው እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْأَرْضَ مَدَدْنَٰهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍۭ بَهِيجٍ
Amharic Translation - Africa Academy7. ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት :: በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَبْصِرَةً وَذِكْرَىٰ لِكُلِّ عَبْدٍ مُّنِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy8. ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَزَّلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً مُّبَٰرَكًا فَأَنۢبَتْنَا بِهِۦ جَنَّٰتٍ وَحَبَّ ٱلْحَصِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy9. ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلنَّخْلَ بَاسِقَٰتٍ لَّهَا طَلْعٌ نَّضِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy10. ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
رِّزْقًا لِّلْعِبَادِ وَأَحْيَيْنَا بِهِۦ بَلْدَةً مَّيْتًا كَذَٰلِكَ ٱلْخُرُوجُ
Amharic Translation - Africa Academy11. ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት):: በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት:: ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَأَصْحَٰبُ ٱلرَّسِّ وَثَمُودُ
Amharic Translation - Africa Academy12. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ وَإِخْوَٰنُ لُوطٍ
Amharic Translation - Africa Academy13. ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَصْحَٰبُ ٱلْأَيْكَةِ وَقَوْمُ تُبَّعٍ كُلٌّ كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy14. የጫካው ባለቤቶችም የቱብበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: ዛቻየም ተረጋገጠባቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَعَيِينَا بِٱلْخَلْقِ ٱلْأَوَّلِ بَلْ هُمْ فِى لَبْسٍ مِّنْ خَلْقٍ جَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy15. በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِۦ نَفْسُهُۥ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ ٱلْوَرِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy16. ሰውንም ነፍሱ በሀሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንሆን ፈጠርነው:: እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy17-ሁለት ቃል ተቀባዮች መላዕክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ሆነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy18. ከቃል ምንም አይናገርም ከአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የሆኑ መላዕክት ያሉበት ቢሆን እንጂ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَتْ سَكْرَةُ ٱلْمَوْتِ بِٱلْحَقِّ ذَٰلِكَ مَا كُنتَ مِنْهُ تَحِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy19. የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች። «(ሰው ሆይ!) ይህ ያ ከእርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» ይባላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنُفِخَ فِى ٱلصُّورِ ذَٰلِكَ يَوْمُ ٱلْوَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy20. በቀንዱም ውስጥ ይነፋል። ያ ቀን የዛቻው መፈጸሚያ ቀን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَآءَتْ كُلُّ نَفْسٍ مَّعَهَا سَآئِقٌ وَشَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy21. ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጅና መስካሪ ያለባት ሆና ትመጣለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّقَدْ كُنتَ فِى غَفْلَةٍ مِّنْ هَٰذَا فَكَشَفْنَا عَنكَ غِطَآءَكَ فَبَصَرُكَ ٱلْيَوْمَ حَدِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy22. «ከዚህ ነገር በእርግጥ የዘነጋህ ነበርክ። ሽፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ:: ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» (ይባላል)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ قَرِينُهُۥ هَٰذَا مَا لَدَىَّ عَتِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. ቁራኛዉም (መልዓክ) «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው።» ይላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلْقِيَا فِى جَهَنَّمَ كُلَّ كَفَّارٍ عَنِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy24. (አላህም ይላል): «ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّنَّاعٍ لِّلْخَيْرِ مُعْتَدٍ مُّرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. «ለበጎ ስራ ከልካይ በዳይ ተጠራጣሪ የሆነን ሁሉ ጣሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى جَعَلَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَأَلْقِيَاهُ فِى ٱلْعَذَابِ ٱلشَّدِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy26. «ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት» ይባላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ قَرِينُهُۥ رَبَّنَا مَآ أَطْغَيْتُهُۥ وَلَٰكِن كَانَ فِى ضَلَٰلٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy27. «ቁራኛው (ሰይጣን) ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም ግን ራሱ በሩቅ ስህተት ውስጥ ነበር» ይላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَا تَخْتَصِمُوا۟ لَدَىَّ وَقَدْ قَدَّمْتُ إِلَيْكُم بِٱلْوَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy28. (አላህም) ይላል: «ወደ እናተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስሆን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا يُبَدَّلُ ٱلْقَوْلُ لَدَىَّ وَمَآ أَنَا۠ بِظَلَّٰمٍ لِّلْعَبِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy29. «ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁም» (ይላቸዋል)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ نَقُولُ لِجَهَنَّمَ هَلِ ٱمْتَلَأْتِ وَتَقُولُ هَلْ مِن مَّزِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለገሀነም «ሞላሽን?» የምንልበትንና (ገሀነምም) «ጭማሪ አለን?» የምትልበትን ቀን አስጠንቅቃቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأُزْلِفَتِ ٱلْجَنَّةُ لِلْمُتَّقِينَ غَيْرَ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy31. ገነትም አላህን ለፈሩት ሁሉ ሩቅ ባልሆነ ስፍራ ትቀረባለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِيظٍ
Amharic Translation - Africa Academy32. (ይባላሉም) «ይህ ወደ አላህ ተመላሽና ህግጋቱን ጠባቂ ለሆነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّنْ خَشِىَ ٱلرَّحْمَٰنَ بِٱلْغَيْبِ وَجَآءَ بِقَلْبٍ مُّنِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy33. «አር-ረህማንን በሩቅ ሆኖ ለፈራና በተመላሽ ልብ ለመጣ ትቅቀረባለች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱدْخُلُوهَا بِسَلَٰمٍ ذَٰلِكَ يَوْمُ ٱلْخُلُودِ
Amharic Translation - Africa Academy34. «በሰላም ግቧታ ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy35. ለእነርሱ በውስጧ ሲሆኑ የሚሹት ሁሉ አላቸው እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّن قَرْنٍ هُمْ أَشَدُّ مِنْهُم بَطْشًا فَنَقَّبُوا۟ فِى ٱلْبِلَٰدِ هَلْ مِن مَّحِيصٍ
Amharic Translation - Africa Academy36. ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች በሀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ሆነው ማምለጫ ፍለጋ በየሀገሮቹ የመረመሩ ብዙዎችንም አጥፍተናል። ማምለጫ አለን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُۥ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى ٱلسَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy37. በዚሁ ውስጥ ልብ ላለው ወይም እርሱ በህሊናው ጆሮውን የሰጠ ሆኖ ወደ ሚነበብለት ጆሮውን ለጣለ ሰው ሁሉ ግሳጼ አለበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ
Amharic Translation - Africa Academy38. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን። ድካምም ምንም አልነካንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ ٱلشَّمْسِ وَقَبْلَ ٱلْغُرُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉትም ላይ ታገስ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመገባቷም በፊት አጥራው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَسَبِّحْهُ وَأَدْبَٰرَ ٱلسُّجُودِ
Amharic Translation - Africa Academy40. ከሌሊትም አጥራው፤ ከስግደቶችም በኋላዎች አጥራው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ ٱلْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (የሚነገርህን) አዳምጥም፤ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يَسْمَعُونَ ٱلصَّيْحَةَ بِٱلْحَقِّ ذَٰلِكَ يَوْمُ ٱلْخُرُوجِ
Amharic Translation - Africa Academy42. ጩኸቲቱን በእውነቱ የሚሰሙበት ቀን፤ ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا نَحْنُ نُحْىِۦ وَنُمِيتُ وَإِلَيْنَا ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy43. እኛው ሕያው እናደርጋለን:: እንገድላለንም:: በመጨረሻም ጊዜ መመለሻው ወደ እኛ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تَشَقَّقُ ٱلْأَرْضُ عَنْهُمْ سِرَاعًا ذَٰلِكَ حَشْرٌ عَلَيْنَا يَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy44. የሚፈጥኑ ሆነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫ ቀን ነው):: ይህ በእኛ ላይ ገር የሆነ መሰብሰብ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ وَمَآ أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ فَذَكِّرْ بِٱلْقُرْءَانِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ የሚሉትን ሁሉ አዋቂ ነን:: አንተም በእነርሱ ላይ አሰገዳጅ አይደለህም:: ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው ሁሉ በቁርኣን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→