caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Muminoon المؤمنون

118 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 74

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ قَدْ أَفْلَحَ ٱلْمُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1.ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ተሳካላቸው)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ هُمْ فِى صَلَاتِهِمْ خَٰشِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. እነዚያም በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُمْ عَنِ ٱللَّغْوِ مُعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. እነዚያም ከመጥፎ ነገር ሁሉ የራቁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያም ዘካን በአግባቡ ሰጪዎች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَٰفِظُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا عَلَىٰٓ أَزْوَٰجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ

Amharic Translation - Africa Academy6. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ሴት ባሪያዎች ላይ ካልሆነ በቀር (ብልቶቻቸውን ጠባቂ የሆኑት)፤ እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَنِ ٱبْتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْعَادُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. ከዚህ ሌላ በሆነ መንገድ (ስሜታቸዉን ሊያረኩ) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ የአላህን ወሰን አላፊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُمْ لِأَمَٰنَٰتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَٰعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. እነዚያም ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمْ يُحَافِظُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያም በስግደቶቻቸው ላይ (ሁለንተናዋን) የሚጠባበቁ የሆኑት

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْوَٰرِثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን) የሚወርሱ ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ خَلَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٍ مِّن طِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy12. በእርግጥ ሰውን (አደምን) ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ جَعَلْنَٰهُ نُطْفَةً فِى قَرَارٍ مَّكِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy13. ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ خَلَقْنَا ٱلنُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا ٱلْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا ٱلْمُضْغَةَ عِظَٰمًا فَكَسَوْنَا ٱلْعِظَٰمَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَٰهُ خَلْقًا ءَاخَرَ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحْسَنُ ٱلْخَٰلِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ስጋ አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጭዋንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን:: አጥንቶችንም ስጋን አለበስናቸው። ከዚያም (በዉስጡ ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው:: ከቅርፅ ሰጪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ከሁሉ ላቀ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّكُم بَعْدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. (ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ تُبْعَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ خَلَقْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلْخَلْقِ غَٰفِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy17. በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን:: ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنزَلْنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءًۢ بِقَدَرٍ فَأَسْكَنَّٰهُ فِى ٱلْأَرْضِ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابٍۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን:: በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው:: እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَنشَأْنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّٰتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَٰبٍ لَّكُمْ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٌ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች አትክልቶችን ለእናንተ አስገኘንላችሁ:: በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَشَجَرَةً تَخْرُجُ مِن طُورِ سَيْنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهْنِ وَصِبْغٍ لِّلْـَٔاكِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy20. ከሲና ተራራም የምትወጣ ዛፍ በቅባትና ለበይዎች መባያ በሚሆን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ لَكُمْ فِى ٱلْأَنْعَٰمِ لَعِبْرَةً نُّسْقِيكُم مِّمَّا فِى بُطُونِهَا وَلَكُمْ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٌ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. (ሰዎች ሆይ!) እናንተም በግመል፤ በከብት በፍየልና በበግ መገምገሚያ አላችሁ:: በሆዶችዋ ውስጥ ካለው ወተት እናጠጣችኋለን:: ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَلَيْهَا وَعَلَى ٱلْفُلْكِ تُحْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. በእርሷም ላይና በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥٓ أَفَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው። ወዲያዉም «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን?» አላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَالَ ٱلْمَلَؤُا۟ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَوْمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيْكُمْ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةً مَّا سَمِعْنَا بِهَٰذَا فِىٓ ءَابَآئِنَا ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy24. ከህዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል። አላህም ቢፈልግ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር። ይህንንም የሚለውን በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هُوَ إِلَّا رَجُلٌۢ بِهِۦ جِنَّةٌ فَتَرَبَّصُوا۟ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy25. «እርሱ እብደት ያለበት ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: በእርሱም እስከ ጊዜው ድረስ ተጠባበቁ።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ ٱنصُرْنِى بِمَا كَذَّبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy26. ኑሕም «ጌታዬ ሆይ! ስለ አስተባበሉኝ እርዳኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِ أَنِ ٱصْنَعِ ٱلْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمْرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسْلُكْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ ٱثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ ٱلْقَوْلُ مِنْهُمْ وَلَا تُخَٰطِبْنِى فِى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا ٱسْتَوَيْتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلْفُلْكِ فَقُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy28. አንተም አብረውህ ካሉት ፍጡሮች ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ በል: «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከበደለኛ ህዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُل رَّبِّ أَنزِلْنِى مُنزَلًا مُّبَارَكًا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْمُنزِلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy29. «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የሆነን ማውረድ አውርደኝ:: አንተም ከአደላዳዮች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ وَإِن كُنَّا لَمُبْتَلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy30. በዚህ ውስጥ ለሃያልነታችን አያሌ ተዓምራት አሉበት:: እነሆ እኛ (የኑሕን ሰዎች) ፈታኞች ነበርን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَنشَأْنَا مِنۢ بَعْدِهِمْ قَرْنًا ءَاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ከዚያ ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَرْسَلْنَا فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُۥٓ أَفَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy32. በውስጣቸዉም ከእነርሱ የሆኑን መልዕክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالَ ٱلْمَلَأُ مِن قَوْمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِلِقَآءِ ٱلْـَٔاخِرَةِ وَأَتْرَفْنَٰهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يَأْكُلُ مِمَّا تَأْكُلُونَ مِنْهُ وَيَشْرَبُ مِمَّا تَشْرَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. ከህዝቦቹም እነዚያ የካዱት ሰዎች በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ህይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። ከምትበሉት ምግብ ይበላል፤ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِنْ أَطَعْتُم بَشَرًا مِّثْلَكُمْ إِنَّكُمْ إِذًا لَّخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy34. «የናንተው ብጤያችሁ የሆነን ሰው ብትታዘዙ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናችሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَيَعِدُكُمْ أَنَّكُمْ إِذَا مِتُّمْ وَكُنتُمْ تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخْرَجُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. «‹እናንተ ሞታችሁ አፈርና አጥንቶችም በሆናችሁ ጊዜ እናንተ ከመቃብር ትወጣላችሁ› በማለት ያስፈራራችኋልን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَيْهَاتَ هَيْهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy36. «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ከእውነት ራቀ፤ በጣም ራቀ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هِىَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا وَمَا نَحْنُ بِمَبْعُوثِينَ

Amharic Translation - Africa Academy37. «እርሷ (ህይወት) ማለት ቅርቢቱ ህይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን። ህያዉም እንሆናለን። እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም" (አሉ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنْ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا وَمَا نَحْنُ لَهُۥ بِمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy38. «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: እኛም በእርሱ አማኞች አይደለንም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ رَبِّ ٱنصُرْنِى بِمَا كَذَّبُونِ

Amharic Translation - Africa Academy39. መልዕክተኛዉም «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ በእነርሱ ላይ እርዳኝ።» አለ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ عَمَّا قَلِيلٍ لَّيُصْبِحُنَّ نَٰدِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy40. አላህም «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥፋታቸው በእርግጥ ተጸጻቾች ይሆናሉ።» አለው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّيْحَةُ بِٱلْحَقِّ فَجَعَلْنَٰهُمْ غُثَآءً فَبُعْدًا لِّلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy41. ወዲያዉም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፤ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው:: ለበደለኞች ህዝቦችም ከእዝነት መራቅ ተገባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَنشَأْنَا مِنۢ بَعْدِهِمْ قُرُونًا ءَاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy42. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا تَسْبِقُ مِنْ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسْتَـْٔخِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy43. ማንኛይቱም ህዝብ ጊዜዋን አትቀድምም:: ከጊዜያቸዉም አይቆዩምም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا تَتْرَا كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةً رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُ فَأَتْبَعْنَا بَعْضَهُم بَعْضًا وَجَعَلْنَٰهُمْ أَحَادِيثَ فَبُعْدًا لِّقَوْمٍ لَّا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy44. ከዚያም መልዕክተኞቻችንን በተከታታይ ላክን፤ ማንኛይቱንም ህዝብ መልእክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት። ከፊላቸውንም በከፊሉ በጥፋት አስከታተልን፤ ወሬዎችም አደረግናቸው፤ ለማያምኑም ህዝቦች ከእዝነታችን መራቅ ተገባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلْطَٰنٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy45. ከዚያ ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችንና በግልጽ ማስረጃ ላክናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦ فَٱسْتَكْبَرُوا۟ وَكَانُوا۟ قَوْمًا عَالِينَ

Amharic Translation - Africa Academy46. ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ ላክናቸው። ድሮውም የኮሩና የተንበጣረሩ ህዝቦችም ነበሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَالُوٓا۟ أَنُؤْمِنُ لِبَشَرَيْنِ مِثْلِنَا وَقَوْمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy47. «ህዝቦቻቸው ለኛ ተገዢዎች ሆነው ሳሉ ብጤያችን ለሆኑ ሰዎች እናምናለን?» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُوا۟ مِنَ ٱلْمُهْلَكِينَ

Amharic Translation - Africa Academy48. አስተባበሏቸዉም፤ ከጠፊዎችም ሆኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ لَعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy49. ሙሳንም ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَجَعَلْنَا ٱبْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةً وَءَاوَيْنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبْوَةٍ ذَاتِ قَرَارٍ وَمَعِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy50. የመርየምን ልጅ ዒሳንና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው:: የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ሆነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُوا۟ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعْمَلُوا۟ صَٰلِحًا إِنِّى بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy51. እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ሁሉ ብሉ:: በጎ ስራንም ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱتَّقُونِ

Amharic Translation - Africa Academy52. ይህችም በአንድ አምላክ የማመን ህግጋት አንድ መንገድ ስትሆን ሃይማኖታችሁ ናት:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَقَطَّعُوٓا۟ أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ زُبُرًا كُلُّ حِزْبٍۭ بِمَا لَدَيْهِمْ فَرِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy53. ከዚያም ተከታዮቻቸው ሃይማኖታቸውን በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፤ ህዝቦች ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذَرْهُمْ فِى غَمْرَتِهِمْ حَتَّىٰ حِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስከ ጊዜያቸዉም ድረስ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَيَحْسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٍ وَبَنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy55. ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

نُسَارِعُ لَهُمْ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ بَل لَّا يَشْعُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy56. በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው እንደሆነ ያስባሉን? አይደለም፤ ይህ ሁሉ እነርሱን ለማዘናጋት መሆኑን አያውቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنْ خَشْيَةِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy57. እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የሆኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمْ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy58. እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራት የሚያምኑት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمْ لَا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy59. እነዚያም በጌታቸው የማያጋሩት፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يُؤْتُونَ مَآ ءَاتَوا۟ وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَٰجِعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy60. እነዚያም የሚሰጡትን ነገር ሁሉ እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ وَهُمْ لَهَا سَٰبِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. እነዚያ በመልካም ስራዎች ይጣደፋሉ:: እነርሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا وَلَدَيْنَا كِتَٰبٌ يَنطِقُ بِٱلْحَقِّ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy62. ማንኛይቱንም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድዳትም:: እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አለ:: እነርሱም አይበደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ قُلُوبُهُمْ فِى غَمْرَةٍ مِّنْ هَٰذَا وَلَهُمْ أَعْمَٰلٌ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمْ لَهَا عَٰمِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy63. በእውነቱ ከሓዲያን ልቦቻቸው ከዚህ መጽሐፍ በዝንጋታ ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱም ከዚህ ሌላ እነርሱ ለእርሷ ሰሪዎችዋ የሆኑ መጥፎ ስራዎች አሏቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذْنَا مُتْرَفِيهِم بِٱلْعَذَابِ إِذَا هُمْ يَجْـَٔرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy64. ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا تَجْـَٔرُوا۟ ٱلْيَوْمَ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy65. (ይባላሉም) «ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱምና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَدْ كَانَتْ ءَايَٰتِى تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُمْ عَلَىٰٓ أَعْقَٰبِكُمْ تَنكِصُونَ

Amharic Translation - Africa Academy66. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር። እናንተ ግን በተረከዞቻችሁ ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُسْتَكْبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرًا تَهْجُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy67. «በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ሆናችሁ (ትመለሱ ነበር)።» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَمْ يَدَّبَّرُوا۟ ٱلْقَوْلَ أَمْ جَآءَهُم مَّا لَمْ يَأْتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy68. የቁርኣንን ንግግርን አያስተነትኑምን? ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَمْ يَعْرِفُوا۟ رَسُولَهُمْ فَهُمْ لَهُۥ مُنكِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy69. ወይስ መልዕክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ በእርሱ ከሓዲያን ናቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةٌۢ بَلْ جَآءَهُم بِٱلْحَقِّ وَأَكْثَرُهُمْ لِلْحَقِّ كَٰرِهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. ወይስ «በእርሱ ዕብደት አለበት» ይላሉን? እብድ አይደለም። እውነትን ይዞ መጣላቸው:: አብዛኞቻቸዉም ግን እውነትን ጠይዎች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلْحَقُّ أَهْوَآءَهُمْ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ بَلْ أَتَيْنَٰهُم بِذِكْرِهِمْ فَهُمْ عَن ذِكْرِهِم مُّعْرِضُونَ

Amharic Translation - Africa Academy71. እውነታው (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸዉም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር:: ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው:: እነርሱም ክብራቸውን ዘንጊዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ تَسْـَٔلُهُمْ خَرْجًا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيْرٌ وَهُوَ خَيْرُ ٱلرَّٰزِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy72. ወይስ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ ከሁሉም በላጭ ነው:: እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّكَ لَتَدْعُوهُمْ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy73.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy74. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ግን ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ رَحِمْنَٰهُمْ وَكَشَفْنَا مَا بِهِم مِّن ضُرٍّ لَّلَجُّوا۟ فِى طُغْيَٰنِهِمْ يَعْمَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy75. ባዘንላቸውና በእነርሱ ያለውን ጉዳትም ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋዥቁ ሆነው ይዘወትሩ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَخَذْنَٰهُم بِٱلْعَذَابِ فَمَا ٱسْتَكَانُوا۟ لِرَبِّهِمْ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy76. በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው:: ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም:: የሚዋደቁም አይደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحْنَا عَلَيْهِم بَابًا ذَا عَذَابٍ شَدِيدٍ إِذَا هُمْ فِيهِ مُبْلِسُونَ

Amharic Translation - Africa Academy77. በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የሆነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِىٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. እርሱም ያ መስሚያዎችን፤ ማያዎችንና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው:: ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى ذَرَأَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ وَإِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy79. እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው:: በመጨረሻም ጊዜ ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخْتِلَٰفُ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy80. እርሱም ያ ህያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው:: የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው :: አታውቁምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ قَالُوا۟ مِثْلَ مَا قَالَ ٱلْأَوَّلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy81. ይልቁንም የመካ ከሓዲያን ልክ የፊተኞቹ ህዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوٓا۟ أَءِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبْعُوثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy82. አሉም: «በሞትንና አፈርና አጥንቶች በሆንን ጊዜ እኛ እንደገና ተቀስቃሾች ነን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَقَدْ وُعِدْنَا نَحْنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبْلُ إِنْ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy83. «ይህንን ሁኔታ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لِّمَنِ ٱلْأَرْضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ እስቲ ንገሩኝ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ የአላህ ነው።» ይሉሃል። «ታዲያ አትገሠጹምን?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبْعِ وَرَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْعَظِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰባቱ ሰማያት ጌታ የታላቁም ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy88. «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ፤ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ (እስቲ መልሱልኝ)» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُونَ لِلَّهِ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ أَتَيْنَٰهُم بِٱلْحَقِّ وَإِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy90. ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው እነርሱም በመካዳቸው ውሸታሞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنْ إِلَٰهٍ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy91. አላህ ምንም ልጅን አልያዘም አልወለደም:: ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም:: ሌላ አምላክ በነበረማ አምላኩ ሁሉ የፈጠረውን ነገር በማስተዳደር ከሌላው በተለየ ነበር:: ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በነገሰ ነበር:: አላህ ከሓዲያን እሱን ከሚመጥኑበት መግለጫ ሁሉ ጠራ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy92. ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ነው:: በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّى مَا يُوعَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «ጌታዬ ሆይ! የሚስፈራሩበትን ቅጣት ብታሳየኝ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبِّ فَلَا تَجْعَلْنِى فِى ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy94. «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ህዝቦች ውስጥ አታድርገኝ።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّا عَلَىٰٓ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمْ لَقَٰدِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy95. እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱدْفَعْ بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ٱلسَّيِّئَةَ نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَصِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጠባይ መጥፎይቱን ነገር መልስ:: እኛ ከሓዲያን የሚሉትን ሁሉ አዋቂዎች ነንና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَٰتِ ٱلشَّيَٰطِينِ

Amharic Translation - Africa Academy97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «ጌታዬ ሆይ ከሰይጣናት ጉትጎታዎች ባንተ እጠበቃለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحْضُرُونِ

Amharic Translation - Africa Academy98. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እኔ ከመጣዳቸው ከመቅረባቸውም ባንተው እጠበቃለሁ።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَهُمُ ٱلْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ٱرْجِعُونِ

Amharic Translation - Africa Academy99. አንዳቸውን ሞት በመጣበት ጊዜ ይላል: «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَعَلِّىٓ أَعْمَلُ صَٰلِحًا فِيمَا تَرَكْتُ كَلَّآ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَا وَمِن وَرَآئِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

Amharic Translation - Africa Academy100. «ችላ ብዬ የተውኩትን በጎ ስራ ልሰራ እከጅላለሁና።» (ይላል)። (ይህን ከማለት ይከልከል):: እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የሆነች ቃል (ብቻ) ናት:: ከበስተፊታቸዉም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا نُفِخَ فِى ٱلصُّورِ فَلَآ أَنسَابَ بَيْنَهُمْ يَوْمَئِذٍ وَلَا يَتَسَآءَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy101. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም። አይጠያየቁምም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَن ثَقُلَتْ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy102.ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَنْ خَفَّتْ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ فِى جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy103. እነዚያ ሚዛኖቻቸዉም የቀለሉባቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ በገሀነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَلْفَحُ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ وَهُمْ فِيهَا كَٰلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy104. ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፋቸዋለች:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَكُنْ ءَايَٰتِى تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy105. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» ይባላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَآلِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy106. (እነርሱም) ይላሉ: «ታላቁ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችንና ጠማማ ህዝቦች ነበርን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَبَّنَآ أَخْرِجْنَا مِنْهَا فَإِنْ عُدْنَا فَإِنَّا ظَٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy107. «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣንና ወደ ዱንያ መልሰን:: ከዚህ በኋላ ወደ ክህደት ብንመለስ እኛ በዳዮች ነን።» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالَ ٱخْسَـُٔوا۟ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ

Amharic Translation - Africa Academy108. አላህም ይላቸዋል: «ወራዶች ሆናችሁ በውስጧ አርፋችሁ ኑሩ እንጂ ፍጹም አታናግሩኝ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُۥ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْ عِبَادِى يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلرَّٰحِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy109. «እነሆ ከባሮቼ መካከል ‹ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን:: እዘንልንም:: አንተ ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ› የሚሉ ክፍሎች ነበሩ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱتَّخَذْتُمُوهُمْ سِخْرِيًّا حَتَّىٰٓ أَنسَوْكُمْ ذِكْرِى وَكُنتُم مِّنْهُمْ تَضْحَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy110. «እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው:: በእነርሱም ላይ ትስቁባቸው ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنِّى جَزَيْتُهُمُ ٱلْيَوْمَ بِمَا صَبَرُوٓا۟ أَنَّهُمْ هُمُ ٱلْفَآئِزُونَ

Amharic Translation - Africa Academy111. «እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱን ብቻ በማድረግ መነዳኋቸው።» ይላቸዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰلَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِى ٱلْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy112. «በምድር ውስጥ ስንትን አመታትን ቆያችሁ?» ይላቸዋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَالُوا۟ لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَسْـَٔلِ ٱلْعَآدِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy113. «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን:: ቆጣሪዎችንም ጠይቅ» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قَٰلَ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا لَّوْ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy114. ይላቸዋልም: «እናንተ የቆያችሁትን መጠን የምታውቁ ብትሆኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ ከምትቆዩት ጊዜ አንጻር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَٰكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy115. «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደ እኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን? (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)።» (ይባላሉ።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْكَرِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy116. የእውነቱ ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: የዚያ የሚያምረው ዐርሽ ጌታም እሱ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرْهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy117. ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሁሉ ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው:: እነሆ ከሓዲያን አይድኑም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقُل رَّبِّ ٱغْفِرْ وَٱرْحَمْ وَأَنتَ خَيْرُ ٱلرَّٰحِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሆይ! ማር:: እዘንም:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል፡:

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70