ሱረቱ Al-Hajj الحج
78 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 103
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمْ إِنَّ زَلْزَلَةَ ٱلسَّاعَةِ شَىْءٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy1.እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ تَرَوْنَهَا تَذْهَلُ كُلُّ مُرْضِعَةٍ عَمَّآ أَرْضَعَتْ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمْلٍ حَمْلَهَا وَتَرَى ٱلنَّاسَ سُكَٰرَىٰ وَمَا هُم بِسُكَٰرَىٰ وَلَٰكِنَّ عَذَابَ ٱللَّهِ شَدِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy2. በምታዩዋት ቀን ሁኔታው አጥቢ ሁሉ ያጠባችውን ልጅ ትዘነጋዋለች። እርጉዝ ሴት ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች:: ሰዎቹንም በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ መስለው ታያቸዋለህ:: እነርሱ ከመጠጥ የሰከሩ ሁው ሳይሆን ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ስለሆነ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيْطَٰنٍ مَّرِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy3. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም የሚከተል ሰው አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُۥ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُۥ يُضِلُّهُۥ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy4. እነሆ የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል:: ወደ አቃጣይ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል:: (ተወስኖባቸዋል)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمْ فِى رَيْبٍ مِّنَ ٱلْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِن مُّضْغَةٍ مُّخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِّنُبَيِّنَ لَكُمْ وَنُقِرُّ فِى ٱلْأَرْحَامِ مَا نَشَآءُ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوٓا۟ أَشُدَّكُمْ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرْذَلِ ٱلْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنۢ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْـًٔا وَتَرَى ٱلْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَآ أَنزَلْنَا عَلَيْهَا ٱلْمَآءَ ٱهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنۢبَتَتْ مِن كُلِّ زَوْجٍۭ بَهِيجٍ
Amharic Translation - Africa Academy5. ሰዎች ሆይ! ከሞት በኋላ ከመቀስቀስ በመጠራጠር ጉዳይ እንደ ሆናችሁ የመጀመሪያውን (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ። እኛም) ከአፈር ፈጠርናችሁ:: ከዚያ ከፍትወት ጠብታ፤ ከዚያም ከረጋ ደም፤ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ። የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማህጸን ውስጥ እናረጋዋለን። ከዚያም ህፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን:: ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን):: ከናንተም መካከል በወጣትነቱ የሚሞት ሰው አለ:: ከናንተም መካከል ከዕውቀት በኋላ ምንንም ላያውቅ ወደ ጃጀ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ:: ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች \ትነቃነቃለች\:: ትነፋለችም:: ውበት ካለው የእጽዋት አይነት ሁሉ ታበቅላለችም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّهُۥ يُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. ይህ ሁሉ አላህ ፍፁም እውነት፤ እርሱም ሙታንን ህያው የሚያደርግ፤ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّ ٱلسَّاعَةَ ءَاتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَأَنَّ ٱللَّهَ يَبْعَثُ مَن فِى ٱلْقُبُورِ
Amharic Translation - Africa Academy7. የሰዓቲቱም መከሰት ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለበት በመሆኑና አላህ በመቃብሮች ውስጥ ያለን ሁሉ የሚቀሰቅስ በመሆኑም ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِى ٱللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَٰبٍ مُّنِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት ያለ አንዳች ማስረጃም ያለ አብራሪ መጽሐፍም ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثَانِىَ عِطْفِهِۦ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُۥ فِى ٱلدُّنْيَا خِزْىٌ وَنُذِيقُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ عَذَابَ ٱلْحَرِيقِ
Amharic Translation - Africa Academy9. ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት (ይከራከራል)። በቅርቢቱ ዓለም ለርሱ ውርደት አለው:: በትንሳኤ ቀንም አቃጣይን (የእሳት) ቅጣት እናቀምሰዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ يَدَاكَ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّٰمٍ لِّلْعَبِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy10. «ይህ እጆችህ ባስቀደሙት ኃጢአት ነው፣ አላህም ለባሮቹ ፈጽሞ በዳይ አይደለም።» (ይባላል።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَعْبُدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ فَإِنْ أَصَابَهُۥ خَيْرٌ ٱطْمَأَنَّ بِهِۦ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ ٱنقَلَبَ عَلَىٰ وَجْهِهِۦ خَسِرَ ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةَ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْخُسْرَانُ ٱلْمُبِينُ
Amharic Translation - Africa Academy11. ከሰዎችም መካከል በሃይማኖት ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ:: እናም መልካም ነገር ካገኘው በእምነቱ ላይ ይረጋል:: መከራ ካገኘው ግን በፊቱ ላይ ይገለበጣል (ይክዳል):: ይህ አይነቱ ሰው የቅርቢቱን ዓለምም ሆነ የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ:: ይህ ነው ግልጽ ኪሳራ ማለት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُۥ وَمَا لَا يَنفَعُهُۥ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلضَّلَٰلُ ٱلْبَعِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy12. ከአላህ ሌላ የማይጎዳውንና የማይጠቅመውን ይገዛል:: ይህ እርሱ ከእውነት የራቀ ስህተት ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَدْعُوا۟ لَمَن ضَرُّهُۥٓ أَقْرَبُ مِن نَّفْعِهِۦ لَبِئْسَ ٱلْمَوْلَىٰ وَلَبِئْسَ ٱلْعَشِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy13. ያንን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ወደ እሱ የሚቀርብን ይገዛል:: ረዳቱ ምንኛ ከፋ! ወዳጁም ምንኛ ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يُدْخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ إِنَّ ٱللَّهَ يَفْعَلُ مَا يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy14. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባቸዋል:: አላህም የሚሻውን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይሰራልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَن كَانَ يَظُنُّ أَن لَّن يَنصُرَهُ ٱللَّهُ فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ فَلْيَمْدُدْ بِسَبَبٍ إِلَى ٱلسَّمَآءِ ثُمَّ لْيَقْطَعْ فَلْيَنظُرْ هَلْ يُذْهِبَنَّ كَيْدُهُۥ مَا يَغِيظُ
Amharic Translation - Africa Academy15. አላህ (መልዕክተኛውን) ሙሐመድን በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አይረዳዉም ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋና ከዚያ (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ:: ይህ ተግባሩ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግደለት እንደሆነም ይመልከት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَٰهُ ءَايَٰتٍۭ بَيِّنَٰتٍ وَأَنَّ ٱللَّهَ يَهْدِى مَن يُرِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy16. ልክ እንደዚሁ (ቁርኣንን) የተብራሩ አናቅጽ አድርገን አወረድነው:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይመራልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَٱلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلصَّٰبِـِٔينَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ وَٱلْمَجُوسَ وَٱلَّذِينَ أَشْرَكُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy17. እነዚያ በአላህ ያመኑ እነዚያ አይሁዳውያን፤ እነዚያ ምንም እምነት የሌላቸው ሳቢያኖች፤ ክርስቲያኖችም፤ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ ሁሉ አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَسْجُدُ لَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِى ٱلْأَرْضِ وَٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ وَٱلنُّجُومُ وَٱلْجِبَالُ وَٱلشَّجَرُ وَٱلدَّوَآبُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ ٱلنَّاسِ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيْهِ ٱلْعَذَابُ وَمَن يُهِنِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّكْرِمٍ إِنَّ ٱللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَآءُ
Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ጸሐይና፤ ጨረቃም፤ ከዋክብትም፤ ተራሮችም፤ ዛፎችም፤ ተንቀሳቃሾችም ፍጡራንና ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቅምን? ብዙዉም በእርሱ ላይ የአላህ ቅጣት ተረጋገጠበት:: አላህ የሚያዋርደው ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለዉም:: አላህ የሻውን ይሰራልና:: {1}
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰذَانِ خَصْمَانِ ٱخْتَصَمُوا۟ فِى رَبِّهِمْ فَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ قُطِّعَتْ لَهُمْ ثِيَابٌ مِّن نَّارٍ يُصَبُّ مِن فَوْقِ رُءُوسِهِمُ ٱلْحَمِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy19. እነዚህ በጌታቸው ጉዳይ የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው:: እነዚያ በአላህ የካዱት የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፤ እንዲቀልጥ ከራሶቻቸው ላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧባቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يُصْهَرُ بِهِۦ مَا فِى بُطُونِهِمْ وَٱلْجُلُودُ
Amharic Translation - Africa Academy20. በሆዶቻቸው ውስጥ ያለውና ቆዳዎቻቸው በእርሱ ይቀለጣል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَهُم مَّقَٰمِعُ مِنْ حَدِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. ለእነርሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلَّمَآ أَرَادُوٓا۟ أَن يَخْرُجُوا۟ مِنْهَا مِنْ غَمٍّ أُعِيدُوا۟ فِيهَا وَذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلْحَرِيقِ
Amharic Translation - Africa Academy22. ከጭንቀት ብርታት የተነሳ ከእርሷ ለመውጣት በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ። «ያን በጣም የሚያቃጥለውን ቅጣት ቅመሱ።» (ይባላሉ።)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يُدْخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy23. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ጅረት ወንዞች በሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: በእርሷ ውስጥ የወርቅ አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ:: በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸዉም ከሐር የተሰሩ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُدُوٓا۟ إِلَى ٱلطَّيِّبِ مِنَ ٱلْقَوْلِ وَهُدُوٓا۟ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلْحَمِيدِ
Amharic Translation - Africa Academy24. ወደ መልካም ንግግር ተመሩ፣ ወደ ምስጉን መንገድም ተመሩ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ ٱلَّذِى جَعَلْنَٰهُ لِلنَّاسِ سَوَآءً ٱلْعَٰكِفُ فِيهِ وَٱلْبَادِ وَمَن يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍۭ بِظُلْمٍ نُّذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy25. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችን ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት (ሰዎች) እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ (አሳማሚ ቅጣት እንቀጣቸዋልን::) በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚያስብ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ
Amharic Translation - Africa Academy26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት (እንዲህ) ባልነውም ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «በኔ ምንንም አታጋራ:: ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት (ለኢባዳ) ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸዉም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَذِّن فِى ٱلنَّاسِ بِٱلْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
Amharic Translation - Africa Academy27. «ኢብራሂም ሆይ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ:: እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎች ሁሉ ላይም ሆነዉም ይመጡልሃልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّيَشْهَدُوا۟ مَنَٰفِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ فِىٓ أَيَّامٍ مَّعْلُومَٰتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْبَآئِسَ ٱلْفَقِيرَ
Amharic Translation - Africa Academy28. «ለእነርሱ የሆኑ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእነዚያ በታወቁ ቀናትም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል:: ከእርሷም ብሉ:: ችግረኛ ድሀንም አብሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ لْيَقْضُوا۟ تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا۟ نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا۟ بِٱلْبَيْتِ ٱلْعَتِيقِ
Amharic Translation - Africa Academy29. «ከዚያም (እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን) ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ:: ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ:: በጥንታዊዉም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ።» አልን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ حُرُمَٰتِ ٱللَّهِ فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُۥ عِندَ رَبِّهِۦ وَأُحِلَّتْ لَكُمُ ٱلْأَنْعَٰمُ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ
Amharic Translation - Africa Academy30. ይሀው ነው። የአላህንም ህግጋት የሚያከብር ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው:: የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች:: ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ:: ሐሰትንም ቃል ራቁ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
حُنَفَآءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِۦ وَمَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَتَخْطَفُهُ ٱلطَّيْرُ أَوْ تَهْوِى بِهِ ٱلرِّيحُ فِى مَكَانٍ سَحِيقٍ
Amharic Translation - Africa Academy31. ለአላህ ታዛዦች፤ በእርሱ የማታጋሩና ወደ ቀጥተኞች መንገድ የተዘነበላችሁ ሁኑ:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ንፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى ٱلْقُلُوبِ
Amharic Translation - Africa Academy32. (ነገሩ) ይህ ነው። የአላህን ሃይማኖታዊ ምልክቶች የሚያከብር ሁሉ ይህ ድርጊቱ አላህን ከሚፈሩ ልቦች የሚፈጸም ጥንቃቄ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَكُمْ فِيهَا مَنَٰفِعُ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّى ثُمَّ مَحِلُّهَآ إِلَى ٱلْبَيْتِ ٱلْعَتِيقِ
Amharic Translation - Africa Academy33. ለእናንተ በእርሷ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከዚያም የ(ኡዱሂያ)ማረጃ ስፍራ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ فَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَلَهُۥٓ أَسْلِمُوا۟ وَبَشِّرِ ٱلْمُخْبِتِينَ
Amharic Translation - Africa Academy34. ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ ለህዝቦች ሁሉ (ወደ አላህ) መስዋዕት ማቅረብን ሀይማኖታዊ ሥርአቶችን ደነገግን:: አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እርሱንም ብቻ ታዘዙ:: ለአላህ ተዋራጆችንም በመልካም ነገር አብስራቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَٱلصَّٰبِرِينَ عَلَىٰ مَآ أَصَابَهُمْ وَٱلْمُقِيمِى ٱلصَّلَوٰةِ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን (የሚፈሩትን)፤ በደረሰባቸዉም መከራ ላይ ታጋሾችን፤ ሰላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱትን በገነት አብስር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلْبُدْنَ جَعَلْنَٰهَا لَكُم مِّن شَعَٰٓئِرِ ٱللَّهِ لَكُمْ فِيهَا خَيْرٌ فَٱذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَيْهَا صَوَآفَّ فَإِذَا وَجَبَتْ جُنُوبُهَا فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْقَانِعَ وَٱلْمُعْتَرَّ كَذَٰلِكَ سَخَّرْنَٰهَا لَكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy36. ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው:: በእነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ:: በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮቿ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ:: ጎኖቻቸዉም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ:: በግልጽ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ:: ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَن يَنَالَ ٱللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَآؤُهَا وَلَٰكِن يَنَالُهُ ٱلتَّقْوَىٰ مِنكُمْ كَذَٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمْ لِتُكَبِّرُوا۟ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَىٰكُمْ وَبَشِّرِ ٱلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy37. አላህን ስጋዎቿም ሆኑ ደሞቿ ፈጽሞ አይደርሰዉም:: ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል:: እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጎ ሰሪዎችንም አብስር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يُدَٰفِعُ عَنِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ خَوَّانٍ كَفُورٍ
Amharic Translation - Africa Academy38. አላህ ከእነዚያ በእርሱ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል። አላህ ከዳተኛንና ውለታ ቢስን ሁሉ አይወድምና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَٰتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا۟ وَإِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy39. ለእነዚያ በከሓዲያን ለሚገደሉት ትክክለኛ አማኞች የተበደሉ በመሆናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው:: አላህ እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ أُخْرِجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّآ أَن يَقُولُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ وَلَوْلَا دَفْعُ ٱللَّهِ ٱلنَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَٰمِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَٰتٌ وَمَسَٰجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا ٱسْمُ ٱللَّهِ كَثِيرًا وَلَيَنصُرَنَّ ٱللَّهُ مَن يَنصُرُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَقَوِىٌّ عَزِيزٌ
Amharic Translation - Africa Academy40. ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው።» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከየቀያቸው የተባረሩ ለሆኑት ከራሳቸው ላይ መከላከል ተፈቀደ:: አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር:: አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሁሉ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِينَ إِن مَّكَّنَّٰهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ أَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَمَرُوا۟ بِٱلْمَعْرُوفِ وَنَهَوْا۟ عَنِ ٱلْمُنكَرِ وَلِلَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلْأُمُورِ
Amharic Translation - Africa Academy41. እነርሱ ማለት እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው (የበላይነትን ሰጥተን ባጎናጸፍናቸው ኖሮ) ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፤ ዘካንም የሚሰጡ፤ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፤ ከመጥፎ ነገርም የሚከለከሉ ናቸው:: የነገሮች ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَعَادٌ وَثَمُودُ
Amharic Translation - Africa Academy42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነርሱ በፊት የኑሕ ህዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም በእርግጥ አስተባብለዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَوْمُ إِبْرَٰهِيمَ وَقَوْمُ لُوطٍ
Amharic Translation - Africa Academy43. የኢብራሂምም ህዝቦች የሉጥም ህዝቦች እንደዚሁ አስተባብለዋል፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَصْحَٰبُ مَدْيَنَ وَكُذِّبَ مُوسَىٰ فَأَمْلَيْتُ لِلْكَٰفِرِينَ ثُمَّ أَخَذْتُهُمْ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
Amharic Translation - Africa Academy44. የመድየንም ሰዎች እንዲሁ አስተባብለዋል:: ሙሳም ተስተባብሏል:: ለከሓዲያንም ጊዜን ሰጠኋቸው:: ከዚያ ያዝኳቸው። ጥላቻዬም እንዴት ነበረ (ተመልከቱ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَٰهَا وَهِىَ ظَالِمَةٌ فَهِىَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَبِئْرٍ مُّعَطَّلَةٍ وَقَصْرٍ مَّشِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy45. ከከተሞች መካከል በደለኛ ሆነው ያጠፋናቸው እና በጣሪያዎቻቸው ላይ ወዳቂ የሆኑ ብዙ ናቸው:: ከተራቆተም የውሃ ጉድጓድ ከተገነባም ህንፃ ያጠፋነው ብዙ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَتَكُونَ لَهُمْ قُلُوبٌ يَعْقِلُونَ بِهَآ أَوْ ءَاذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا فَإِنَّهَا لَا تَعْمَى ٱلْأَبْصَٰرُ وَلَٰكِن تَعْمَى ٱلْقُلُوبُ ٱلَّتِى فِى ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy46. ለእነርሱም የሚያውቁባቸው ልቦች፤ ወይም የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም:: እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ናቸው የሚታወሩት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِٱلْعَذَابِ وَلَن يُخْلِفَ ٱللَّهُ وَعْدَهُۥ وَإِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ
Amharic Translation - Africa Academy47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን ቅጣትን እንድታመጣ ያቻኩሉሃል (ያጣድፉሃል):: በጌታህ ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት የሚመጥን ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ أَمْلَيْتُ لَهَا وَهِىَ ظَالِمَةٌ ثُمَّ أَخَذْتُهَا وَإِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy48. ከከተማ በዳይ ሆና ጊዜ የሰጠኋትና ከዚያ የያዝኳት የቀጣኋት ብዙ ናት:: የመጨረሻው መመለሻም ወደ እኔ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَآ أَنَا۠ لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy50. እነዚያም በትክክል ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ለእነርሱ ምህረትና ያማረ ሲሳይ አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ سَعَوْا۟ فِىٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy51. እነዚያ ከአላህ የሚያመልጡ መስሏቸው ተዓምራታችንን በመንቀፍ የተጉ ሁሉ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት አንድንም መልዕክተኛ ወይም ነብይ አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ የማጥመሚያን ሀሳብ የሚጥል ቢሆን እንጂ:: ወዲያዉም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ማጥመሚያ ቃል ያስወግዳል:: ከዚያም አላህ አናቅጽን ያጠነክራል (ያጸናል):: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّيَجْعَلَ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ فِتْنَةً لِّلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ وَٱلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy53. ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸውና ልቦቻቸው ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል:: በዳዮችም ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ (ውዝግብ) ውስጥ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِيَعْلَمَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَيُؤْمِنُوا۟ بِهِۦ فَتُخْبِتَ لَهُۥ قُلُوبُهُمْ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهَادِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy54. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት እርሱ (ቁርኣን) ከጌታህ የሆነ እውነት መሆኑን እንዲያውቁና በእርሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸዉም በእርሱ እንዲረኩ (ያጠነክራል):: አላህም እነዚያን በትክክል ያመኑትን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا يَزَالُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى مِرْيَةٍ مِّنْهُ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغْتَةً أَوْ يَأْتِيَهُمْ عَذَابُ يَوْمٍ عَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy55. እነዚያ የካዱት ሰዎች ሰዓቲቱ በድንገት እስከምትመጣባቸው ወይም ከደግ ነገር መካን የሆነው ቀን ቅጣት እስከሚመጣባቸው ድረስ በቁርኣን ጉዳይ ከመጠራጠር አያቆሙም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فِى جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy56. በዚያ ቀን ንግስናው የአላህ ብቻ ነው:: በመካከላቸውም ይፈርዳል:: እነዚያም ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَكَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy57. እነዚያም የካዱትና በአናቅጻችንም ያስተባበሉት ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ قُتِلُوٓا۟ أَوْ مَاتُوا۟ لَيَرْزُقَنَّهُمُ ٱللَّهُ رِزْقًا حَسَنًا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ خَيْرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy58. እነዚያም ለአላህ ሀይማኖት ሲሉ የተሰደዱና ከዚያም ሲታገሉ የተገደሉ ወይም የሞቱ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَيُدْخِلَنَّهُم مُّدْخَلًا يَرْضَوْنَهُۥ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَعَلِيمٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy59. የሚወዱትን መግቢያ ገነትን በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህም በእርግጥ አዋቂና ታጋሽ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ وَمَنْ عَاقَبَ بِمِثْلِ مَا عُوقِبَ بِهِۦ ثُمَّ بُغِىَ عَلَيْهِ لَيَنصُرَنَّهُ ٱللَّهُ إِنَّ ٱللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy60. (ነገሩ) ይህ ነው:: ያ በተበደለበት ብጤ (መጠን) የተበቀለና ከዚያ በእርሱ ላይ ግፍ የተዋለበት ሰው አላህ በእርግጥ ይረዳዋል:: አላህ ይቅር ባይና መሓሪ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ يُولِجُ ٱلَّيْلَ فِى ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِى ٱلَّيْلِ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy61. ይህ የሆነው አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ (ቻይ) ፤ ሁሉንም ሰሚ፤ ሁሉንም ተመልካች በመሆኑ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلْبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy62. ይህ የሆነው አላህም ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑና አላህም የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَتُصْبِحُ ٱلْأَرْضُ مُخْضَرَّةً إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy63. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱንና ከዚያ ምድር የምትለመልም መሆኗን አላየህምን? አላህ ፍጹም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْغَنِىُّ ٱلْحَمِيدُ
Amharic Translation - Africa Academy64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አላህ እርሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ وَٱلْفُلْكَ تَجْرِى فِى ٱلْبَحْرِ بِأَمْرِهِۦ وَيُمْسِكُ ٱلسَّمَآءَ أَن تَقَعَ عَلَى ٱلْأَرْضِ إِلَّا بِإِذْنِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy65. አላህ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለእናንተ የገራላችሁ መርከቦችንም በባህር ውስጥ በፈቃዱ የሚንሻለሉ ሲሆኑ የገራላችሁ መሆኑን፤ ሰማይንም በፈቃዱ ካልሆነ በምድር ላይ እንዳትወድቅ የሚይዛት መሆኑን አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهُوَ ٱلَّذِىٓ أَحْيَاكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَكَفُورٌ
Amharic Translation - Africa Academy66. እርሱም ያ ህያው ያደረጋችሁ ነው:: ከዚያም ይገድላችኋል:: ከዚያም ህያው ያደርጋችኋል:: ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِّكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا هُمْ نَاسِكُوهُ فَلَا يُنَٰزِعُنَّكَ فِى ٱلْأَمْرِ وَٱدْعُ إِلَىٰ رَبِّكَ إِنَّكَ لَعَلَىٰ هُدًى مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለየህዝቡ ሁሉ እነርሱ የሚሰሩበት የሆነን ስርዓተ ሃይማኖት አድርገናል:: ስለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ:: ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ:: አንተ በእርግጥ በቅኑ መመርያ ላይ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن جَٰدَلُوكَ فَقُلِ ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም (እንዲህ) በላቸው: «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy69. «አላህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት (ትወዛገቡበት) በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል።» (በላቸው)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ إِنَّ ذَٰلِكَ فِى كِتَٰبٍ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِۦ سُلْطَٰنًا وَمَا لَيْسَ لَهُم بِهِۦ عِلْمٌ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٍ
Amharic Translation - Africa Academy71. ከአላህ ሌላም ምንም ማስረጃን ያላወረደበትንና ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የሌላቸውን ነገር ያመልካሉ፤ ለበዳዮች ምንም ረዳት የላቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ تَعْرِفُ فِى وُجُوهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلْمُنكَرَ يَكَادُونَ يَسْطُونَ بِٱلَّذِينَ يَتْلُونَ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِنَا قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ٱلنَّارُ وَعَدَهَا ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy72. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን የተብራሩ ሆነው በእነርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በአላህ በካዱት ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻን ታውቃለህ:: በእነዚያ አናቅጻችንን በሚያነቡት ላይም በኃይል ሊተናኮሏቸው ይቃረባሉ:: ይልቅ ከዚህ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? እርሷም እሳት ናት:: አላህ ለእነዚያ በርሱ ለካዱት ሰዎች ሁሉ ቀጥሯታል:: መመለሻነቷ ምን ይከፋ በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥٓ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخْلُقُوا۟ ذُبَابًا وَلَوِ ٱجْتَمَعُوا۟ لَهُۥ وَإِن يَسْلُبْهُمُ ٱلذُّبَابُ شَيْـًٔا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلْمَطْلُوبُ
Amharic Translation - Africa Academy73. ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ:: ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ሁሉ ዝንብን ለመፍጠር ቢሰበሰቡ ፈጽሞ መፍጠር እንኳ አይችሉም:: አንዳችንም ነገር ዝንብ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም:: ፈላጊዉም (አምላኪው) ተፈላጊዉም (ተመላኪው) ደከሙ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا قَدَرُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَقَوِىٌّ عَزِيزٌ
Amharic Translation - Africa Academy74. አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም:: አላህ በጣም ሀያልና ሁሉን አሸናፊ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ يَصْطَفِى مِنَ ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ ٱلنَّاسِ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy75. አላህ ከመላእክት ውስጥ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: ከሰዎችም መካከል እንደዚሁ መልዕክተኞችን ይመርጣል:: አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ
Amharic Translation - Africa Academy76. በስተፊታቸዉም ሆነ በስተኋላቸው ያለን ሁሉ ያውቃል:: ወደ አላህም ነገሮች ሁሉ ይመለሳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱرْكَعُوا۟ وَٱسْجُدُوا۟ وَٱعْبُدُوا۟ رَبَّكُمْ وَٱفْعَلُوا۟ ٱلْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy77. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአላህ ቁጣ ትድኑ ዘንድ በስግደታችሁ አጎንብሱ:: በግንባራችሁም ላይ ተደፉ:: (ሩኩዕና ሱጁድ አድርጉ) ጌታችሁንም በትክክል ተገዙት:: በጎንም ነገር ስሩ:: ልትድኑ ይከጀልላችኋልና:: {1}
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَجَٰهِدُوا۟ فِى ٱللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِۦ هُوَ ٱجْتَبَىٰكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلدِّينِ مِنْ حَرَجٍ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَٰهِيمَ هُوَ سَمَّىٰكُمُ ٱلْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ وَفِى هَٰذَا لِيَكُونَ ٱلرَّسُولُ شَهِيدًا عَلَيْكُمْ وَتَكُونُوا۟ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِ فَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱعْتَصِمُوا۟ بِٱللَّهِ هُوَ مَوْلَىٰكُمْ فَنِعْمَ ٱلْمَوْلَىٰ وَنِعْمَ ٱلنَّصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy78. በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ:: እርሱ መርጧችኋል:: በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም:: የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ:: እርሱ (አላህ) ከዚህ በፊት በነበሩት መጽሐፍትም ሆነ በዚህ ቁርኣን ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል። (ይሄዉም) መልዕክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እና እናንተም በሰዎች ላይ መስካሪዎች እንድትሆኑ ነው:: ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም በአግባቡ ለተገቢው ስጡ:: በአላህም ተጠበቁ:: እርሱ ረዳታችሁ ነውና:: እርሱ ምን ያማረ ጠባቂ፤ ምን ያማረም ረዳት ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→