caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Muminoon፣ አንቀጽ 27

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 74 · 23:27

فَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِ أَنِ ٱصْنَعِ ٱلْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمْرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسْلُكْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ ٱثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ ٱلْقَوْلُ مِنْهُمْ وَلَا تُخَٰطِبْنِى فِى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓا۟ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደርሱም (እንዲህ ስንል) ላክን «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችንም ታንኳን ሥራ ት እዛዛችን በመጣና እቶኑ በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከነሱ (ጠፊ በመኾን) ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር፤ አስገባ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታነጋግረኝ፡፡ እነሱ ተሰጣሚዎች ነቸውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70