مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنْ إِلَٰهٍ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy91. አላህ ምንም ልጅን አልያዘም አልወለደም:: ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም:: ሌላ አምላክ በነበረማ አምላኩ ሁሉ የፈጠረውን ነገር በማስተዳደር ከሌላው በተለየ ነበር:: ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በነገሰ ነበር:: አላህ ከሓዲያን እሱን ከሚመጥኑበት መግለጫ ሁሉ ጠራ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡