ሱረቱ Taa-Haa طه
135 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 45
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ طه
Amharic Translation - Africa Academy1. ጧሃ፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْقُرْءَانَ لِتَشْقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን አንድትቸገር ባንተ ላይ አላወረድንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِلَّا تَذْكِرَةً لِّمَن يَخْشَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy3. አላህን ለሚፈራ ሁሉ መገሠጫ ይሆን ዘንድ እንጂ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَنزِيلًا مِّمَّنْ خَلَقَ ٱلْأَرْضَ وَٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلْعُلَى
Amharic Translation - Africa Academy4. ቁርኣን ምድርንና የላይኛዎቹን (የተከበሩ) ሰማያትን ከፈጠረ አምላክ ተወረደ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَى ٱلْعَرْشِ ٱسْتَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy5.እርሱ አዛኙ ጌታ (አር-ረህማን) በዐርሹ ላይ ከፍ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَمَا تَحْتَ ٱلثَّرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy6. በሰማያት፤በምድርና በመካከላቸዉም ያለው ከአፈር በታችም ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن تَجْهَرْ بِٱلْقَوْلِ فَإِنَّهُۥ يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ وَأَخْفَى
Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው።) እርሱ ምስጢርን ከዚያም በጣም የተደበቀንም ያውቃልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ لَهُ ٱلْأَسْمَآءُ ٱلْحُسْنَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy8.አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ለእርሱ መልካሞች የሆኑ አያሌ ስሞች አሉት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَهَلْ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ (ታሪክ) መጥቶሃልን (ደርሶሃልን)?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ رَءَا نَارًا فَقَالَ لِأَهْلِهِ ٱمْكُثُوٓا۟ إِنِّىٓ ءَانَسْتُ نَارًا لَّعَلِّىٓ ءَاتِيكُم مِّنْهَا بِقَبَسٍ أَوْ أَجِدُ عَلَى ٱلنَّارِ هُدًى
Amharic Translation - Africa Academy10. እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ «(እዚህ) ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ፤ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy11. እናም ወደ እርሷ በመጣ ጊዜ (እንዲህ) በማለት ተጠራ: «ሙሳ ሆይ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنِّىٓ أَنَا۠ رَبُّكَ فَٱخْلَعْ نَعْلَيْكَ إِنَّكَ بِٱلْوَادِ ٱلْمُقَدَّسِ طُوًى
Amharic Translation - Africa Academy12. «እኔ ጌታህ ነኝ። ጫማዎችህን አውልቅ፤ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَا ٱخْتَرْتُكَ فَٱسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy13. «እኔም መረጥኩህ ስለ ሆነም የሚወረድልህን ነገር በደንብ አዳምጥ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
Amharic Translation - Africa Academy14. «እኔ አላህ ነኝ። ያለ እኔ ትክክለኛ አምላክ የለምና እኔን ብቻ ተገዛኝ:: ሶላትንም እኔን ለማውሳት በአግባቡ ስገድ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلسَّاعَةَ ءَاتِيَةٌ أَكَادُ أُخْفِيهَا لِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا تَسْعَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy15. «ነፍስ ሁሉ በምትሰራው ነገር ትመነዳ ዘንድ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት። የትንሳኤውን ወሬ ልደብቃት እቀርባለሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَا يَصُدَّنَّكَ عَنْهَا مَن لَّا يُؤْمِنُ بِهَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَتَرْدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy16. (ሙሳ ሆይ!) «በእርሷ የማያምንና ዝንባሌውን የሚከተል ሰው ሁሉ ከእርሷ አያግድህ ትጠፋለህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَا تِلْكَ بِيَمِينِكَ يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy17. (ሙሳ ሆይ!) «ይህችም በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድን ናት?» (ተባለ)።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ هِىَ عَصَاىَ أَتَوَكَّؤُا۟ عَلَيْهَا وَأَهُشُّ بِهَا عَلَىٰ غَنَمِى وَلِىَ فِيهَا مَـَٔارِبُ أُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy18. «እርሷ በትሬ ናት:: በእርሷም እደገፍባታለሁ:: በእርሷም ለፍየሎቼ ቅጠልን አረግፍባታለሁ:: በእርሷ ሌሎች ጉዳዮችም አሉኝ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَلْقِهَا يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy19. አላህም «ሙሳ ሆይ! እስቲ ጣላት።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَلْقَىٰهَا فَإِذَا هِىَ حَيَّةٌ تَسْعَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy20.ሙሳም ጣላትና፤ ወዲያዉም እርሷ የምትሮጥ እባብ ሆነች::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ خُذْهَا وَلَا تَخَفْ سَنُعِيدُهَا سِيرَتَهَا ٱلْأُولَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy21.አላህም አለው: «ሙሳ ሆይ! ያዛት አትፍራም ወደ መጀመሪያ ጠባይዋ እንመልሳታለን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱضْمُمْ يَدَكَ إِلَىٰ جَنَاحِكَ تَخْرُجْ بَيْضَآءَ مِنْ غَيْرِ سُوٓءٍ ءَايَةً أُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy22. «እጅህንም ወደ ብብትህ አስገባ:: ሌላ ተዓምር ስትሆን ያለ ምንም ችግር ነጭ ሆና ትወጣለችና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لِنُرِيَكَ مِنْ ءَايَٰتِنَا ٱلْكُبْرَى
Amharic Translation - Africa Academy23. (ሙሳ ሆይ!) «ከተዓምራቶቻችን ታላቋን እናሳይህ ዘንድ ይህን ፈጸምን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy24. (ሙሳ ሆይ!) «ወደ ፈርዖን ሂድ:: እርሱ ወሰን (ድንበር) አልፏልና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ ٱشْرَحْ لِى صَدْرِى
Amharic Translation - Africa Academy25. ሙሳም አለ: «ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسِّرْ لِىٓ أَمْرِى
Amharic Translation - Africa Academy26. «ጉዳዬንም አግራልኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱحْلُلْ عُقْدَةً مِّن لِّسَانِى
Amharic Translation - Africa Academy27. «የምላሴን መኮላተፍም አስወግድልኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَفْقَهُوا۟ قَوْلِى
Amharic Translation - Africa Academy28. «ንግግሬን ይረዱ ዘንድ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱجْعَل لِّى وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِى
Amharic Translation - Africa Academy29. «ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
هَٰرُونَ أَخِى
Amharic Translation - Africa Academy30. «ወንድሜን ሃሩንን
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱشْدُدْ بِهِۦٓ أَزْرِى
Amharic Translation - Africa Academy31. «ኃይሌንም በእርሱ አበርታልኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَشْرِكْهُ فِىٓ أَمْرِى
Amharic Translation - Africa Academy32. «በነገሬም አጋራው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَىْ نُسَبِّحَكَ كَثِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy33. «በብዛት እንድናጠራህና
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَنَذْكُرَكَ كَثِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy34. «በብዛት እንድናወሳህ
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّكَ كُنتَ بِنَا بَصِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy35. «አንተ በእኛ ነገር አዋቂ ነህና።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ قَدْ أُوتِيتَ سُؤْلَكَ يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy36. አላህም አለ: «ሙሳ ሆይ! ልመናህ በእርግጥ ተቀባይነትን አገኝቷል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَيْكَ مَرَّةً أُخْرَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy37. «ሙሳ ሆይ! በሌላም ጊዜ ባንተ ላይ በእርግጥ ውለታን ውለናል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰٓ أُمِّكَ مَا يُوحَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy38. «ለእናትህ በራእይ ባሳወቅን ጊዜ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَنِ ٱقْذِفِيهِ فِى ٱلتَّابُوتِ فَٱقْذِفِيهِ فِى ٱلْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ ٱلْيَمُّ بِٱلسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّى وَعَدُوٌّ لَّهُۥ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّى وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِىٓ
Amharic Translation - Africa Academy39. «‹ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገቢው እርሱንም (ሳጥኑን) በባህር ላይ ጣይው፤ ባህሩም በዳርቻው ይጥለዋል (ይተፋዋል):: ለእኔም ለእርሱም ጠላት የሆነ ሰው ይይዘዋልና› በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)። ልትወደድና በዐይኔ እይታ (በእኔም ጥበቃ) ታድግ ዘንድ ባንተ ላይም ከእኔ የሆነ መወደድን ጣልኩብህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِذْ تَمْشِىٓ أُخْتُكَ فَتَقُولُ هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ مَن يَكْفُلُهُۥ فَرَجَعْنَٰكَ إِلَىٰٓ أُمِّكَ كَىْ تَقَرَّ عَيْنُهَا وَلَا تَحْزَنَ وَقَتَلْتَ نَفْسًا فَنَجَّيْنَٰكَ مِنَ ٱلْغَمِّ وَفَتَنَّٰكَ فُتُونًا فَلَبِثْتَ سِنِينَ فِىٓ أَهْلِ مَدْيَنَ ثُمَّ جِئْتَ عَلَىٰ قَدَرٍ يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy40. «እህትህ በምትሄድና ‹የሚያሳድገውን ሰው ላመላክታችሁን?› ባለች ጊዜ (መወደድን ጣልኩብህ):: ወደ እናትህም ዓይኗ እንዲረጋና እርሷ እንዳታዝንም መለስንህ:: ነፍስንም ገደልክ ከጭንቅም አዳንንህ:: ፈተናዎችንም ፈተንህ:: በመድየን ቤተሰቦችም ውስጥ ብዙ ዓመታትን ተቀመጥክ:: ከዚያ ሙሳ ሆይ! በተወሰነ ጊዜ ላይ መጣህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِى
Amharic Translation - Africa Academy41. «ለራሴም ለመልዕክተኝነት መረጥኩህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱذْهَبْ أَنتَ وَأَخُوكَ بِـَٔايَٰتِى وَلَا تَنِيَا فِى ذِكْرِى
Amharic Translation - Africa Academy42. «አንተና ወንድምህ በተዓምራቴ ሆናችሁ ሂዱ:: እኔንም ከማውሳትም አትቦዝኑ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱذْهَبَآ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy43. «ወደ ፈርዖን ሂዱ:: እርሱ ወሰን አልፏልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقُولَا لَهُۥ قَوْلًا لَّيِّنًا لَّعَلَّهُۥ يَتَذَكَّرُ أَوْ يَخْشَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy44. «እርሱ ምን አልባትም ይገሰጥ ወይም ይፈራ ዘንድ:: ለእርሱ ለስላሳን ቃል ተናገሩት።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَا رَبَّنَآ إِنَّنَا نَخَافُ أَن يَفْرُطَ عَلَيْنَآ أَوْ أَن يَطْغَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy45. «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ክፋት በመስራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَا تَخَافَآ إِنَّنِى مَعَكُمَآ أَسْمَعُ وَأَرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy46. አላህም አለ: «እኔ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ:: የሚለውንም ሁሉ እሰማለሁ። የሚፈጸመዉንም አያለሁም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأْتِيَاهُ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرْسِلْ مَعَنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَلَا تُعَذِّبْهُمْ قَدْ جِئْنَٰكَ بِـَٔايَةٍ مِّن رَّبِّكَ وَٱلسَّلَٰمُ عَلَىٰ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلْهُدَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy47. እናም ወደ እርሱም ሂዱና (እንዲህ) በሉት: ‹እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነንና የኢስራኢልን ልጆች ሁሉ ከእኛ ጋር ልቀቅ። አታሰቃያቸዉም:: ከጌታህ በሆነው ተዓምር በእርግጥ መጥተንሃልና:: ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّا قَدْ أُوحِىَ إِلَيْنَآ أَنَّ ٱلْعَذَابَ عَلَىٰ مَن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy48. «‹እነሆ የአላህ ቅጣት እውነትን ባስተባበለና እምቢ ባለ ሰው ላይ እንደሆነ በእርግጥ አያሌ መልዕክት ተወረደልን።› በሉት።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَمَن رَّبُّكُمَا يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy49. ፈርዖንም «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبُّنَا ٱلَّذِىٓ أَعْطَىٰ كُلَّ شَىْءٍ خَلْقَهُۥ ثُمَّ هَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy50. «ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚያስፈልገውን ቅርጹንና ባህሪውን የሰጠው ከዚያም ሁሉንም ለተፈጠረለት የመራው ነው።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَمَا بَالُ ٱلْقُرُونِ ٱلْأُولَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy51. ፈርዖንም «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ህዝቦች ሁኔታስ ምንድን ነው?» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى فِى كِتَٰبٍ لَّا يَضِلُّ رَبِّى وَلَا يَنسَى
Amharic Translation - Africa Academy52. ሙሳም «የዚህ ዕውቀት እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው:: ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ مَهْدًا وَسَلَكَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَخْرَجْنَا بِهِۦٓ أَزْوَٰجًا مِّن نَّبَاتٍ شَتَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy53. ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መንገድን ያገራላችሁ ውሃንም ከሰማይ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም ከተለያየ በቃይ ዓይነቶችን አወጣንላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلُوا۟ وَٱرْعَوْا۟ أَنْعَٰمَكُمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّأُو۟لِى ٱلنُّهَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy54. ለራሳችሁ ብሉ:: እንስሳዎቻችሁንም አግጡ:: (ባዮች ሆነን አወጣንላችሁ።) በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ ተዐምራት አለበት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مِنْهَا خَلَقْنَٰكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy55. (ሰዎች ሆይ!) ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ:: ወደ እርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን:: ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَرَيْنَٰهُ ءَايَٰتِنَا كُلَّهَا فَكَذَّبَ وَأَبَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy56.ተዓምራቶቻችንንም ሁሏንም ለፈርዖን በእርግጥ አሳየነው:: አስተባበለም:: እምቢም አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ أَجِئْتَنَا لِتُخْرِجَنَا مِنْ أَرْضِنَا بِسِحْرِكَ يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy57. አለም: «ሙሳ ሆይ! ከምድራችን በድግምትህ ልታወጣን መጣህብን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَنَأْتِيَنَّكَ بِسِحْرٍ مِّثْلِهِۦ فَٱجْعَلْ بَيْنَنَا وَبَيْنَكَ مَوْعِدًا لَّا نُخْلِفُهُۥ نَحْنُ وَلَآ أَنتَ مَكَانًا سُوًى
Amharic Translation - Africa Academy58. «መሰሉንም ድግምት እናመጣብሃለን:: በእኛና ባንተም መካከል እኛም አንተም የማንጥሰው የሆነ ቀጠሮን በመካከለኛ ስፍራ አድርግልን።» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ مَوْعِدُكُمْ يَوْمُ ٱلزِّينَةِ وَأَن يُحْشَرَ ٱلنَّاسُ ضُحًى
Amharic Translation - Africa Academy59.ሙሳም: «ቀጠሯችሁ ያ የማጌጫው የበአሉ ቀን ነው። ሰዎችም ረፋድ ላይ እንዲሰበሰቡ ይሁን።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَوَلَّىٰ فِرْعَوْنُ فَجَمَعَ كَيْدَهُۥ ثُمَّ أَتَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy60. ፈርዖንም ዞረ:: ተንኮሉን ሰበሰበ:: ከዚያ መጣ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ وَيْلَكُمْ لَا تَفْتَرُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا فَيُسْحِتَكُم بِعَذَابٍ وَقَدْ خَابَ مَنِ ٱفْتَرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy61.ሙሳም ለእነርሱ: «ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ:: በቅጣት ያጠፋችኋልና:: የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَنَٰزَعُوٓا۟ أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy62. (ድግምተኞቹ) በመካከላቸውም ነገራቸውን ተጨቃጨቁ፡፡ ውይይትንም ደበቁ፡፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ إِنْ هَٰذَٰنِ لَسَٰحِرَٰنِ يُرِيدَانِ أَن يُخْرِجَاكُم مِّنْ أَرْضِكُم بِسِحْرِهِمَا وَيَذْهَبَا بِطَرِيقَتِكُمُ ٱلْمُثْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy63. አሉም: «እነዚህ በእርግጥ ደጋሚዎች ናቸው:: ከምድራችሁ በድግምታቸው ሊያወጧችሁ በላጪቱንም መንገዳችሁን ሊያስወግዱባችሁ ይሻሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَجْمِعُوا۟ كَيْدَكُمْ ثُمَّ ٱئْتُوا۟ صَفًّا وَقَدْ أَفْلَحَ ٱلْيَوْمَ مَنِ ٱسْتَعْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy64. «ተንኮላችሁንም አጠንክሩ:: ከዚያም ተሰልፋችሁ ኑ:: ዛሬ ያሸነፈም ሰው ምኞቱን አገኘ።» ተባባሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلْقِىَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَلْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy65. «ሙሳ ሆይ! በመጀመሪያ ትጥላለህ ወይስ እኛ እንጣል? (ምረጥ)» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ بَلْ أَلْقُوا۟ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy66. ሙሳም «እናንተ በመጀመሪያ ጣሉ።» አላቸው። ጣሉም:: ወዲያዉም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ የሚሮጡ እባቦች ሆነው (መስለው) ወደ እርሱ ተመሰሉበት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَوْجَسَ فِى نَفْسِهِۦ خِيفَةً مُّوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy67.ሙሳም በውስጡ ፍርሃት አደረበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْنَا لَا تَخَفْ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْأَعْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy68. አልነውም: «አትፍራ። የበላዩ አንተ ነህና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَلْقِ مَا فِى يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوٓا۟ إِنَّمَا صَنَعُوا۟ كَيْدُ سَٰحِرٍ وَلَا يُفْلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy69. «በቀኝ እጅህ ያለችውን ብትር ጣል:: ያንን የሰሩትን ሁሉ ትውጣለችና። ያ የሰሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ብቻ ነውና:: ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናዉም::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأُلْقِىَ ٱلسَّحَرَةُ سُجَّدًا قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِرَبِّ هَٰرُونَ وَمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy70. ድግምተኞቹም ሱጁድ ወረዱ: «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን።» አሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ءَامَنتُمْ لَهُۥ قَبْلَ أَنْ ءَاذَنَ لَكُمْ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِى عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحْرَ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَٰفٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِى جُذُوعِ ٱلنَّخْلِ وَلَتَعْلَمُنَّ أَيُّنَآ أَشَدُّ عَذَابًا وَأَبْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy71. (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁለትን! እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ መሪያችሁ ነው:: እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (በማናጋት) ግራንና ቀኝን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ:: በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ:: የማንኛችን ቅጣት በጣም ብርቱና የሚቆይ መሆኑን በዚያ ጊዜ ታውቃላችሁ።» አላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ لَن نُّؤْثِرَكَ عَلَىٰ مَا جَآءَنَا مِنَ ٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلَّذِى فَطَرَنَا فَٱقْضِ مَآ أَنتَ قَاضٍ إِنَّمَا تَقْضِى هَٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَآ
Amharic Translation - Africa Academy72. አሉትም: «ከመጡልን ተዓምራትና ከዚያ ከፈጠረን አምላክ ፈጽሞ አናስበልጥህም:: እናም የምትፈርደውን ፍረድ:: የምትፈርደው በዚህች በአነስተኛይቱ ህይወት ብቻ ላይ ነውና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّآ ءَامَنَّا بِرَبِّنَا لِيَغْفِرَ لَنَا خَطَٰيَٰنَا وَمَآ أَكْرَهْتَنَا عَلَيْهِ مِنَ ٱلسِّحْرِ وَٱللَّهُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy73. «ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም እንድንፈጽመው ያስገደድከንን ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል:: አላህ በጣም በላጭ ነው:: ቅጣቱም ሆነ ምንዳው በጣም የሚዘወትር ነው።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّهُۥ مَن يَأْتِ رَبَّهُۥ مُجْرِمًا فَإِنَّ لَهُۥ جَهَنَّمَ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy74. ከሃዲ ሆኖ ወደ ጌታው የሚመጣ (የሚሞት) ሰው ሁሉ ለእርሱ ገሀነም አለችለት:: በውስጧም አይሞትም ህያዉም አይሆንም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يَأْتِهِۦ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلدَّرَجَٰتُ ٱلْعُلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy75.እነዚያ በጎ ስራዎችን የሰሩና አማኝ ሆነው ወደ ጌታቸው የመጡ ሰዎች ደግሞ እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
جَنَّٰتُ عَدْنٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَذَٰلِكَ جَزَآءُ مَن تَزَكَّىٰ
Amharic Translation - Africa Academy76.ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አሏቸው:: ይህም አይነቱ ክፍያ ለተጥራራ ሁሉ ምንዳው ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِى فَٱضْرِبْ لَهُمْ طَرِيقًا فِى ٱلْبَحْرِ يَبَسًا لَّا تَخَٰفُ دَرَكًا وَلَا تَخْشَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy77. ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ሂድ:: ለእነርሱም በባህር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው:: ፈርዖን ያገኘኛል ብለህ አትፍራ:: ከመስመጥም አትጨነቅ።» ስንል በእርግጥ ላክንበት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ بِجُنُودِهِۦ فَغَشِيَهُم مِّنَ ٱلْيَمِّ مَا غَشِيَهُمْ
Amharic Translation - Africa Academy78. ፈርዖን ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ ተከተላቸው:: ከባህሩም የሚሸፍን ነገር ሸፈናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَضَلَّ فِرْعَوْنُ قَوْمَهُۥ وَمَا هَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy79.ፈርዖንም ህዝቦቹን አሳሳታቸው:: ቅኑንም መንገድ አልመራቸዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ قَدْ أَنجَيْنَٰكُم مِّنْ عَدُوِّكُمْ وَوَٰعَدْنَٰكُمْ جَانِبَ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنَ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy80. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ:: በጡር ተራራም ቀኝ ጎን ላይ ቀጠሮ አደረግንላችሁ። በእናንተም ላይ መናንና ሰልዋን (ድርጭት) አወረድንላችሁ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كُلُوا۟ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقْنَٰكُمْ وَلَا تَطْغَوْا۟ فِيهِ فَيَحِلَّ عَلَيْكُمْ غَضَبِى وَمَن يَحْلِلْ عَلَيْهِ غَضَبِى فَقَدْ هَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy81. ከሰጠናችሁ ሲሳይ ከመልካሙ ብሉ:: በእርሱም ወሰንን አትለፉ:: ቁጣዬ በእናንተ ላይ ይወርድባችኋልና:: ቁጣዬ የሚወርድበት ሁሉ በእርግጥ ይጠፋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِنِّى لَغَفَّارٌ لِّمَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًا ثُمَّ ٱهْتَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy82.እኔም ለተጸጸተ ላመነም መልካምንም ለሰራ ከዚያ ለተመራ ሁሉ በእርግጥ መሓሪ ነኝ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَآ أَعْجَلَكَ عَن قَوْمِكَ يَٰمُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy83. «ሙሳ ሆይ! ከህዝቦችህ ምን አስቸኮለህ?» ተባለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ هُمْ أُو۟لَآءِ عَلَىٰٓ أَثَرِى وَعَجِلْتُ إِلَيْكَ رَبِّ لِتَرْضَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy84. «እነርሱ እነዚህ በዱካዬ ላይ ያሉ ናቸው:: ጌታዬ ሆይ! ትወድልኝ ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَإِنَّا قَدْ فَتَنَّا قَوْمَكَ مِنۢ بَعْدِكَ وَأَضَلَّهُمُ ٱلسَّامِرِىُّ
Amharic Translation - Africa Academy85.(አላህም) «እኛም ካንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈተንን:: ሳምራዊዉም አሳሳታቸው።» አለው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَرَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوْمِهِۦ غَضْبَٰنَ أَسِفًا قَالَ يَٰقَوْمِ أَلَمْ يَعِدْكُمْ رَبُّكُمْ وَعْدًا حَسَنًا أَفَطَالَ عَلَيْكُمُ ٱلْعَهْدُ أَمْ أَرَدتُّمْ أَن يَحِلَّ عَلَيْكُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَخْلَفْتُم مَّوْعِدِى
Amharic Translation - Africa Academy86. ሙሳም ወደ ሰዎች የተቆጣና ያዘነ ሆኖ ተመለሰ:: «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁ መልካም ተስፋን አልቀጠራችሁምን? ቀጠሮው በእናንተ ላይ ረዘመባችሁን? ወይስ በእናንተ ላይ ከጌታችሁ ቅጣት ሊወርድባችሁ ፈለጋችሁና ቃል ኪዳኔን አፈረሳችሁ?» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ مَآ أَخْلَفْنَا مَوْعِدَكَ بِمَلْكِنَا وَلَٰكِنَّا حُمِّلْنَآ أَوْزَارًا مِّن زِينَةِ ٱلْقَوْمِ فَقَذَفْنَٰهَا فَكَذَٰلِكَ أَلْقَى ٱلسَّامِرِىُّ
Amharic Translation - Africa Academy87. «ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም:: ግን እኛ ከህዝቦች ጌጥ ሸክሞችን ተጫን:: በእሳት ላይ ጣልናትም:: ሳምራዊዉም እንደዚሁ አብሮን ጣለ።» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُۥ خُوَارٌ فَقَالُوا۟ هَٰذَآ إِلَٰهُكُمْ وَإِلَٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِىَ
Amharic Translation - Africa Academy88. ለእነርሱም የመጓጎር ባህሪ ያለውን ጥጃን (መሰል) አካልን አወጣላቸው። «ተከታዮቹ ሆይ! ይህ የእናንተም ሆነ የሙሳ አምላክ ነው:: ግን ረሳው እንጂ።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَا يَرَوْنَ أَلَّا يَرْجِعُ إِلَيْهِمْ قَوْلًا وَلَا يَمْلِكُ لَهُمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا
Amharic Translation - Africa Academy89.ወደ እነርሱ ንግግርን የማይመልስ ለእነርሱም ጉዳትንና ጥቅምን የማይችል መሆኑን አያዩምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ قَالَ لَهُمْ هَٰرُونُ مِن قَبْلُ يَٰقَوْمِ إِنَّمَا فُتِنتُم بِهِۦ وَإِنَّ رَبَّكُمُ ٱلرَّحْمَٰنُ فَٱتَّبِعُونِى وَأَطِيعُوٓا۟ أَمْرِى
Amharic Translation - Africa Academy90-.ከዚያ በፊት ሀሩንም በእርግጥ አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! ይህ በእርሱ የተሞከራችሁበት ብቻ ነው:: ጌታችሁም አር-ረህማን ነው:: ተከተሉኝም፤ ትእዛዜንም ስሙ።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ لَن نَّبْرَحَ عَلَيْهِ عَٰكِفِينَ حَتَّىٰ يَرْجِعَ إِلَيْنَا مُوسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy91. «ሙሳ ወደ እኛ እስከሚመለስ በእርሱ መገዛት ላይ ከመቆየት ፈጽሞ አንወገድም።» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَٰهَٰرُونُ مَا مَنَعَكَ إِذْ رَأَيْتَهُمْ ضَلُّوٓا۟
Amharic Translation - Africa Academy92- ሙሳም አለ፡- «ሃሩን ሆይ! ተሳስተው ባየሃቸው ጊዜ ምን ከለከለህ?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَلَّا تَتَّبِعَنِ أَفَعَصَيْتَ أَمْرِى
Amharic Translation - Africa Academy93. «እኔን ከመከተል? ትእዛዜን ጣስክን?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ يَبْنَؤُمَّ لَا تَأْخُذْ بِلِحْيَتِى وَلَا بِرَأْسِىٓ إِنِّى خَشِيتُ أَن تَقُولَ فَرَّقْتَ بَيْنَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَلَمْ تَرْقُبْ قَوْلِى
Amharic Translation - Africa Academy94. «ሃሩን የእናቴ ልጅ ሆይ! ፂሜንም ሆነ ራሴን አትያዝ:: እኔ ‹በኢስራኢል ልጆች መካከል ለያየህ ቃሌንም አልጠበክም› ማለትህን ፈራሁና ነው።» አለው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَمَا خَطْبُكَ يَٰسَٰمِرِىُّ
Amharic Translation - Africa Academy95. ሙሳም «ሳምራዊው ሆይ! ነገርህ ምንድን ነው?» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ بَصُرْتُ بِمَا لَمْ يَبْصُرُوا۟ بِهِۦ فَقَبَضْتُ قَبْضَةً مِّنْ أَثَرِ ٱلرَّسُولِ فَنَبَذْتُهَا وَكَذَٰلِكَ سَوَّلَتْ لِى نَفْسِى
Amharic Translation - Africa Academy96. ሳምራዊውም: «እነርሱ ያላዩትን ነገር አየሁ:: ከመልዕክተኛው ፈረስ ኮቴ ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ:: በቅርጹ ላይ ጣልኳትም:: ልክ እንደዚሁ ነፍሴ ሸለመችልኝ።» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ فَٱذْهَبْ فَإِنَّ لَكَ فِى ٱلْحَيَوٰةِ أَن تَقُولَ لَا مِسَاسَ وَإِنَّ لَكَ مَوْعِدًا لَّن تُخْلَفَهُۥ وَٱنظُرْ إِلَىٰٓ إِلَٰهِكَ ٱلَّذِى ظَلْتَ عَلَيْهِ عَاكِفًا لَّنُحَرِّقَنَّهُۥ ثُمَّ لَنَنسِفَنَّهُۥ فِى ٱلْيَمِّ نَسْفًا
Amharic Translation - Africa Academy97. ሙሳም ለሳምራዊው አለው: «ሂድ። በህይወትህ ላየኸው ሰው ሁሉ ‹መነካካት የለም› እያልክ ኑር:: ላንተም ፈጽሞ የማትቀር ቀጠሮ አለህ:: ወደ እዚያዉም በእርሱ ላይ ተገዢው ሆነህ ወደ ቆየህበት አምላክህ ተመልከት:: በእርግጥ እናቃጥለዋለን:: ከዚያም በባህሩ ውስጥ እንበትነዋለን::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَآ إِلَٰهُكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَسِعَ كُلَّ شَىْءٍ عِلْمًا
Amharic Translation - Africa Academy98.(ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ያ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነው አላህ ብቻ ነው:: እውቀቱ ሁሉን ነገር አዳረሰ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ مَا قَدْ سَبَقَ وَقَدْ ءَاتَيْنَٰكَ مِن لَّدُنَّا ذِكْرًا
Amharic Translation - Africa Academy99. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች ባንተ ላይ እንተርካለን፤ ከእኛም ዘንድ ቁርኣንን በእርግጥ ሰጠንህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَّنْ أَعْرَضَ عَنْهُ فَإِنَّهُۥ يَحْمِلُ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وِزْرًا
Amharic Translation - Africa Academy100.ከእርሱ ያፈገፈገ ሰው እርሱ በትንሳኤ ቀን ከባድን ቅጣት ይሸከማል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
خَٰلِدِينَ فِيهِ وَسَآءَ لَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ حِمْلًا
Amharic Translation - Africa Academy101.በእርሱ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው ይሸከማሉ:: በትንሳኤ ቀን ለእነርሱ እጣ ፈንታ የሆነው ሸክም ከፋ!
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَ يُنفَخُ فِى ٱلصُّورِ وَنَحْشُرُ ٱلْمُجْرِمِينَ يَوْمَئِذٍ زُرْقًا
Amharic Translation - Africa Academy102. በቀንዱ በሚነፋ ቀን ሸክማቸው ከፋ:: ከሓዲያን በዚያ ቀን ዓይኖቻቸው ሰማያዊዎች ሆነው እንሰበስባቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَتَخَٰفَتُونَ بَيْنَهُمْ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا عَشْرًا
Amharic Translation - Africa Academy103. «አስርን (ቀን) እንጂ አልቆያችሁም።» በመባባል በመካከላቸው ይንሾካሾካሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ إِذْ يَقُولُ أَمْثَلُهُمْ طَرِيقَةً إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا يَوْمًا
Amharic Translation - Africa Academy104. በሃሳብ ቀጥተኛቸው «አንድን ቀን እንጂ አልቆያችሁም።» በሚል ጊዜ የሚሉትን ነገር እኛ አዋቂዎች ነን።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْجِبَالِ فَقُلْ يَنسِفُهَا رَبِّى نَسْفًا
Amharic Translation - Africa Academy105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጋራዎች ይጠይቁሃልና (እንዲህ) በላቸው: «ጌታዬ መበተንን ይበትናቸዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَيَذَرُهَا قَاعًا صَفْصَفًا
Amharic Translation - Africa Academy106. «ትክክል ሜዳም ሆና ይተዋታል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
لَّا تَرَىٰ فِيهَا عِوَجًا وَلَآ أَمْتًا
Amharic Translation - Africa Academy107. «በእርሷ ዝቅታና ከፍታን ፈጽሞ አታይም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَئِذٍ يَتَّبِعُونَ ٱلدَّاعِىَ لَا عِوَجَ لَهُۥ وَخَشَعَتِ ٱلْأَصْوَاتُ لِلرَّحْمَٰنِ فَلَا تَسْمَعُ إِلَّا هَمْسًا
Amharic Translation - Africa Academy108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ ቀን ለመሰብሰብ ጠሪውን ምንም እንከን የሌለውን ተጣሪ ይከተላሉ:: ድምፆችም ሁሉ ለአር-ረህማን ጸጥ ይላሉ:: ስለዚህ (የኮቴ) ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحْمَٰنُ وَرَضِىَ لَهُۥ قَوْلًا
Amharic Translation - Africa Academy109.በዚያ ቀን ለእርሱ አር-ረህማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ብቻ ቢሆን እንጂ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِۦ عِلْمًا
Amharic Translation - Africa Academy110. በስተፊታቸው ያለውንም ሆነ በስተኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል:: በእርሱ ላይ ግን ማንም በእውቀቱ አያካብብም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَعَنَتِ ٱلْوُجُوهُ لِلْحَىِّ ٱلْقَيُّومِ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا
Amharic Translation - Africa Academy111. ፊቶችም ሁሉ ህያውና የሁሉ አስተናባሪ ለሆነው አላህ ተዋረዱ:: በደልንም የተሸከመ በእርግጥ ከሰረ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن يَعْمَلْ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا يَخَافُ ظُلْمًا وَلَا هَضْمًا
Amharic Translation - Africa Academy112. አማኝ ሆኖ መልካም ስራዎችን የሰራ በደልንም ሆነ መጉደልን አይፈራም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَانًا عَرَبِيًّا وَصَرَّفْنَا فِيهِ مِنَ ٱلْوَعِيدِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ أَوْ يُحْدِثُ لَهُمْ ذِكْرًا
Amharic Translation - Africa Academy113.ልክ እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ሆኖ አወረድነው:: አላህን ይፈሩ ዘንድ ወይም ለእነርሱ ግሣጼን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ وَلَا تَعْجَلْ بِٱلْقُرْءَانِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰٓ إِلَيْكَ وَحْيُهُۥ وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًا
Amharic Translation - Africa Academy114. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኛው ንጉስ አላህ ከሓዲያን ከሚሉት ነገር ሁሉ ላቀ:: ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት ቁርኣንን በማንበብ አትቸኩል:: «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ።» በልም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِىَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُۥ عَزْمًا
Amharic Translation - Africa Academy115. ወደ አደምም ከዚህ በፊት ቃል ኪዳንን በእርግጥ አወረድንና ረሳ:: ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَٰٓئِكَةِ ٱسْجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ أَبَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy116.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ።» ባልን ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እነርሱም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሰገዱ:: እሱማ እምቢ አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَقُلْنَا يَٰٓـَٔادَمُ إِنَّ هَٰذَا عَدُوٌّ لَّكَ وَلِزَوْجِكَ فَلَا يُخْرِجَنَّكُمَا مِنَ ٱلْجَنَّةِ فَتَشْقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy117.ከዚያም አልን: «አደም ሆይ! ይህ ላንተም ለሚስትህም በእርግጥ ጠላት ነው:: ስለዚህ ከገነት አያውጣችሁ፤ ትለፋለህና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ لَكَ أَلَّا تَجُوعَ فِيهَا وَلَا تَعْرَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy118.(አደም ሆይ!) «ላንተ በእርሷ ውስጥ አለመራብና አለመታረዝ አለህ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأَنَّكَ لَا تَظْمَؤُا۟ فِيهَا وَلَا تَضْحَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy119. «አንተም ከእርሷ ውስጥ አትጠማም:: በጸሐይም አትተኮስም።»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ ٱلشَّيْطَٰنُ قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ ٱلْخُلْدِ وَمُلْكٍ لَّا يَبْلَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy120. ሰይጣን ወደ እርሱ (አደም) « አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግስናም ላይ ላመላክትህን?» በማለት ጎተጎተ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy121.ከእርሷም በሉ:: ለእነርሱም ሀፍረተ ገላቸው ተገለጸች:: ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር:: አደምም የጌታውን ትእዛዝ ረስቶ ጣሰ:: ተሳሳተም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ثُمَّ ٱجْتَبَٰهُ رَبُّهُۥ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy122. ከዚያም ጌታው መረጠው:: ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው:: መራዉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ ٱهْبِطَا مِنْهَا جَمِيعًۢا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّى هُدًى فَمَنِ ٱتَّبَعَ هُدَاىَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy123.አላህም አላቸው፡- «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን (አደምና ሐዋ) ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ:: ከእኔ የሆነ መመሪያ ቢመጣላችሁ መመሪያየን የተከተለ ሁሉ አይሳሳትም:: አይቸገርምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِى فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةً ضَنكًا وَنَحْشُرُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَعْمَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy124. «ከግሳጼዬ የዞረ ግን በዚህች ዓለም ጠባብ ኑሮ አለው:: በትንሳኤ ቀንም ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን::»
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ رَبِّ لِمَ حَشَرْتَنِىٓ أَعْمَىٰ وَقَدْ كُنتُ بَصِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy125. «ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ:: በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስሆን» አለ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ ءَايَٰتُنَا فَنَسِيتَهَا وَكَذَٰلِكَ ٱلْيَوْمَ تُنسَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy126. «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: ተዓምራቶቻችን መጡልህና ተውካቸውም:: ልክ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ።» ይለዋል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى مَنْ أَسْرَفَ وَلَمْ يُؤْمِنۢ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ وَلَعَذَابُ ٱلْـَٔاخِرَةِ أَشَدُّ وَأَبْقَىٰٓ
Amharic Translation - Africa Academy127.እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አናቅጽ ያላመነን እንቀጣዋለን:: የመጨረሻይቱ ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱና ለሁልጊዜም ዘውታሪ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَفَلَمْ يَهْدِ لَهُمْ كَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّنَ ٱلْقُرُونِ يَمْشُونَ فِى مَسَٰكِنِهِمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّأُو۟لِى ٱلنُّهَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ቁረይሾች) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሆነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልዕክቶች አሉበት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِن رَّبِّكَ لَكَانَ لِزَامًا وَأَجَلٌ مُّسَمًّى
Amharic Translation - Africa Academy129.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ አሁኑኑ የሚይዛቸው ይሆን ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ ٱلشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا وَمِنْ ءَانَآئِ ٱلَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ ٱلنَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy130. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) በሚሉትም ሁሉ ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመግባቷም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው:: ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው:: በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَا تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعْنَا بِهِۦٓ أَزْوَٰجًا مِّنْهُمْ زَهْرَةَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا لِنَفْتِنَهُمْ فِيهِ وَرِزْقُ رَبِّكَ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy131.ዐይኖችህን ከሰዎች የተወሰኑ ክፍሎችን ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት ወደ ቅርቢቱ ህይወት ጌጦች አትዘርጋ:: የጌታህ ሲሳይ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱصْطَبِرْ عَلَيْهَا لَا نَسْـَٔلُكَ رِزْقًا نَّحْنُ نَرْزُقُكَ وَٱلْعَٰقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy132.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤተሰብህንም በሶላት ላይ እዘዝ:: አንተም በእርሷ ላይ ዘውትር:: ሲሳይን አንጠይቅህም:: እኛ እንሰጥሃለን:: መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالُوا۟ لَوْلَا يَأْتِينَا بِـَٔايَةٍ مِّن رَّبِّهِۦٓ أَوَلَمْ تَأْتِهِم بَيِّنَةُ مَا فِى ٱلصُّحُفِ ٱلْأُولَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተከራካሪዎችህ «ከጌታው በሆነ ተዓምር አይመጣምን?» አሉ:: በመጀመሪያዎቹ ጹሁፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸዉምን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّآ أَهْلَكْنَٰهُم بِعَذَابٍ مِّن قَبْلِهِۦ لَقَالُوا۟ رَبَّنَا لَوْلَآ أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا فَنَتَّبِعَ ءَايَٰتِكَ مِن قَبْلِ أَن نَّذِلَّ وَنَخْزَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy134. እኛም (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አናቅጽህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልዕክተኛን አትልክልንም ነበርን?» ባሉ ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ كُلٌّ مُّتَرَبِّصٌ فَتَرَبَّصُوا۟ فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ أَصْحَٰبُ ٱلصِّرَٰطِ ٱلسَّوِىِّ وَمَنِ ٱهْتَدَىٰ
Amharic Translation - Africa Academy135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም ተጠባባቂ ነው:: ተጠባበቁም የቀጥታዉም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደ ሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደፊት ታውቃላችሁ።» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→