ሱረቱ Al-Hujuraat الحجرات
18 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 106
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُقَدِّمُوا۟ بَيْنَ يَدَىِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው ፊት ነፍሶቻችሁን አታስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሚፈጸመው ነገር ሁሉ አዋቂ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَرْفَعُوٓا۟ أَصْوَٰتَكُمْ فَوْقَ صَوْتِ ٱلنَّبِىِّ وَلَا تَجْهَرُوا۟ لَهُۥ بِٱلْقَوْلِ كَجَهْرِ بَعْضِكُمْ لِبَعْضٍ أَن تَحْبَطَ أَعْمَٰلُكُمْ وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምፆቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ:: ከፊላችሁ ለከፊሉ እንደሚጮህም ሁሉ በንግግር ለርሱ ስትናገሩ አትጩሁ:: እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ከዚህ ተከልከሉ)::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَغُضُّونَ أَصْوَٰتَهُمْ عِندَ رَسُولِ ٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱمْتَحَنَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمْ لِلتَّقْوَىٰ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy3. እነዚያ በአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ድምፆቻቸውን ዝቅ የሚያደርጉ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ለፍርሃት የፈተናቸው ናቸው:: ለእነርሱም ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُنَادُونَكَ مِن وَرَآءِ ٱلْحُجُرَٰتِ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከመኖሪያ ክፍሎቹ ውጭ ሆነው የሚጠሩህ አብዛሀኞቻቸው አያውቁም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَوْ أَنَّهُمْ صَبَرُوا۟ حَتَّىٰ تَخْرُجَ إِلَيْهِمْ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy5. ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ ዝምብለው በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በሆነ ነበር:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy6. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬ ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ህዝባችሁን እንዳትጎዱና ከዚያም በሰራችሁት ነገር ላይ ተጸፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ ٱللَّهِ لَوْ يُطِيعُكُمْ فِى كَثِيرٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ لَعَنِتُّمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ حَبَّبَ إِلَيْكُمُ ٱلْإِيمَٰنَ وَزَيَّنَهُۥ فِى قُلُوبِكُمْ وَكَرَّهَ إِلَيْكُمُ ٱلْكُفْرَ وَٱلْفُسُوقَ وَٱلْعِصْيَانَ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلرَّٰشِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy7. በውስጣችሁም የአላህ መልዕክተኛ መኖሩን እወቁ:: ከነገሩ በብዙው ነገሮች ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር:: ግን አላህ እምነትን ወደ እናንተ አስወደደ :: በልቦቻችሁም ውስጥ አስዋበው። ክህደትን፣ አመፅንና እምቢተኝነትንም ለናንተ የተጠላ አደረገ። እነዚያ እምነትን የወደዱና ክሕደትን የጠሉ ሰዎች እነርሱ ትክክለኛ ቅኖቹ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَضْلًا مِّنَ ٱللَّهِ وَنِعْمَةً وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy8. ከአላህ በሆነው ችሮታና ጸጋ ሲሆን ቅኖች ናቸው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِن طَآئِفَتَانِ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ ٱقْتَتَلُوا۟ فَأَصْلِحُوا۟ بَيْنَهُمَا فَإِنۢ بَغَتْ إِحْدَىٰهُمَا عَلَى ٱلْأُخْرَىٰ فَقَٰتِلُوا۟ ٱلَّتِى تَبْغِى حَتَّىٰ تَفِىٓءَ إِلَىٰٓ أَمْرِ ٱللَّهِ فَإِن فَآءَتْ فَأَصْلِحُوا۟ بَيْنَهُمَا بِٱلْعَدْلِ وَأَقْسِطُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُقْسِطِينَ
Amharic Translation - Africa Academy9. ሁለት የምዕምናን ቡድኖች እርስ በእርስ ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ:: ከሁለት አንደኛይቱ በሌላኛይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመጣ ድረስ ተጋደሏት፤ ብትመለስ ግን በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ:: በነገሩ ሁሉ አስተካክሉ:: አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا۟ بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy10.(አማኞች ሆይ!) ምዕመናኖች ወንድማማቾች ናቸውና በሁለት ወንድሞቻችሁ መካከል አስታርቁ:: ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُونُوا۟ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَآءٌ مِّن نِّسَآءٍ عَسَىٰٓ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ وَلَا تَلْمِزُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا۟ بِٱلْأَلْقَٰبِ بِئْسَ ٱلِٱسْمُ ٱلْفُسُوقُ بَعْدَ ٱلْإِيمَٰنِ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11.እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች በወንዶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ሴቶችም በሴቶች አይሳለቁ:: ከእነርሱ የበለጡ ሊሆኑ ይከጀላልና:: ነፍሶቻችሁንም አታነዉሩ በመጥፎ ሰሞችም አትጠራሩ:: ከእምነት በኋላ መጥፎ ስም ከፋ:: ያልተጸጸተ ሰው በእውነት እነርሱ በዳዮቹ ናቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱجْتَنِبُوا۟ كَثِيرًا مِّنَ ٱلظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ ٱلظَّنِّ إِثْمٌ وَلَا تَجَسَّسُوا۟ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙን ራቁ:: ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና:: ነውርንም አትከታተሉ። ከፊላችሁም ከፊሉን አይማው። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላ ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁት (ሀሜቱንም ጥሉት):: አላህንም ፍሩ:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy13. እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ:: እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ:: አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ብቻ ነው:: አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَتِ ٱلْأَعْرَابُ ءَامَنَّا قُل لَّمْ تُؤْمِنُوا۟ وَلَٰكِن قُولُوٓا۟ أَسْلَمْنَا وَلَمَّا يَدْخُلِ ٱلْإِيمَٰنُ فِى قُلُوبِكُمْ وَإِن تُطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ لَا يَلِتْكُم مِّنْ أَعْمَٰلِكُمْ شَيْـًٔا إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዐረብ ዘላኖች አምነናል አሉ:: «አላመናችሁም ግን ሰልመናል በሉ እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና ጠልቆ አልገባም:: አላህንና መልዕክተኛውን ብትታዘዙ ከስራዎቻችሁ ምንም አይጎድልባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy15. አማኞች እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑትና ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَتُعَلِّمُونَ ٱللَّهَ بِدِينِكُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን?» በላቸው:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَمُنُّونَ عَلَيْكَ أَنْ أَسْلَمُوا۟ قُل لَّا تَمُنُّوا۟ عَلَىَّ إِسْلَٰمَكُم بَلِ ٱللَّهُ يَمُنُّ عَلَيْكُمْ أَنْ هَدَىٰكُمْ لِلْإِيمَٰنِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመስለማቸው ባንተ ላይ ይመፃደቃሉ። «በእስልምናችሁ በእኔ ላይ አትመጻደቁ:: ይልቁንም አላህ ወደ ትክክለኛው እምነት ስለመራችሁ ፀጋውን ውሎላችኋል:: እውነተኞች ብትሆኑ (መመፃደቅ የሚገባው ለአላህ) ብቻ ነው» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱللَّهُ بَصِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy18. አላህ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ሚስጥር ሁሉ ያውቃል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካችም ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→