ሱረቱ Al-Ahqaf الأحقاف
35 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 66
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ
Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ ሚይም፤
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تَنزِيلُ ٱلْكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَكِيمِ
Amharic Translation - Africa Academy2. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፤ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
مَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَآ إِلَّا بِٱلْحَقِّ وَأَجَلٍ مُّسَمًّى وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ عَمَّآ أُنذِرُوا۟ مُعْرِضُونَ
Amharic Translation - Africa Academy3. ሰማያትን፤ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምር እና በተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጂ ለቀልድ አልፈጠርናቸዉም። እነዚያ በአላህ የካዱት የተስፈራሩትን ነገር ደንታ አይሰጡትም።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِى مَاذَا خَلَقُوا۟ مِنَ ٱلْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱئْتُونِى بِكِتَٰبٍ مِّن قَبْلِ هَٰذَآ أَوْ أَثَٰرَةٍ مِّنْ عِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy4. (መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አላያችሁምን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ እስቲ አሳዩኝ:: ወይስ በሰማያት መፍጠር ለእነርሱ ከአላህ ጋር መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደሆናችሁ ይህንን ጉዳይ ከዚህ በፊት የሆነን መጽሐፍ ወይም ከእውቀት ቅሪት እስቲ አምጡልኝ» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy5. እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልሱለትን ጣዖታት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማንነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمْ أَعْدَآءً وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمْ كَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy6. ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ ጣኦቶቹ ለእነርሱ ጠላቶች ይሆናሉ:: እነርሱን መገዛታቸውንም ይክዳሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمْ هَٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. በእነርሱም ላይ አንቀፆቻችን ግልፆች ሆነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ክፍሎች «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ قُلْ إِنِ ٱفْتَرَيْتُهُۥ فَلَا تَمْلِكُونَ لِى مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا هُوَ أَعْلَمُ بِمَا تُفِيضُونَ فِيهِ كَفَىٰ بِهِۦ شَهِيدًۢا بَيْنِى وَبَيْنَكُمْ وَهُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «(ሙሐመድ ራሱ) ቀጠፈው» ይላሉን? «ብቀጥፈው ኖሮ እኔን ከአላህ ቅጣት ለማዳን በምንም አትችሉም:: እርሱ ያንን የምትቀባዥሩበትን ነገር ሁሉ አዋቂ ነው:: በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪነት እሱው በቃ:: እርሱ መሀሪ እና አዛኝ ነውና» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች የተለየሁ ብጤ የሌለኝ አይደለሁም:: በእኔም በእናንተም ላይ ምን እንደሚሰራብንም አላውቅም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን መመሪያ አልከተልም:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قُلْ أَرَءَيْتُمْ إِن كَانَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَكَفَرْتُم بِهِۦ وَشَهِدَ شَاهِدٌ مِّنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَلَىٰ مِثْلِهِۦ فَـَٔامَنَ وَٱسْتَكْبَرْتُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy10. «(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስቲ ንገሩኝ ቁርኣኑ ከአላህ ዘንድ ቢሆንና በእርሱ ብትክዱ ከኢስራኢል ልጆች የሆነ መስካሪ ደግሞ በቢጤው ቢያምንና በእርሱ ላይ ቢመሰክር እናንተ (ግን) ብትኮሩ (በዳይ አትሆኑምን)? አላህ በእርግጥ በደለኛ ህዝቦችን ሁሉ አያቀናም» በላቸው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَوْ كَانَ خَيْرًا مَّا سَبَقُونَآ إِلَيْهِ وَإِذْ لَمْ يَهْتَدُوا۟ بِهِۦ فَسَيَقُولُونَ هَٰذَآ إِفْكٌ قَدِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያም የካዱት ሰዎች ስላመኑት ሰዎች «እምነቱ መልካም ነገር በሆነ ኖሮ ወደ እርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ:: በእርሱም ባልተቀኑ ጊዜ «ይህ ቁርኣን ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمِن قَبْلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامًا وَرَحْمَةً وَهَٰذَا كِتَٰبٌ مُّصَدِّقٌ لِّسَانًا عَرَبِيًّا لِّيُنذِرَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ وَبُشْرَىٰ لِلْمُحْسِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy12. ከፊቱም የሙሳን መጽሐፍ ለሰዎች መሪና የአላህ ጸጋ ሲሆን እንዳወረድን አላየህምን? ይህ ቁርኣን እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ የወረደ ሲሆን የፊቶቹንም መጽሐፍት አረጋጋጭ እና ለበጎ አድራጊዎችም ሁሉ የብስራት መጽሐፍ ነው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy13. «እነዚያ ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም በዚሁ ቃላቸው ላይ ቀጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በእነርሱ ላይ ምንም (ይደርስብናል ብለው) ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም (ነገር ያመልጠናል ብለው) አያዝኑምም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ خَٰلِدِينَ فِيهَا جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው:: በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በዚያ በዱንያ ይሰሩት በነበሩት መልካም ተግባር ምክንያት ያገኙት ምንዳ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ إِحْسَٰنًا حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا وَحَمْلُهُۥ وَفِصَٰلُهُۥ ثَلَٰثُونَ شَهْرًا حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَبَلَغَ أَرْبَعِينَ سَنَةً قَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِىٓ أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتَ عَلَىَّ وَعَلَىٰ وَٰلِدَىَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَٰلِحًا تَرْضَىٰهُ وَأَصْلِحْ لِى فِى ذُرِّيَّتِىٓ إِنِّى تُبْتُ إِلَيْكَ وَإِنِّى مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy15. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ በጎ መዋል እንዳለበት በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው:: በችግርም ላይ ሆና ወለደችው:: እርግዝናውና (ከጡት) መለያው ሙሉ ሰላሳ ወር ነው:: ከዚያም የጥንካሬውን ወቅት በደረሰ ጊዜ አርባ ዓመት በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስከዉን ጸጋህን እንዳመሰግንህና የምትወደውን መልካም ስራም እንድሰራ ወደ ቀናው መንገድ ምራኝ:: ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ:: እኔ ወደ አንተ ብቻ ተመለስኩ:: እኔ ከሙስሊሞች አንዱ ነኝ» አለ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ نَتَقَبَّلُ عَنْهُمْ أَحْسَنَ مَا عَمِلُوا۟ وَنَتَجَاوَزُ عَن سَيِّـَٔاتِهِمْ فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلْجَنَّةِ وَعْدَ ٱلصِّدْقِ ٱلَّذِى كَانُوا۟ يُوعَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያ (ይህንን ባዩች ሁሉ) ከገነት ጓዶች መካከል ሲሆኑ እነዚያ ከሰሩት ስራ መልካሙን የምንቀበላቸውና ከኃጢአቶቻቸዉም የምናልፋቸው ሰዎች ናቸው:: ያንን ተስፋ ይሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ እንሞላላቸዋለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱلَّذِى قَالَ لِوَٰلِدَيْهِ أُفٍّ لَّكُمَآ أَتَعِدَانِنِىٓ أَنْ أُخْرَجَ وَقَدْ خَلَتِ ٱلْقُرُونُ مِن قَبْلِى وَهُمَا يَسْتَغِيثَانِ ٱللَّهَ وَيْلَكَ ءَامِنْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَيَقُولُ مَا هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. ያንንም ለሁለቱ ወላጆቹ አላህን የሚለምኑ ሲሆኑ «በአላህ እመን፤ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፤» ሲሉት «ኡፍ! ከእኔ በፊት የብዙ ክፈለ ዘመናት ሰዎች ሳይወጡ በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመቃብር እንደምወጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ይላልም: "ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም" ይላል።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ حَقَّ عَلَيْهِمُ ٱلْقَوْلُ فِىٓ أُمَمٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِم مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ خَٰسِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy18. እነዚህ እነዚያ ከአጋንንትም ከሰዉም ከእነርሱ በፊት ካለፉት ህዝቦች ጋር የአላህ ቃሉ በእነርሱ ላይ የተረጋገጠባቸው ናቸው:: እነርሱ ከሳሪዎች ነበሩና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلِكُلٍّ دَرَجَٰتٌ مِّمَّا عَمِلُوا۟ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَٰلَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy19. ለሁሉም በሰሩት ስራ ልክ ተገቢ የሆኑ ደረጃዎች አሏቸው:: ስራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው:: እነርሱም አይበደሉም::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يُعْرَضُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ عَلَى ٱلنَّارِ أَذْهَبْتُمْ طَيِّبَٰتِكُمْ فِى حَيَاتِكُمُ ٱلدُّنْيَا وَٱسْتَمْتَعْتُم بِهَا فَٱلْيَوْمَ تُجْزَوْنَ عَذَابَ ٱلْهُونِ بِمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَبِمَا كُنتُمْ تَفْسُقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡበት ቀን ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ:: በእርሷም ተጣቀማችሁ። ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ምክኒያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ ይባላሉ፡
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَٱذْكُرْ أَخَا عَادٍ إِذْ أَنذَرَ قَوْمَهُۥ بِٱلْأَحْقَافِ وَقَدْ خَلَتِ ٱلنُّذُرُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِۦٓ أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአል አሕቃፍ የነበረው የዓድ ወንድም የሆነው ሁድ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላም አስፈራሪዎች ባለፉት መልኩ «ከአላህ ውጪ ሌሎች አማልክትን አታምልኩ:: የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» በሚል ሲያስጠነቅቃቸው (የነበረውን አስታውስ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا لِتَأْفِكَنَا عَنْ ءَالِهَتِنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy22. «ከአማልክቶቻችን ልታሸሸን መጣህን? እውነተኛ ከሆንክ ያንን የምታስፈራራን ቅጣት አሁን እንዲከሰት አድርግ» አሉት።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالَ إِنَّمَا ٱلْعِلْمُ عِندَ ٱللَّهِ وَأُبَلِّغُكُم مَّآ أُرْسِلْتُ بِهِۦ وَلَٰكِنِّىٓ أَرَىٰكُمْ قَوْمًا تَجْهَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy23. «የቅጣቱ መከሰቻ ትክከለኛ ወቅት እውቀት ያለው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: የተላኩበትን መልዕክት ብቻ አደርስላችኋለሁ:: ግና እንደማያችሁ መሀይማን ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَمَّا رَأَوْهُ عَارِضًا مُّسْتَقْبِلَ أَوْدِيَتِهِمْ قَالُوا۟ هَٰذَا عَارِضٌ مُّمْطِرُنَا بَلْ هُوَ مَا ٱسْتَعْجَلْتُم بِهِۦ رِيحٌ فِيهَا عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy24. ለቅጣት የተላከባቸውን (ዳመና) ወደ ሸለቆዎቻቸው አቅጣጫ ሲጓዝ ባዩ ጊዜ «ይህ ዝናብ የሚያወርድልን ዳመና ነው» አሉ:: አይደለም። ይልቁንም ያ በፍጥነት ይከሰት ዘንድ የጠየቃችሁት ቅጣት ነው:: አሳማሚ ቅጣት ያዘለ ንፋስ ነው።
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
تُدَمِّرُ كُلَّ شَىْءٍۭ بِأَمْرِ رَبِّهَا فَأَصْبَحُوا۟ لَا يُرَىٰٓ إِلَّا مَسَٰكِنُهُمْ كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْقَوْمَ ٱلْمُجْرِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy25. በጌታዋ ትዕዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች» (አላቸው)፡፡ ባዶ ቤቶቻቸው እንጂ ሌላ ነገር የማይታይ ሆነው አነጉ:: አመጸኞች ህዝቦችን በዚህ መልኩ እንቀጣለን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ مَكَّنَّٰهُمْ فِيمَآ إِن مَّكَّنَّٰكُمْ فِيهِ وَجَعَلْنَا لَهُمْ سَمْعًا وَأَبْصَٰرًا وَأَفْـِٔدَةً فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُمْ سَمْعُهُمْ وَلَآ أَبْصَٰرُهُمْ وَلَآ أَفْـِٔدَتُهُم مِّن شَىْءٍ إِذْ كَانُوا۟ يَجْحَدُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Amharic Translation - Africa Academy26. ለእናንተ ያልሰጠነውን ኃይልና ምቾት ለእነርሱ ሰጥተናል:: መሰሚያ ጆሮዎችን፤ መመልከቻ ዓይኖችን እና ማሰቢያ አእምሮንም ለግሰናቸዋል:: ግና ጆሮዎቻቸዉም፤ ዓይኖቻቸዉም፤ አእምሮዎቻቸዉም የፈየዷቸው ነገር አልነበረም:: የአላህን አናቅጽ ያስተባብሉ ነበርና:: በመሆኑም በእነርሱ ላይ ያ ያፌዙበት በነበረው ቅጣት ወረደባቸው::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا مَا حَوْلَكُم مِّنَ ٱلْقُرَىٰ وَصَرَّفْنَا ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. በዙሪያችሁ የነበሩ ከተሞችንም አጠፋን:: ይመለሱ ዘንድም ተደጋጋሚ ታዐምራትን አሳይተናቸው ነበር::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَلَوْلَا نَصَرَهُمُ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ قُرْبَانًا ءَالِهَةًۢ بَلْ ضَلُّوا۟ عَنْهُمْ وَذَٰلِكَ إِفْكُهُمْ وَمَا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy28. እነዚያ መቃረቢያ ይሆናቸው ዘንድ ከአላህ ሌላ በረዳትነት የያዟቸው አማልክት በመከራቸው ወቅት ለምን አልረዷቸዉም? ይልቁንም ከእነርሱ ራቁ:: ይህ ሀሰታቸውና ይቀጥፉት የነበረው ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَإِذْ صَرَفْنَآ إِلَيْكَ نَفَرًا مِّنَ ٱلْجِنِّ يَسْتَمِعُونَ ٱلْقُرْءَانَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوٓا۟ أَنصِتُوا۟ فَلَمَّا قُضِىَ وَلَّوْا۟ إِلَىٰ قَوْمِهِم مُّنذِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን የሚያደምጡ ሁነው በላክንልህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ሲነበብ በደረሱ ጊዜ «ዝም በሉ» ተባባሉ:: ንባቡ ሲጠናቀቅም ወገኖቻቸውን ለማስጠንቀቅ ወደ ህዝቦቻቸው ተመለሱ::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
قَالُوا۟ يَٰقَوْمَنَآ إِنَّا سَمِعْنَا كِتَٰبًا أُنزِلَ مِنۢ بَعْدِ مُوسَىٰ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ يَهْدِىٓ إِلَى ٱلْحَقِّ وَإِلَىٰ طَرِيقٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy30. አሉም ለወገኖቻቸው: «ወገኖቻችን ሆይ! ከሙሳ ተውራት በኋላ የተወረደንና ከእርሱ በፊት የወረዱትን መጽሐፍት አጽዳቂ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛው ጎዳና መሪም የሆነን መጽሐፍ አደመጥን::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
يَٰقَوْمَنَآ أَجِيبُوا۟ دَاعِىَ ٱللَّهِ وَءَامِنُوا۟ بِهِۦ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy31. «ወገኖቻችን ሆይ! ለዚህ ወደ አላህ ለሚጠራችሁ ሰው በጎ ምላሽ ስጡ:: በእርሱ እመኑም:: ይህን ካረጋችሁ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃችኋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَمَن لَّا يُجِبْ دَاعِىَ ٱللَّهِ فَلَيْسَ بِمُعْجِزٍ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَيْسَ لَهُۥ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءُ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
Amharic Translation - Africa Academy32. ወደ አላህ ለሚጠራ ሰው ሁሉ በጎ ምላሽ ያልሰጠ በምድር ላይ ከአላህ ቅጣት አያመልጥም:: ከእርሱ ሌላም ረዳት አይኖረዉም:: እንዲህ አይነት ሰዎች ግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::» (አሉ)
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَلَمْ يَعْىَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحْـِۧىَ ٱلْمَوْتَىٰ بَلَىٰٓ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy33. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱም በመፍጠሩም ድካም ያልተሰማው አላህ ሙታንን ህያው ማድረግ እንደሚችል አላዩምን ? በእርግጥም ይህን ማድረግ የሚሳነው አይደለም :: እርሱ ሁሉንም ነገር ቻይ ነውና::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
وَيَوْمَ يُعْرَضُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ عَلَى ٱلنَّارِ أَلَيْسَ هَٰذَا بِٱلْحَقِّ قَالُوا۟ بَلَىٰ وَرَبِّنَا قَالَ فَذُوقُوا۟ ٱلْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy34. እነዚያም የካዱት ሰዎች ሁሉ ወደ እሳት እንዲቀርቡ በሚደረጉ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። «ይህ እውነት አይደለምን ?» ይባላሉ :: «አዎ እውነት መሆኑን በጌታችን በመማል እናረጋግጣለን» ይላሉ:: እርሱም «ታስተባብሉት በነበራችሁት ሰበብ ቅጣትን ቅመሱ» ይላቸዋል::
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
فَٱصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْعَزْمِ مِنَ ٱلرُّسُلِ وَلَا تَسْتَعْجِل لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَ مَا يُوعَدُونَ لَمْ يَلْبَثُوٓا۟ إِلَّا سَاعَةً مِّن نَّهَارٍۭ بَلَٰغٌ فَهَلْ يُهْلَكُ إِلَّا ٱلْقَوْمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች መካከል የጽናት ባለቤቶች እንደታገሱት ሁሉ አንተም ታገስ::(በህዝቦችህ ላይ) ቅጣቱ ይፋጠንባቸው ዘንድም አትጠይቅ:: ያን ቃል የተገባላቸውን ቅጣት በሚያዩ ጊዜ ምድር ላይ ከቀን ውስጥ የተወሰነ ወቅት ብቻ እንጂ እንዳልቆዩ ይሰማቸዋል:: ይህ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው:: ከአመጸኞች ህዝቦች ውጪ ሌሎች እንዲጠፉ ይደረጋልን?
የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
→