caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Muhammad محمد

38 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 95

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ أَضَلَّ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy1. እነዚያ የካዱ እና ከአላህ መንገድ ሌሎችን የከለከሉ አላህ ስራዎቻቸውን አጠፋባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَءَامَنُوا۟ بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy2. እነዚያም ያመኑ በጎዎችንም ተግባራት የሰሩ በሙሐመድ ላይም የተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለሆነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱتَّبَعُوا۟ ٱلْبَٰطِلَ وَأَنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّبَعُوا۟ ٱلْحَقَّ مِن رَّبِّهِمْ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ أَمْثَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy3.ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለተከተሉ ነው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَضَرْبَ ٱلرِّقَابِ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَثْخَنتُمُوهُمْ فَشُدُّوا۟ ٱلْوَثَاقَ فَإِمَّا مَنًّۢا بَعْدُ وَإِمَّا فِدَآءً حَتَّىٰ تَضَعَ ٱلْحَرْبُ أَوْزَارَهَا ذَٰلِكَ وَلَوْ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَٱنتَصَرَ مِنْهُمْ وَلَٰكِن لِّيَبْلُوَا۟ بَعْضَكُم بِبَعْضٍ وَٱلَّذِينَ قُتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَن يُضِلَّ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy4. አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ:: ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው:: መሳሪያውንም አጥብቁ:: በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ:: ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ:: ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው:: ነገሩ ይህ ነው:: አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَهْدِيهِمْ وَيُصْلِحُ بَالَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy5. በእርግጥ ይመራቸዋል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُدْخِلُهُمُ ٱلْجَنَّةَ عَرَّفَهَا لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy6. ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy7. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ ይረዳችኋል:: ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል።ያጸናላችኋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَتَعْسًا لَّهُمْ وَأَضَلَّ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy8. እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው:: ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَرِهُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأَحْبَطَ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy9. ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ دَمَّرَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ وَلِلْكَٰفِرِينَ أَمْثَٰلُهَا

Amharic Translation - Africa Academy10. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ከሓዲያን ሁሉ መጨረሻ እንዴት እንደነበር ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልሄዱምን? አላህ ያላቸውን ሁሉ አጠፋባቸው። ለካሓዲያንም ሁሉ የዚሁ ተመሳሳይ አለባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ مَوْلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَأَنَّ ٱلْكَٰفِرِينَ لَا مَوْلَىٰ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy11. ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ረዳት ስለሆነና ከሓዲያንም ለእነርሱ ረዳት ስሌላቸው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ يُدْخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يَتَمَتَّعُونَ وَيَأْكُلُونَ كَمَا تَأْكُلُ ٱلْأَنْعَٰمُ وَٱلنَّارُ مَثْوًى لَّهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy12. አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና መልካሞችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች ወደ ሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: እነዚያም በአላህ የካዱት በቅርቢቱ ዓለም ብቻ ይጣቀማሉ። እንሰሳዎች እንደሚበሉም ይበላሉ:: የገሀነም እሳትም ለእነርሱ (የሁል ጊዜ) መኖሪያቸው ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ هِىَ أَشَدُّ قُوَّةً مِّن قَرْيَتِكَ ٱلَّتِىٓ أَخْرَجَتْكَ أَهْلَكْنَٰهُمْ فَلَا نَاصِرَ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያች አንተን ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በሀይል ጠንካራ የሆኑ ባለቤቶቻቸዉን ያጠፋናቸው ብዙ ናቸው:: ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِۦ كَمَن زُيِّنَ لَهُۥ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُم

Amharic Translation - Africa Academy14. ከጌታው በሆነች አስረጅ ላይ የሆነ ምዕመን ክፉ ስራቸው ለእነርሱ እንደተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉ ክፍሎች ነውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّثَلُ ٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ فِيهَآ أَنْهَٰرٌ مِّن مَّآءٍ غَيْرِ ءَاسِنٍ وَأَنْهَٰرٌ مِّن لَّبَنٍ لَّمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُۥ وَأَنْهَٰرٌ مِّنْ خَمْرٍ لَّذَّةٍ لِّلشَّٰرِبِينَ وَأَنْهَٰرٌ مِّنْ عَسَلٍ مُّصَفًّى وَلَهُمْ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَمَغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ كَمَنْ هُوَ خَٰلِدٌ فِى ٱلنَّارِ وَسُقُوا۟ مَآءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَآءَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy15. ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት:: በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል:: በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمِنْهُم مَّن يَسْتَمِعُ إِلَيْكَ حَتَّىٰٓ إِذَا خَرَجُوا۟ مِنْ عِندِكَ قَالُوا۟ لِلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ مَاذَا قَالَ ءَانِفًا أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጡ አሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ እውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ:: እነዚያ እነዚህ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተማቸው ዝንባሌዎቻቸውን የተከተሉ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ٱهْتَدَوْا۟ زَادَهُمْ هُدًى وَءَاتَىٰهُمْ تَقْوَىٰهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy17. እነዚያም ወደ ቀናው መንገድ የተመሩት አላህ መመራትን ጨመረላቸው:: (ከእሳት) መጠበቂያቸውንም ሰጣቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَهَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأْتِيَهُم بَغْتَةً فَقَدْ جَآءَ أَشْرَاطُهَا فَأَنَّىٰ لَهُمْ إِذَا جَآءَتْهُمْ ذِكْرَىٰهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy18. የሰዓቲቱንም በድንገት መምጣት እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ምልክቶቿም በእርግጥ መጥተዋል:: በመጣችባቸዉም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَٱعْلَمْ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱسْتَغْفِرْ لِذَنۢبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ مُتَقَلَّبَكُمْ وَمَثْوَىٰكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለመኖሩንም እወቅ:: ስለ ስህተትህም ሆነ ለወንድም ለሴትም አማኞች ስህተት ምህረትን ለምን:: አላህም መዘዋወሪያችሁንም ሆነ መርጊያችሁን ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَتْ سُورَةٌ فَإِذَآ أُنزِلَتْ سُورَةٌ مُّحْكَمَةٌ وَذُكِرَ فِيهَا ٱلْقِتَالُ رَأَيْتَ ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ نَظَرَ ٱلْمَغْشِىِّ عَلَيْهِ مِنَ ٱلْمَوْتِ فَأَوْلَىٰ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ያመኑት ሰዎች (ለዲን ለመታገል ግፊት ያለበት)« የቁርኣን ምዕራፍ አይወረድም ኖሯልን?» ይላሉ:: የጠነከረም ምዕራፍ በወረደና በውስጡም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በእርሱ ላይ እንደወደቀበት ሰው አስተያያት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ለእነርሱው ተገባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

طَاعَةٌ وَقَوْلٌ مَّعْرُوفٌ فَإِذَا عَزَمَ ٱلْأَمْرُ فَلَوْ صَدَقُوا۟ ٱللَّهَ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy21. ታዛዥነትና መልካም ንግግር ይሻላቸዋል:: ትዕዛዙም ቁርጥ በሆነ ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ እውነተኞች በሆኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِن تَوَلَّيْتُمْ أَن تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوٓا۟ أَرْحَامَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy22. ብትሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فَأَصَمَّهُمْ وَأَعْمَىٰٓ أَبْصَٰرَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy23. እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው ያደነቆራቸዉም ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ أَمْ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقْفَالُهَآ

Amharic Translation - Africa Academy24. ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አሉባቸውን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱرْتَدُّوا۟ عَلَىٰٓ أَدْبَٰرِهِم مِّنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلْهُدَى ٱلشَّيْطَٰنُ سَوَّلَ لَهُمْ وَأَمْلَىٰ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy25. እነዚያ ለእነርሱ ቅኑው መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን መቀልበሳቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ለእነርሱም አዘናጋቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا۟ لِلَّذِينَ كَرِهُوا۟ مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ سَنُطِيعُكُمْ فِى بَعْضِ ٱلْأَمْرِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ إِسْرَارَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy26. ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊሉን እንታዘዛችኃለን» ያሉ በመሆናቸው ነው:: አላህም መደበቂያቸውንም ያውቃል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ إِذَا تَوَفَّتْهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَٰرَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy27. መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ በገደሏቸው ጊዜ (ሁኔታቸው እንዴት ይሆናል?)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱتَّبَعُوا۟ مَآ أَسْخَطَ ٱللَّهَ وَكَرِهُوا۟ رِضْوَٰنَهُۥ فَأَحْبَطَ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy28. ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ሁሉ ስለተከተሉ ውዴታውንም ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ حَسِبَ ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَن لَّن يُخْرِجَ ٱللَّهُ أَضْغَٰنَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy29. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሙስሊሞች ላይ የነበራቸዉን ቂሞቻቸውን አላህ አለማውጣቱን ጠረጠሩን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ نَشَآءُ لَأَرَيْنَٰكَهُمْ فَلَعَرَفْتَهُم بِسِيمَٰهُمْ وَلَتَعْرِفَنَّهُمْ فِى لَحْنِ ٱلْقَوْلِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ أَعْمَٰلَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy30. (ሙሐመድ ሆይ!) ብንፈልግ ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸዉም በእርግጥ ባወቅካቸው ነበር:: ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ:: አላህም ስራዎቻችሁን ሁሉ ያውቃልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَنَبْلُوَنَّكُمْ حَتَّىٰ نَعْلَمَ ٱلْمُجَٰهِدِينَ مِنكُمْ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَنَبْلُوَا۟ أَخْبَارَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy31. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ተዋጊዎችንና ታጋሾቹን እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: ወሬዎቻችሁንም (እስከምንገልጽ ድረስ) እንሞክራችኋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَشَآقُّوا۟ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلْهُدَىٰ لَن يَضُرُّوا۟ ٱللَّهَ شَيْـًٔا وَسَيُحْبِطُ أَعْمَٰلَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy32. እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ሰዎችን ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልዕክተኛውን የተከራከሩ ሁሉ አላህን በምንም አይጎዱትም:: ስራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوٓا۟ أَعْمَٰلَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy33. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ:: መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ስራዎቻችሁንም አታበላሹ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ مَاتُوا۟ وَهُمْ كُفَّارٌ فَلَن يَغْفِرَ ٱللَّهُ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy34. እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ያገዱና ከዚያም እነርሱ ከሓዲያን ሆነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا تَهِنُوا۟ وَتَدْعُوٓا۟ إِلَى ٱلسَّلْمِ وَأَنتُمُ ٱلْأَعْلَوْنَ وَٱللَّهُ مَعَكُمْ وَلَن يَتِرَكُمْ أَعْمَٰلَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy35. እናንተ አሸናፊዎች ስትሆኑና አላህም ከናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ:: ወደ እርቅም አትጥሩ:: ስራዎቻችሁን ፈጽሞ አያጎድልባችሁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَإِن تُؤْمِنُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ يُؤْتِكُمْ أُجُورَكُمْ وَلَا يَسْـَٔلْكُمْ أَمْوَٰلَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy36. ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት:: ብታምኑና ቅጣቱንም ብትጠነቀቁ ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል:: ገንዘቦቻችሁንም ሁሉ አይጠይቃችሁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَسْـَٔلْكُمُوهَا فَيُحْفِكُمْ تَبْخَلُوا۟ وَيُخْرِجْ أَضْغَٰنَكُمْ

Amharic Translation - Africa Academy37. እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ:: ቂሞቻችሁንም ያወጣል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰٓأَنتُمْ هَٰٓؤُلَآءِ تُدْعَوْنَ لِتُنفِقُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَمِنكُم مَّن يَبْخَلُ وَمَن يَبْخَلْ فَإِنَّمَا يَبْخَلُ عَن نَّفْسِهِۦ وَٱللَّهُ ٱلْغَنِىُّ وَأَنتُمُ ٱلْفُقَرَآءُ وَإِن تَتَوَلَّوْا۟ يَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُونُوٓا۟ أَمْثَٰلَكُم

Amharic Translation - Africa Academy38. (አማኞች ሆይ!) አስተውሉ:: እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጠሩ ናችሁ:: ከናንተም መካከልም የሚሰስት ሰው አለ:: የሚሰስት ሰው ሁሉ የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂ ነውና:: እናንተ ግን ድሆች ናችሁ:: ብትሸሹም ሌሎችን ሀዝቦች በቦታችሁ ይለውጣል:: ከዚያም ባለመታዘዝ እንደናንተ ብጤዎቻችሁ አይሆኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70