وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ إِحْسَٰنًا حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا وَحَمْلُهُۥ وَفِصَٰلُهُۥ ثَلَٰثُونَ شَهْرًا حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ أَشُدَّهُۥ وَبَلَغَ أَرْبَعِينَ سَنَةً قَالَ رَبِّ أَوْزِعْنِىٓ أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ ٱلَّتِىٓ أَنْعَمْتَ عَلَىَّ وَعَلَىٰ وَٰلِدَىَّ وَأَنْ أَعْمَلَ صَٰلِحًا تَرْضَىٰهُ وَأَصْلِحْ لِى فِى ذُرِّيَّتِىٓ إِنِّى تُبْتُ إِلَيْكَ وَإِنِّى مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy15. የሰውን ልጅ ለወላጆቹ በጎ መዋል እንዳለበት በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው:: በችግርም ላይ ሆና ወለደችው:: እርግዝናውና (ከጡት) መለያው ሙሉ ሰላሳ ወር ነው:: ከዚያም የጥንካሬውን ወቅት በደረሰ ጊዜ አርባ ዓመት በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስከዉን ጸጋህን እንዳመሰግንህና የምትወደውን መልካም ስራም እንድሰራ ወደ ቀናው መንገድ ምራኝ:: ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ:: እኔ ወደ አንተ ብቻ ተመለስኩ:: እኔ ከሙስሊሞች አንዱ ነኝ» አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ በችግር ላይ ኾና አረገዘችው፡፡ በችግርም ወለደችው፡፡ እርግዝናውና ከጡት መለያውም ሰላሳ ወር ነው፡፡ ጥንካሬውንም ወቅት በደረሰ ጊዜ (ከዚያ አልፎ) አርባ ዓመትንም በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያችን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም መልካም ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ፡፡ እኔ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም ከሙስሊሞ ነኝ» አለ፡፡