caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Jaathiya الجاثية

37 አንቀጾች · መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 65

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ حمٓ

Amharic Translation - Africa Academy1. ሓ፤ሚይም፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تَنزِيلُ ٱلْكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَكِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy2. የመጽሐፉ መወረድ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَـَٔايَٰتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy3. በሰማያትና በምድር ውስጥ ለአማኞች ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى خَلْقِكُمْ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَٰتٌ لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን በመፍጠር እና ከተንቀሳቃሽ ነገሮች በምድር ላይ የሚበተነውን ሁሉ በመፍጠሩ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱخْتِلَٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن رِّزْقٍ فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَتَصْرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ ءَايَٰتٌ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. በሌሊትና በቀን መተካካትም፤ አላህ ከሰማይ ባወረደው ሲሳይ (ዝናብ) በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው በማድረጉ፤ ንፋሶችንም (በየ አቅጣጫው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ በቂ ማስረጃዎች አሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy6. እነዚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የሆኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው:: ከአላህና ከማስረጃዎቹ በኋላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيْلٌ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ውሸታም፤ ኃጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት (ጥፋት ተገባው)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْمَعُ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُتْلَىٰ عَلَيْهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسْتَكْبِرًا كَأَن لَّمْ يَسْمَعْهَا فَبَشِّرْهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy8. የአላህን አናቅጽ በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ ይሰማል:: ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማ ሆኖ በክህደቱ ላይ ይዘወትራል:: እናም እርሱን በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا عَلِمَ مِنْ ءَايَٰتِنَا شَيْـًٔا ٱتَّخَذَهَا هُزُوًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy9. ከአናቅጻችንም አንዲትን ነገር ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ ያደርጋታል:: እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِّن وَرَآئِهِمْ جَهَنَّمُ وَلَا يُغْنِى عَنْهُم مَّا كَسَبُوا۟ شَيْـًٔا وَلَا مَا ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوْلِيَآءَ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy10. ከፊታቸዉም ገሀነም አለች:: የሰበሰቡት ሀብትም ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸዉም:: ከአላህ ሌላም ረዳቶች ያደረጓቸው ሁሉ ምንንም አይጠቅሟቸዉም:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذَا هُدًى وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمْ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy11. ይህ ቁርኣን መሪ ነው:: እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ የካዱት ሁሉ ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት ድርሻቸው አለባቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى سَخَّرَ لَكُمُ ٱلْبَحْرَ لِتَجْرِىَ ٱلْفُلْكُ فِيهِ بِأَمْرِهِۦ وَلِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. አላህ ያ ባህርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታዉም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናንተ የገራላችሁ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. ለእናንተ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ያገራላችሁ ነው። በዚህ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يَغْفِرُوا۟ لِلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ أَيَّامَ ٱللَّهِ لِيَجْزِىَ قَوْمًۢا بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «ለእነዚያ የአላህን ቀናት ለማይፈሩት ሰዎች ምህረት (ይቅርታ) አድርጉ» በላቸው:: (አላህ) ህዝቦችን ይሰሩት በነበሩት ነገር ይመነዳልና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا فَلِنَفْسِهِۦ وَمَنْ أَسَآءَ فَعَلَيْهَا ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

Amharic Translation - Africa Academy15. መልካምን የሰራ ሁሉ ጥቅሙ ለነፍሱ ነው:: ክፉንም ተግባር የሰራ ሁሉ ክፋቱ በእርሱው ላይ ነው:: ከዚያም ሁላችሁም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ وَرَزَقْنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلْنَٰهُمْ عَلَى ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ለኢስራኢል ልጆችም መጽሐፍን፤ ሕግን እና ነብይነትን በእርግጥ ሰጠናቸው:: ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው:: (በዘመናቸው ከነበሩት) የዓለማት ህዝብ ላይም አበለጥናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاتَيْنَٰهُم بَيِّنَٰتٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ فَمَا ٱخْتَلَفُوٓا۟ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِى بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከትዕዛዝም ግልጽ ነገሮችን ሰጠናቸው:: እውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በመካከላቸው በትክክል ይፈርዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ثُمَّ جَعَلْنَٰكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ فَٱتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ከሃይማኖት በትክክለኛው ሕግ ላይ አደረግንህ:: ስለዚህ ተከተለው:: የነዚያን የማያውቁትን ህዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّهُمْ لَن يُغْنُوا۟ عَنكَ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ وَٱللَّهُ وَلِىُّ ٱلْمُتَّقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy19. እነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንንም ካንተ አይገፈትሩልህምና። በደለኞችም ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: አላህ የጥንቁቆቹ ወዳጅ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذَا بَصَٰٓئِرُ لِلنَّاسِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው:: ለሚያረጋግጡትም ህዝቦች ሁሉ መሪና እዝነት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ حَسِبَ ٱلَّذِينَ ٱجْتَرَحُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن نَّجْعَلَهُمْ كَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَوَآءً مَّحْيَاهُمْ وَمَمَاتُهُمْ سَآءَ مَا يَحْكُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያ ኃጢአቶችን የሰሩ ሕይወታቸዉንም ሞታቸዉንም ልክ እንደነዚያ እንዳመኑት መልካሞችንም እንደሰሩት ልናደርጋቸው ያስባሉን? (አይስቡ):: ይህ ከሆነ ፍርዱ ምንኛ ከፋ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَخَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ وَلِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. አላህም ሰማያትንና ምድርን በትክክል ፈጠረ:: እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳ ዘንድ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَرَءَيْتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَٰهَهُۥ هَوَىٰهُ وَأَضَلَّهُ ٱللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِۦ وَقَلْبِهِۦ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِۦ غِشَٰوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِنۢ بَعْدِ ٱللَّهِ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዝንባሌውን አምላኩ ያደረገውን አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን በጆሮውና በልቡም ላይ ያተመበትን በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን? ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَالُوا۟ مَا هِىَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا وَمَا يُهْلِكُنَآ إِلَّا ٱلدَّهْرُ وَمَا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنْ عِلْمٍ إِنْ هُمْ إِلَّا يَظُنُّونَ

Amharic Translation - Africa Academy24. (ከሓዲያን) «እርሷም(ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን:: ህያዉም እንሆናለን:: ከጊዜም (ማለፍ) በሰተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ:: ለእነርሱም በዚህ በሚሉት ምንም እውቀት የላቸዉም:: እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّآ أَن قَالُوا۟ ٱئْتُوا۟ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy25. አናቅጻችንም ግልፆች ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ የክርክራቸው ማስረጃ «እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ የቀድሞ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلِ ٱللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ህያው ያደርጋችኋል ከዚያም ያሞታችኋልም:: ከዚያም በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: ይህም ጥርጥር የለበትም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوْمَئِذٍ يَخْسَرُ ٱلْمُبْطِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy27. የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው:: ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَتَرَىٰ كُلَّ أُمَّةٍ جَاثِيَةً كُلُّ أُمَّةٍ تُدْعَىٰٓ إِلَىٰ كِتَٰبِهَا ٱلْيَوْمَ تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ህዝቦችን ሁሉ ተንበርካኪ ሆነው ታያቸዋለህ:: ህዝብም ሁሉ ወደ ግል መጽሐፋቸው ይጠራሉ:: ይባላሉም: «ዛሬ ቀደም ሲል ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰذَا كِتَٰبُنَا يَنطِقُ عَلَيْكُم بِٱلْحَقِّ إِنَّا كُنَّا نَسْتَنسِخُ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy29. «ይህ መጽሐፋችን ነው:: በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል:: እኛ ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ እናስገለብጥ ነበርንና» (ይባላሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُدْخِلُهُمْ رَبُّهُمْ فِى رَحْمَتِهِۦ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْمُبِينُ

Amharic Translation - Africa Academy30. እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባቸዋል:: ይህ እርሱ ግልጽ የሆነ እድልን ማግኘት ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَفَلَمْ تَكُنْ ءَايَٰتِى تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَٱسْتَكْبَرْتُمْ وَكُنتُمْ قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy31. እነዚያም የካዱትማ ለእነርሱ ይባላሉ: «አናቅጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም :: ከሓዲያን ህዝቦችም ነበራችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَٱلسَّاعَةُ لَا رَيْبَ فِيهَا قُلْتُم مَّا نَدْرِى مَا ٱلسَّاعَةُ إِن نَّظُنُّ إِلَّا ظَنًّا وَمَا نَحْنُ بِمُسْتَيْقِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy32. «የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: በእርሷ መምጣት (ጥርጥር) የለም:: በተባለ ጊዜም 'ሰዓቲቱ ምን እንደሆነች አናውቅም መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጂ ሌላ አይደለንም:: እኛም አረጋጋጮች አይደለንም' አላችሁ::» (ይባላሉ)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبَدَا لَهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُوا۟ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy33. የሰሩዋቸው ኃጢአቶችም ለእነርሱ ይገለጹላቸዋል:: ያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقِيلَ ٱلْيَوْمَ نَنسَىٰكُمْ كَمَا نَسِيتُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا وَمَأْوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّٰصِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy34. «በዱንያ የዚህንም ቀናችሁን መገናኘት እንደረሳችሁ ሁሉ ዛሬ እኛም እንተዋችኋለን:: መኖሪያችሁም እሳት ናት:: ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكُم بِأَنَّكُمُ ٱتَّخَذْتُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ هُزُوًا وَغَرَّتْكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا فَٱلْيَوْمَ لَا يُخْرَجُونَ مِنْهَا وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy35. «ይህ እናንተ የአላህን አናቅጽ መቀላጃ በማድረጋችሁና ቅርቢቱ ሕይወት ስለ አታለለቻችሁ ነው» ይባላሉ:: ዛሬ ከእርሷ አይወጡም:: እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلِلَّهِ ٱلْحَمْدُ رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَرَبِّ ٱلْأَرْضِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy36. ምስጋና ሁሉ ለሰማያት፤ ለምድርና ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ የተገባው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهُ ٱلْكِبْرِيَآءُ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy37. ኩራትም በሰማያትም ሆነ በምድር ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70