caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahqaf፣ አንቀጽ 24

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 66 · 46:24

فَلَمَّا رَأَوْهُ عَارِضًا مُّسْتَقْبِلَ أَوْدِيَتِهِمْ قَالُوا۟ هَٰذَا عَارِضٌ مُّمْطِرُنَا بَلْ هُوَ مَا ٱسْتَعْجَلْتُم بِهِۦ رِيحٌ فِيهَا عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy24. ለቅጣት የተላከባቸውን (ዳመና) ወደ ሸለቆዎቻቸው አቅጣጫ ሲጓዝ ባዩ ጊዜ «ይህ ዝናብ የሚያወርድልን ዳመና ነው» አሉ:: አይደለም። ይልቁንም ያ በፍጥነት ይከሰት ዘንድ የጠየቃችሁት ቅጣት ነው:: አሳማሚ ቅጣት ያዘለ ንፋስ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሸለቆዎቻቸውን ተቅጣጪ አግዳሚ ደመና ኾኖ ባዩትም ጊዜ «ይህ አዝናቢያችን የኾነ ደመና ነው» አሉ፡፡ (ሁድም) «አይደለም፤ እርሱ ያ በእርሱ የተቻኮላችሁበት መዐት ነው፡፡ በውስጧ አሳማሚ ስቃይ ያለባት ነፋስ ናት፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70