أَمْ يَقُولُونَ ٱفْتَرَىٰهُ قُلْ إِنِ ٱفْتَرَيْتُهُۥ فَلَا تَمْلِكُونَ لِى مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا هُوَ أَعْلَمُ بِمَا تُفِيضُونَ فِيهِ كَفَىٰ بِهِۦ شَهِيدًۢا بَيْنِى وَبَيْنَكُمْ وَهُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «(ሙሐመድ ራሱ) ቀጠፈው» ይላሉን? «ብቀጥፈው ኖሮ እኔን ከአላህ ቅጣት ለማዳን በምንም አትችሉም:: እርሱ ያንን የምትቀባዥሩበትን ነገር ሁሉ አዋቂ ነው:: በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪነት እሱው በቃ:: እርሱ መሀሪ እና አዛኝ ነውና» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? «ብቀጥፈው ለእኔ ከአላህ (ቅጣት ለማዳን) ምንንም አትችሉም፡፡ እርሱ ያንን በእርሱ የምትቀባዥሩበትን ዐዋቂ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በእርሱ በቃ፡፡ እርሱም መሓሪው አዛኙ ነው» በላቸው፡፡