وَإِذْ صَرَفْنَآ إِلَيْكَ نَفَرًا مِّنَ ٱلْجِنِّ يَسْتَمِعُونَ ٱلْقُرْءَانَ فَلَمَّا حَضَرُوهُ قَالُوٓا۟ أَنصِتُوا۟ فَلَمَّا قُضِىَ وَلَّوْا۟ إِلَىٰ قَوْمِهِم مُّنذِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን የሚያደምጡ ሁነው በላክንልህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ሲነበብ በደረሱ ጊዜ «ዝም በሉ» ተባባሉ:: ንባቡ ሲጠናቀቅም ወገኖቻቸውን ለማስጠንቀቅ ወደ ህዝቦቻቸው ተመለሱ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቁርኣንን የሚያዳምጡ ሲኾኑ ወዳንተ ባዞርን ጊዜም (አስታውስ)፡፡ በተጣዱትም ጊዜ ዝም ብላችሁ አዳምጡ ተባባሉ፡፡ በተጨረሰም ጊዜ አስጠንቃቂዎች ኾነው ወደ ሕዝቦቻቸው ተመለሱ፡፡