وَٱلَّذِى قَالَ لِوَٰلِدَيْهِ أُفٍّ لَّكُمَآ أَتَعِدَانِنِىٓ أَنْ أُخْرَجَ وَقَدْ خَلَتِ ٱلْقُرُونُ مِن قَبْلِى وَهُمَا يَسْتَغِيثَانِ ٱللَّهَ وَيْلَكَ ءَامِنْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَيَقُولُ مَا هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. ያንንም ለሁለቱ ወላጆቹ አላህን የሚለምኑ ሲሆኑ «በአላህ እመን፤ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፤» ሲሉት «ኡፍ! ከእኔ በፊት የብዙ ክፈለ ዘመናት ሰዎች ሳይወጡ በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመቃብር እንደምወጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ይላልም: "ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም" ይላል።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያንንም ለወላጆቹ «ፎህ ለእናንተ ከእኔ በፊት የክፍል ዘመናት ሰዎች (ሳይወጡ) በእርግጥ ያለፉ ሲኾኑ (ከመቃብር) እንድወጥጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ያለውን ሁለቱም (ወላጆቹ) አላህን የሚለምኑ ሲኾኑ (ባታምን) «ወዮልህ፡፡ እመን፡፡ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፡፡» "ይህ የቀደምቶች ተረት እንጅ ሌላ አይደለም" ይላል።