أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ نَتَقَبَّلُ عَنْهُمْ أَحْسَنَ مَا عَمِلُوا۟ وَنَتَجَاوَزُ عَن سَيِّـَٔاتِهِمْ فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلْجَنَّةِ وَعْدَ ٱلصِّدْقِ ٱلَّذِى كَانُوا۟ يُوعَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያ (ይህንን ባዩች ሁሉ) ከገነት ጓዶች መካከል ሲሆኑ እነዚያ ከሰሩት ስራ መልካሙን የምንቀበላቸውና ከኃጢአቶቻቸዉም የምናልፋቸው ሰዎች ናቸው:: ያንን ተስፋ ይሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ እንሞላላቸዋለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚህ (ይህንን ባዮች) በገነት ጓዶች ውስጥ ሲኾኑ እነዚያ ከሠሩት ሥራ መልካሙን ከነሱ የምንቀበላቸውና ከኀጢአቶቻቸውም የምናልፋቸው ናቸው፡፡ ያንን ተስፋ ይስሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ (እንሞላላቸዋለን)፡፡