caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ahqaf፣ አንቀጽ 26

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 66 · 46:26

وَلَقَدْ مَكَّنَّٰهُمْ فِيمَآ إِن مَّكَّنَّٰكُمْ فِيهِ وَجَعَلْنَا لَهُمْ سَمْعًا وَأَبْصَٰرًا وَأَفْـِٔدَةً فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُمْ سَمْعُهُمْ وَلَآ أَبْصَٰرُهُمْ وَلَآ أَفْـِٔدَتُهُم مِّن شَىْءٍ إِذْ كَانُوا۟ يَجْحَدُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Amharic Translation - Africa Academy26. ለእናንተ ያልሰጠነውን ኃይልና ምቾት ለእነርሱ ሰጥተናል:: መሰሚያ ጆሮዎችን፤ መመልከቻ ዓይኖችን እና ማሰቢያ አእምሮንም ለግሰናቸዋል:: ግና ጆሮዎቻቸዉም፤ ዓይኖቻቸዉም፤ አእምሮዎቻቸዉም የፈየዷቸው ነገር አልነበረም:: የአላህን አናቅጽ ያስተባብሉ ነበርና:: በመሆኑም በእነርሱ ላይ ያ ያፌዙበት በነበረው ቅጣት ወረደባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበዚያም እናንተን በእርሱ ባላስመቸንበት (ድሎት) በእርግጥ አስመቸናቸው፡፡ ለእነርሱም መስሚያንና ማያዎችን፣ ልቦችንም አደረግንላቸው፡፡ ግን መስሚያቸውና ማያዎቻቸው፣ ልቦቻቸውም ከእነሱ ምንም አልጠቀሟቸውም፡፡ በአላህ አንቀጾች ይክዱ ነበሩና፡፡ በእነርሱም ላይ ያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ወረደባቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70