فَٱصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْعَزْمِ مِنَ ٱلرُّسُلِ وَلَا تَسْتَعْجِل لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَ مَا يُوعَدُونَ لَمْ يَلْبَثُوٓا۟ إِلَّا سَاعَةً مِّن نَّهَارٍۭ بَلَٰغٌ فَهَلْ يُهْلَكُ إِلَّا ٱلْقَوْمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች መካከል የጽናት ባለቤቶች እንደታገሱት ሁሉ አንተም ታገስ::(በህዝቦችህ ላይ) ቅጣቱ ይፋጠንባቸው ዘንድም አትጠይቅ:: ያን ቃል የተገባላቸውን ቅጣት በሚያዩ ጊዜ ምድር ላይ ከቀን ውስጥ የተወሰነ ወቅት ብቻ እንጂ እንዳልቆዩ ይሰማቸዋል:: ይህ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው:: ከአመጸኞች ህዝቦች ውጪ ሌሎች እንዲጠፉ ይደረጋልን?
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከመልክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡ ለእነርሱም (ለሕዝቦችህ ቅጣት) አትቻኮል፡፡ ያንን የሚስፈራሩበትን ቅጣት በሚያዩ ቀን እነርሱ ከቀን አንዲትን ሰዓት አንጅ እንዳልቆዩ ይኾናሉ፡፡ (ይህ ቁርኣን) በቂ ግሳጼ ነው አመጸኞችም ሕዝቦች እንጅ (ሌሎች) ይጥጠፋሉን?