قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ مُّبِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞች የተለየሁ ብጤ የሌለኝ አይደለሁም:: በእኔም በእናንተም ላይ ምን እንደሚሰራብንም አላውቅም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን መመሪያ አልከተልም:: እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፡፡ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም፡፡ ወደእኔ የሚወረደውን እንጅ ሌላን አልከተልም፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡