caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd الرعد

43 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ الٓمٓر تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ٱلْحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1. አሊፍ ፤ላም ፤ሚይም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፉ አናቅጽ ናቸው:: ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው እውነት ነው:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى رَفَعَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِى لِأَجَلٍ مُّسَمًّى يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ يُفَصِّلُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُم بِلِقَآءِ رَبِّكُمْ تُوقِنُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ያ ሰማያትን የምታይዋት ቋሚዎች ሳይኖራት በችሎታው ከፍ ያረጋት፤ ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፤ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል:: ከጌታችሁ ጋር መገናኘትን ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራትን ይዘረዝራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى مَدَّ ٱلْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنْهَٰرًا وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ ٱثْنَيْنِ يُغْشِى ٱلَّيْلَ ٱلنَّهَارَ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. እርሱ (አላህ)ያ ምድርን የዘረጋ፤ በእርሷም ውስጥ ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ:: በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው:: ሌሊትን በቀን ይሸፍናል:: በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ምልክቶች አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَفِى ٱلْأَرْضِ قِطَعٌ مُّتَجَٰوِرَٰتٌ وَجَنَّٰتٌ مِّنْ أَعْنَٰبٍ وَزَرْعٌ وَنَخِيلٌ صِنْوَانٌ وَغَيْرُ صِنْوَانٍ يُسْقَىٰ بِمَآءٍ وَٰحِدٍ وَنُفَضِّلُ بَعْضَهَا عَلَىٰ بَعْضٍ فِى ٱلْأُكُلِ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. በምድርም ውስጥ የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አሉ:: የወይኖች አትክልቶችም፤ አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ:: በአንድ ውሃ ይጠጣሉ:: በጣዕም ግን ይለያያሉ ከፊልዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን:: በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ብዙ ተአምራት አለበት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن تَعْجَبْ فَعَجَبٌ قَوْلُهُمْ أَءِذَا كُنَّا تُرَٰبًا أَءِنَّا لَفِى خَلْقٍ جَدِيدٍ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِرَبِّهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ ٱلْأَغْلَٰلُ فِىٓ أَعْنَاقِهِمْ وَأُو۟لَٰٓئِكَ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ هُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትደነቅም አፈር በሆንን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን? ማለታቸው በጣም የሚደንቅ ነው:: እነዚህ እነዚያ ሰዎች ማለት እነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ናቸው:: እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው:: እነዚህም የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِٱلسَّيِّئَةِ قَبْلَ ٱلْحَسَنَةِ وَقَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِمُ ٱلْمَثُلَٰتُ وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ لِّلنَّاسِ عَلَىٰ ظُلْمِهِمْ وَإِنَّ رَبَّكَ لَشَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎ ያስቸኩሉሃል! ጌታህም ለሰዎች ሁሉ ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው:: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ብርቱም ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ ءَايَةٌ مِّن رَّبِّهِۦٓ إِنَّمَآ أَنتَ مُنذِرٌ وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተአምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አለላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَحْمِلُ كُلُّ أُنثَىٰ وَمَا تَغِيضُ ٱلْأَرْحَامُ وَمَا تَزْدَادُ وَكُلُّ شَىْءٍ عِندَهُۥ بِمِقْدَارٍ

Amharic Translation - Africa Academy8. አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ጽንስ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: ማሕጸኖች የሚያጎድሉትንም ሆነ የሚጨምሩትን ያውቃል:: ነገሩ ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلْكَبِيرُ ٱلْمُتَعَالِ

Amharic Translation - Africa Academy9. ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ታላቅና የላቀ ጌታ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَوَآءٌ مِّنكُم مَّنْ أَسَرَّ ٱلْقَوْلَ وَمَن جَهَرَ بِهِۦ وَمَنْ هُوَ مُسْتَخْفٍۭ بِٱلَّيْلِ وَسَارِبٌۢ بِٱلنَّهَارِ

Amharic Translation - Africa Academy10. ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ፤ በእርሱ የጮኸም፤ እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን ተገልፆ ሂያጅም የሆነ ሁሉ (እርሱ አላህ ዘንድ) እኩል ነው (አላህ ያውቀዋል)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُۥ مُعَقِّبَٰتٌ مِّنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِۦ يَحْفَظُونَهُۥ مِنْ أَمْرِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ وَإِذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِقَوْمٍ سُوٓءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُۥ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَالٍ

Amharic Translation - Africa Academy11. ለእርሱ ለሰው በስተፊቱም ከኋላዉም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላዕክት አሉት:: አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም:: አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለዉም:: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِى يُرِيكُمُ ٱلْبَرْقَ خَوْفًا وَطَمَعًا وَيُنشِئُ ٱلسَّحَابَ ٱلثِّقَالَ

Amharic Translation - Africa Academy12. እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُسَبِّحُ ٱلرَّعْدُ بِحَمْدِهِۦ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ مِنْ خِيفَتِهِۦ وَيُرْسِلُ ٱلصَّوَٰعِقَ فَيُصِيبُ بِهَا مَن يَشَآءُ وَهُمْ يُجَٰدِلُونَ فِى ٱللَّهِ وَهُوَ شَدِيدُ ٱلْمِحَالِ

Amharic Translation - Africa Academy13. ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል:: መላዕክትም እርሱን ከመፍራት ያጠሩታል፤ መብረቆችም ይልካል። እነርሱም (ከሓዲያን) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል:: እርሱም ሀይለ ብርቱ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَهُۥ دَعْوَةُ ٱلْحَقِّ وَٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُم بِشَىْءٍ إِلَّا كَبَٰسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَٰلِغِهِۦ وَمَا دُعَآءُ ٱلْكَٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ

Amharic Translation - Africa Academy14. ለእርሱ(አላህ) የእውነት ጥሪ አለው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው ጣዖታት ምሳሌው ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን በሩቅ ሆኖ እንደሚዘረጋና እንደማይደርስባት ሰው እንጂ ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸዉም:: እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም:: የከሓዲያን ጥሪ በከንቱ ልፋት እንጂ ሌላ አይደለም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَظِلَٰلُهُم بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ

Amharic Translation - Africa Academy15. በሰማያትና በምድር ያሉት ሁሉ በዉድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ:: ጥላዎቻቸዉም በጧቶችና በማታዎች ይሰግዳሉ:: (1)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُلْ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ قُلِ ٱللَّهُ قُلْ أَفَٱتَّخَذْتُم مِّن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِى ٱلظُّلُمَٰتُ وَٱلنُّورُ أَمْ جَعَلُوا۟ لِلَّهِ شُرَكَآءَ خَلَقُوا۟ كَخَلْقِهِۦ فَتَشَٰبَهَ ٱلْخَلْقُ عَلَيْهِمْ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?» በላቸው:: «አላህ ነው።» በልም። «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትን የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደ እርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አረጉለትና ፍጥረቱ በእነርሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» በልም። «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው:: እርሱም ብቸኛውና ሁሉን አሸናፊው ነው።» በል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَسَالَتْ أَوْدِيَةٌۢ بِقَدَرِهَا فَٱحْتَمَلَ ٱلسَّيْلُ زَبَدًا رَّابِيًا وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيْهِ فِى ٱلنَّارِ ٱبْتِغَآءَ حِلْيَةٍ أَوْ مَتَٰعٍ زَبَدٌ مِّثْلُهُۥ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْحَقَّ وَٱلْبَٰطِلَ فَأَمَّا ٱلزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَآءً وَأَمَّا مَا يَنفَعُ ٱلنَّاسَ فَيَمْكُثُ فِى ٱلْأَرْضِ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْأَمْثَالَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከሰማይ ውሃን አወረደ:: ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ:: ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ:: ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል:: የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል:: ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል:: ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِلَّذِينَ ٱسْتَجَابُوا۟ لِرَبِّهِمُ ٱلْحُسْنَىٰ وَٱلَّذِينَ لَمْ يَسْتَجِيبُوا۟ لَهُۥ لَوْ أَنَّ لَهُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفْتَدَوْا۟ بِهِۦٓ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ سُوٓءُ ٱلْحِسَابِ وَمَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ

Amharic Translation - Africa Academy18. ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት ሰዎች መልካም ነገር ገነት አለላቸው:: እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነርሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር:: እነዚያ ለእነርሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ፍራሻቸዉም ገሀነም ከፋች!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَن يَعْلَمُ أَنَّمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ٱلْحَقُّ كَمَنْ هُوَ أَعْمَىٰٓ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው ልክ እንደዚያ እርሱ እውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يُوفُونَ بِعَهْدِ ٱللَّهِ وَلَا يَنقُضُونَ ٱلْمِيثَٰقَ

Amharic Translation - Africa Academy20. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَصِلُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ وَيَخَافُونَ سُوٓءَ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፤ ጌታቸውንም የሚያከብሩ፤ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ صَبَرُوا۟ ٱبْتِغَآءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُوا۟ مِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِٱلْحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ عُقْبَى ٱلدَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy22. እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ ሰዎች እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው:: እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለችላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

جَنَّٰتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنْ ءَابَآئِهِمْ وَأَزْوَٰجِهِمْ وَذُرِّيَّٰتِهِمْ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِم مِّن كُلِّ بَابٍ

Amharic Translation - Africa Academy23. እርሷም የመኖሪያ ገነቶች ናት:: ይገቡባታል:: ከአባቶቻቸዉም ከሚስቶቻቸዉም ከዝርያቸዉም መልካም የሠራ ሰው ሁሉ ይገባባታል። መላዕክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَلَٰمٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ فَنِعْمَ عُقْبَى ٱلدَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy24. «ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ የተሰጣችሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهْدَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مِيثَٰقِهِۦ وَيَقْطَعُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيُفْسِدُونَ فِى ٱلْأَرْضِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱللَّعْنَةُ وَلَهُمْ سُوٓءُ ٱلدَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy25. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ፤ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለእነርሱ እርግማን አለባቸው:: ለእነርሱም መጥፎ ሀገር ገሀነም አለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ يَبْسُطُ ٱلرِّزْقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقْدِرُ وَفَرِحُوا۟ بِٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ إِلَّا مَتَٰعٌ

Amharic Translation - Africa Academy26. አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል:: ለሚሻውም ያጠባል:: ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ:: የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ ءَايَةٌ مِّن رَّبِّهِۦ قُلْ إِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِىٓ إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ

Amharic Translation - Africa Academy27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደልትም?» ይላሉ:: «አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የተመለሰንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ

Amharic Translation - Africa Academy28. እነርሱም እነዚያ በአላህ ያመኑ ልቦቻቸዉም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው:: አስተውሉ:: አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ طُوبَىٰ لَهُمْ وَحُسْنُ مَـَٔابٍ

Amharic Translation - Africa Academy29. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩት ለእነርሱ ደግ ኑሮና መልካም መመለሻ አለላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَٰكَ فِىٓ أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهَآ أُمَمٌ لِّتَتْلُوَا۟ عَلَيْهِمُ ٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِٱلرَّحْمَٰنِ قُلْ هُوَ رَبِّى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ

Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደ ሆነችው ሕዝብ እነርሱ በአር-ረህማን የሚክዱ ሲሆኑ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ:: «እርሱ አር-ረህማን ጌታዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ተመካሁ። መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ أَنَّ قُرْءَانًا سُيِّرَتْ بِهِ ٱلْجِبَالُ أَوْ قُطِّعَتْ بِهِ ٱلْأَرْضُ أَوْ كُلِّمَ بِهِ ٱلْمَوْتَىٰ بَل لِّلَّهِ ٱلْأَمْرُ جَمِيعًا أَفَلَمْ يَا۟يْـَٔسِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن لَّوْ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَهَدَى ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَلَا يَزَالُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ تُصِيبُهُم بِمَا صَنَعُوا۟ قَارِعَةٌ أَوْ تَحُلُّ قَرِيبًا مِّن دَارِهِمْ حَتَّىٰ يَأْتِىَ وَعْدُ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُخْلِفُ ٱلْمِيعَادَ

Amharic Translation - Africa Academy31. ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች የሚነዱበት፤ ወይም በእርሱ ምድር የሚቆራረጥበት፤ ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ የሚደረጉበት ቢሆን ኖሮ (ይሀው ቁርአን በሆነ ነበር።) በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ወደ ቀናው መንገድ ይመራቸው እንደ ነበረ አያውቁምን? እነዚያን የካዱት በሥራቸው ምክንያት አጥፊ አደጋ የምታገኛቸው ከመሆን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪ መጣ በሀገራቸው አቅራቢያ አንተ የምትሰፍርባቸው ከመሆን አይወገዱም:: አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدِ ٱسْتُهْزِئَ بِرُسُلٍ مِّن قَبْلِكَ فَأَمْلَيْتُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ثُمَّ أَخَذْتُهُمْ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy32. ካንተ በፊት የነበሩትም መልዕክተኞች በእርግጥ ተላግጦባቸው ነበር:: እናም ለእነዚያም ለካዱት ጊዜን ሰጠኋቸው:: ከዚያም በቅጣት ያዝኳቸው:: ቅጣቴ እንዴት ነበር (ምን ያህል የከፋ ነበር።)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَمَنْ هُوَ قَآئِمٌ عَلَىٰ كُلِّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ وَجَعَلُوا۟ لِلَّهِ شُرَكَآءَ قُلْ سَمُّوهُمْ أَمْ تُنَبِّـُٔونَهُۥ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِى ٱلْأَرْضِ أَم بِظَٰهِرٍ مِّنَ ٱلْقَوْلِ بَلْ زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مَكْرُهُمْ وَصُدُّوا۟ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ላይ ተጠባባቂ የሆነው አላህም እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን? ለአላህ ተጋሪዎችን አደረጉ። «ጥሯቸው:: አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታለችሁን? ወይስ ከቃል በቀጥታ ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎቹ በማለት ትጠሯቸዋላችሁን?» በላቸው። በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው። ከእውነቱ መንገድም ታገዱ። አላህ ያጠመመውንም ምንም አቅኚ የለዉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّهُمْ عَذَابٌ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَلَعَذَابُ ٱلْـَٔاخِرَةِ أَشَقُّ وَمَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٍ

Amharic Translation - Africa Academy34. ለእነርሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አለባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም የበረታ ነው:: ለእነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّثَلُ ٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ أُكُلُهَا دَآئِمٌ وَظِلُّهَا تِلْكَ عُقْبَى ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ وَّعُقْبَى ٱلْكَٰفِرِينَ ٱلنَّارُ

Amharic Translation - Africa Academy35. ያች ጥንቁቆች የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (ምሳሌዋ) እንደሚነገራችሁ ነው:: ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ:: ምግቧ ሁል ጊዜም የማያቋረጥ ነው:: ጥላዋም እንደዚሁ። ይህች ገነት የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት:: የከሓዲያን መጨረሻ ግን እሳት ናት::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَاتَيْنَٰهُمُ ٱلْكِتَٰبَ يَفْرَحُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمِنَ ٱلْأَحْزَابِ مَن يُنكِرُ بَعْضَهُۥ قُلْ إِنَّمَآ أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ ٱللَّهَ وَلَآ أُشْرِكَ بِهِۦٓ إِلَيْهِ أَدْعُوا۟ وَإِلَيْهِ مَـَٔابِ

Amharic Translation - Africa Academy36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸውን ወደ አንተ በተወረደው ይደሰታሉ:: ከአህዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ። «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛና በእርሱም እንዳላጋራ ነው። ወደ እርሱ እጠራለሁ:: መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَٰهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم بَعْدَ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّ وَلَا وَاقٍ

Amharic Translation - Africa Academy37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::37. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው:: እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَٰجًا وَذُرِّيَّةً وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِىَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ

Amharic Translation - Africa Academy38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ብዙ መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል:: ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል:: ማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባዉም:: ለየጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَمْحُوا۟ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُ وَيُثْبِتُ وَعِندَهُۥٓ أُمُّ ٱلْكِتَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy39. አላህ የሚፈልገውን ያብሳል:: የሚሻውን ያጸድቃል:: የመጽሐፉ ዋና መሠረትም እርሱ ዘንድ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن مَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ ٱلَّذِى نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ ٱلْبَلَٰغُ وَعَلَيْنَا ٱلْحِسَابُ

Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ያስፈራራናቸውን ቅጣት ከፊሉን በሕይወት እያለህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወቀሳ የለብህም:: ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትህን ማድረስ ብቻ ነው:: ምርመራው ግን በእኛ ላይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا نَأْتِى ٱلْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا وَٱللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِۦ وَهُوَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy41. እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን የምናመጣባት መሆናችንን አላወቁምን? አላህም ይፈርዳል:: ለፍርዱም በይግባኝ ገልባጭ የለዉም:: እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَدْ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَلِلَّهِ ٱلْمَكْرُ جَمِيعًا يَعْلَمُ مَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ وَسَيَعْلَمُ ٱلْكُفَّٰرُ لِمَنْ عُقْبَى ٱلدَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy42. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች መከሩ (አሴሩ):: አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ ነፍስ ሁሉ የምትሰራውን ያውቃል:: ከሓዲያን የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትሆን ወደፊት ያውቃሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَسْتَ مُرْسَلًا قُلْ كَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًۢا بَيْنِى وَبَيْنَكُمْ وَمَنْ عِندَهُۥ عِلْمُ ٱلْكِتَٰبِ

Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች መልእክተኛ አይደለህም።» ይላሉ። «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ እውቀት ባለው ሰው በቃ።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70