caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd፣ አንቀጽ 14

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96 · 13:14

لَهُۥ دَعْوَةُ ٱلْحَقِّ وَٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُم بِشَىْءٍ إِلَّا كَبَٰسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَٰلِغِهِۦ وَمَا دُعَآءُ ٱلْكَٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَٰلٍ

Amharic Translation - Africa Academy14. ለእርሱ(አላህ) የእውነት ጥሪ አለው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው ጣዖታት ምሳሌው ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን በሩቅ ሆኖ እንደሚዘረጋና እንደማይደርስባት ሰው እንጂ ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸዉም:: እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም:: የከሓዲያን ጥሪ በከንቱ ልፋት እንጂ ሌላ አይደለም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለእርሱ (ለአላህ) የእውነት መጥሪያ አለው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዙዋቸው (ጣዖታት) ለነርሱ በምንም አይመልሱላቸውም፤ ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን (በሩቅ ሆኖ) እንደሚዘረጋ (ሰው መልስ) እንጂ፡፡ እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሓዲዎችም ጥሪ በከንቱ እንጂ አይደለም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70