caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd፣ አንቀጽ 33

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96 · 13:33

أَفَمَنْ هُوَ قَآئِمٌ عَلَىٰ كُلِّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ وَجَعَلُوا۟ لِلَّهِ شُرَكَآءَ قُلْ سَمُّوهُمْ أَمْ تُنَبِّـُٔونَهُۥ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِى ٱلْأَرْضِ أَم بِظَٰهِرٍ مِّنَ ٱلْقَوْلِ بَلْ زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مَكْرُهُمْ وَصُدُّوا۟ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ

Amharic Translation - Africa Academy33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ላይ ተጠባባቂ የሆነው አላህም እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን? ለአላህ ተጋሪዎችን አደረጉ። «ጥሯቸው:: አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታለችሁን? ወይስ ከቃል በቀጥታ ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎቹ በማለት ትጠሯቸዋላችሁን?» በላቸው። በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው። ከእውነቱ መንገድም ታገዱ። አላህ ያጠመመውንም ምንም አቅኚ የለዉም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ በነፍስ ሁሉ ላይ በሠራቸው ሥራ ተጠባባቂ የኾነው (አላህ እንደዚህ እንዳልኾነው ጣዖት ብጤ ነውን?) (አይደለም)። ለአላህም ተጋሪዎችን አደረጉ፡፡ ጥሯቸው «አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ኖሮ ትነግሩታላችሁን? ወይስ ከቃል በግልጽ (ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎች በማለት ትጠሩዋቸዋላችሁን?)» በላቸው፡፡ በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው፡፡ ከእውነቱ መንገድም ታገዱ፡፡ አላህም ያጠመመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70