caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd፣ አንቀጽ 17

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96 · 13:17

أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَسَالَتْ أَوْدِيَةٌۢ بِقَدَرِهَا فَٱحْتَمَلَ ٱلسَّيْلُ زَبَدًا رَّابِيًا وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيْهِ فِى ٱلنَّارِ ٱبْتِغَآءَ حِلْيَةٍ أَوْ مَتَٰعٍ زَبَدٌ مِّثْلُهُۥ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْحَقَّ وَٱلْبَٰطِلَ فَأَمَّا ٱلزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَآءً وَأَمَّا مَا يَنفَعُ ٱلنَّاسَ فَيَمْكُثُ فِى ٱلْأَرْضِ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْأَمْثَالَ

Amharic Translation - Africa Academy17. ከሰማይ ውሃን አወረደ:: ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ:: ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ:: ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል:: የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል:: ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል:: ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ ሸለቆዎቹም በመጠናቸው ፈሰሱ፡፡ ጎርፉም አሰፋፊውን ኮረፋት ተሸከመ፡፡ ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም (ማዕድን) ብጤው የኾነ ኮረፋት አልለው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል፡፡ ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70