مَّثَلُ ٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ أُكُلُهَا دَآئِمٌ وَظِلُّهَا تِلْكَ عُقْبَى ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوا۟ وَّعُقْبَى ٱلْكَٰفِرِينَ ٱلنَّارُ
Amharic Translation - Africa Academy35. ያች ጥንቁቆች የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (ምሳሌዋ) እንደሚነገራችሁ ነው:: ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ:: ምግቧ ሁል ጊዜም የማያቋረጥ ነው:: ጥላዋም እንደዚሁ። ይህች ገነት የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት:: የከሓዲያን መጨረሻ ግን እሳት ናት::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (እንደሚነገራችሁ ነው)፡፡ ከሥርዋ ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ ምግቧ (ሁልጊዜ) የማይቋረጥ፤ ነው፡፡ ጥላዋም (እንደዚሁ)፡፡ ይህች የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት፡፡ የከሃዲዎችም መጨረሻ እሳት ናት፡፡