caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Ar-Ra'd፣ አንቀጽ 16

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 96 · 13:16

قُلْ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ قُلِ ٱللَّهُ قُلْ أَفَٱتَّخَذْتُم مِّن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِى ٱلظُّلُمَٰتُ وَٱلنُّورُ أَمْ جَعَلُوا۟ لِلَّهِ شُرَكَآءَ خَلَقُوا۟ كَخَلْقِهِۦ فَتَشَٰبَهَ ٱلْخَلْقُ عَلَيْهِمْ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

Amharic Translation - Africa Academy16. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?» በላቸው:: «አላህ ነው።» በልም። «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትን የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደ እርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አረጉለትና ፍጥረቱ በእነርሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» በልም። «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው:: እርሱም ብቸኛውና ሁሉን አሸናፊው ነው።» በል።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበል «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «አላህ ነው» በል፡፡ «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በእነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» (አይደላም)፤ «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70